መቋሚያ (ሥርጉተ – ሥላሴ)

መቋሚያ።

ከሥርጉተ – ሥላሴ 06.12.2017 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

„በንጉሡ ቤት የነበረው ጃንደረባ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ ኤርምያስን በጉድጓዱ ውስጥ እንዳኖሩት ሰማ።“

(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፰  ቁጥር ፯)

ይድረስ ለፕ/ ዶር. ዳንኤል ተፈራ እና ለአቶ ያሬድ ጥበቡ።

መነሻ።

https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-state-of-the-nation-looking-ahead-beyond-the-crisis-yared-tibebu-and-dr-daniel-teferra-alula-kebede-vol-i-ii-november-2017/4127168.html.

„የአገር ጉዳይ:- ወደ የት እየሄድን ነው?“ የVOAን ግብዣውን ተቀብዬ አዳምጥኩት። ዕይታንም እንዲህ ገልጽኩት።

ውስጠት።

የምናፍቃችሁ የሐገሬ የኢትዮጵያ ልጆች እንዴት ሰነበታችሁ? እንሆ ፕ/ዶር ዳንኤል ተፈራ እና አቶ ያሬድ ጥበቡ ከአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ፕሮግራም ከባለ ክህሎቱ ከጋዜጠኛ አሉላ ከበደ ጋር ባደረጉት ከክፍል አንድ እሰከ ሦስት በነበረው ውይይት የምለው ይኖረኛል – ዛሬ። የውይይቱን ጠቅላላ ይዘቱን በጥልቀት ባልነካካው ስለሚሻል – አልፈዋለሁ። ግን ከውይይቱ ውስጥ ለእኔ ትኩረት ቅርብ የሆኑትን ተቀራራቢ ሃሰቦችን ብቻ አነሳለሁ። ስለዚህም ፕ/ዶር. ዳንኤል ተፈራ ባነሱት ላይ አብዝቼ አተኩራለሁ። „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ የዚህ ዓመት ዓውራ ፕሮጀክቴ ስለሆነ። በአቶ ያሬድ ጥበቡ አለዝበኝ ዕይታም ላይ ትንሽ አስተያዬት ለምራቂ እጨምራአለሁ። እንዲሁም ተያያዥነት ስላለው የህዳር 2.2017 እ.አ.አ የኢሳትን የሦስትዮሽ ብሄራዊ ውይይት እፍታን ላፍታ ዳስሼ ዕርገት በዶቸቬለ የቅኔ ጉባኤ ይሆናል።

የማከብረዎት ፕ/ ዶር. ዳንኤል ተፈራ እንደምን አሉልን? ሦስቱንም የውይይት ክፈለ ጊዜ በተደሞ ሆኜ አዳምጨዋለሁ። ዘግዬት ያልኩትም አላምጦ መዋጡን ፈልጌው ነው። ሁሉንም ጊዜ ወስጄ በተደጋጋሚ ኖት እያያዝኩኝ ማዳመጥ ነበርብኝ። እርሰዎ ያነሷቸው መሠረታዊ ጉዳይ ሁለት ናቸው ብዬ አምናለሁ። አንደኛው „የአካዳሚ ነፃነት“ ሲሆን፤ ሁለተኛው „የሀገርን ህይወት“ አደራጃጀት። ነፍስዎት መልክዕምድራዊ አቀማመጥን የተከተለ አስተዳደር ለዘላቂ ችግር ፍቱን ነው የሚል ነው። ይህ ወደ አባቶቻችን ልቅና እንመለስ፤ ያን ክብር እንስጠው ይመስለኛል። አባቶቻችን ቀድመው የሠሯቸውን የጥበባት፤ የቅርሳት፤ የትውፊታት ሥነ – ነፍስ ዛሬ ላይ ሆነን ስንመለከታቸው አይደለም የዛሬ ትውልድ በቀጣይ ከ500 ዓመት በኋዋላ እንኳን ይመጣሉ፤ ሊገኙ ይችላሉ ተብሎ መተንበይ ይቻል ይሆን ያሰኛል። ይህም ይመስለኛል ኢትዮጵያን ሠርቶልን ያቆዬው። መሰረታዊ ምክንያቱ እኔ እንደማስበው፣ እንደሚገባኝ እና እንደምረዳው አባቶቻችን ከፈጣሪያቸው ጋር የቀረበ የመንፈስ ግንኙነት ስለነበራቸው ከእነሱ ጋር መንፈስ ቅዱስ እንደነበረ ነው የማምነው። መንገዳቸው ቀና ነበር ባልልም፤ መደረሻቸው ግን አሸናፊ እና ቀጣይነት የነበረው ቅኔ ነበር። ደግሞም ይገባል፤ በታሪክ እኮ በትረ ሥልጣናቸውን ትተው ገዳም የገቡ ነገሥታት ያላት ሐገር ናት – ኢትዮጵያ። በትረ ሥልጣን ትቶ ገዳም መግባት ቀርቶ በትረ ሥልጣን ማከፋፈል አይችልም የዛሬው ትውልድ። በሁሉም ቦታ የሚታዬው የሥልጣን መማከል ነው። የሚገነባው የሃሳብ ተዋረድ አለመኖሩ ግለሰቦችን ከሚችሉት በላይ የተወጠሩ ሆነው መፍትሄዎች ታፍነው እንዲያምጡ የሚሆኑበትም መሰረታዊ ምክንያት ይህ ይመስለኛል። ሥልጣን እና የሃላፊነት ክፍፍል ከሌለ፤ አምልኮቱ የተቋጠረ መፍትሄ፤ አዲስ ሃሳብ አምንጭነቱም የታቆረ ነው የሚሆነው። ይሄ የዛሬው ዘመን ሥልጣኔ ከአንድ ተራ ገበሬ ሐገርን ሊያድን የሚችል መፍትሄ ሊፈልቅ የሚችል ስለመሆኑ መታማመኑ እንዳይኖር አድርጎታል – አዳዲስ የመፍትሄ ሃሳቦችንም ክው አድርጎ አድርቆታል። ሁሉንም መፍትሄ አምንጩ ወይንም ሌሎች ያአፈለቁት የመፍትሄ መንገድ በአንድ ታቦት ይሁንታ ማጽደቅ ያባት ነው፤ ጠቃሚ እስከሆነ ድረስ ግን የሌላው ህሊና አምጦ የወለደውን መቅኖ ማፈሰሱ ነው ችግሩ። እያንዳንዱ ሰው የራሱ ቀለም አለው። እያንዳንዱ ልጀ ሲወለድ የተሰጠው ልዩ መክሊት አለው። ይህ ነፍስ ዕድሉን ካለገኘ የጋን መብራት ነው የሚሆነው። ይህ በግል ህይወት ሳይሆን በዘመን ሽግግር፤ በትውልድ ውርርስ ላይ የጠቆረ ዕጣ ፈንታ ያጫል። እኛ የምንዳክረውም በዚህ የቀለበት ዳጥ እና ረግርግ የሽምጥ ሸለቆ ነው። ፖለቲካኞችን በሚያስደስት ፌስታ ብቻ ላይ ነው የተቀረቀረነው።

ስለዚህም ነው በአለንበት ተቸክለን የችግር ራሮተኞች፤ የችግር እስረኞች የሆነው። ችግሮች ውጠውናል። አባቶቻችን ደግሞ ከብት እረኛ ዛሬ ምን አለ ብለው፤ የአንድ እረኛ መልዕክትን ህግ እንዲረቀቅበት ያደርጋሉ። ትጥቅ እንዲጠብቅበት ይወስናሉ። ስንቅ እንዲዘጋጅ ያደርጋሉ። መስታውታቸው ነው፤ እራሳቸውን ያረቁበታል። ውስጣቸውን በቀጥታ ያርሙበታል። የኪነ ሰው ትንበያም እገዳ የሚጣልበት ሳይሆን የምልዕት መንፈስ አብሮ እንዲከተምበት ይታደሉበታል። ስለሆነም አባቶቻችን ክ/ ሀገራትን ሲያደራጁ ጥበቡ የተሰጣቸው ከሰማዬ ሰማዬት ስለነበር ውስጡ ቅዱስ መንፈስ ነበረው። የተባረከ ነበር። የሰላም መሰረት እንጂ እንዲህ ውስጣዊ መንፈስን የሚሸነሽን ቢላዋ አልነበረም። የመቃቃር ዓዋጅ ነገሪም አልነበረም። ሌላው ቀርቶ ከአንዱ ክ/ሐገር ተክፍሎ ለሌላው ሲሰጥ አባቶቻችን ቅሬታ አያምጡም። ለምሳሌ ሐይቅ እና ባህርዳር የበጌምድርና የስሜን ግዛት ነበሩ። ይህም ብቻ አይደለም ማዕከላዊ መንግስት ከወሎ ወደ ሽዋ በቅዱስ አባታችን በሰላም እንዲሸጋጋር ሲጠዬቁ የወቅቱ የፖለቲካ ሊቃናት በጸጋ ነበር ያስተናገዱት። ይህ ልቅናቸው፤ ጥልቅነታቸውን ለማግስታዊነት ያላቸውን የፍቅር፤ የአብሮነት ቅድስና ያሳዬናል። በሌላ በኩል የሀገርን ልዑላዊነት በማስጠበቅ እረገድም ቢሆን ምንም የመገናኛ አውታር ባልነበርበት፤ የጠላቶቻቸው ምኞት ማርከሻው ከመዳፋቸው ነበር። የሀገር ሉዕላዊነት በአባቶቻችን ዘንድ ከበትረ ግላዊ ሥልጣን፤ ከኢጎ እና ከበቀል ማወራራጃ ሴራ በላይ ነበር። ጥበቡ ከማስተዋሉ፤ ጥበቡ – ከፈርሃ እግዚአብሄር ጋር፤ ጥበቡ ከኢትዮጵያዊ ባህል እና ይሉንታ ጋር የተጠለፈ፤ አብዝቶ ማስተዋል የተሰጣቸው ድንቆች ስለነበሩ። ዛሬ ጀርመን የሰው ልጆችን ህይወት በጤና ሊታደግ መቻሉ ብቻ ሳይሆን፤ ለኢኮኖሚ ልዕልናቸውም መሰረት የሆነው እኮ „መጸሐፈ ፈውስ“ ነው። ለዚህም ነው ጀርመኖች ግዕዝን እንደ አንድ የእውቀት ምንጭ አድርገው ተቀብለው የዩንቨርስቲያቸው ሁሉ ንጉሥ ያደረጉት። ሚስጢሩ – የመኖር፤ ጥልቀቱ – የፍልስፍና፤ ፍስፍናው – የጥበብ፤ ልቅናው – የመፍትሄ፤ ራዕዩ – የትውልድ፤ ውጤቱ – የነገ መሠረት ከዚያ እንዳለ ያውቃሉ ከጥቁሮች መንደር። ባያወጡትም ኢትዮጵያ አብዝቶ ቅድስና የተሰጣት ሀገር መሆኗን አሳምረው ያውቃሉ። እናም በዘዴ ውስጧን ሰርቀውታል፤ ሁነውበታልም።

እናት ሐገራችን ኢትዮጵያ እኮ መልዐምድራዊ አቀማመጧ ራሱ በጠላት እጅ ይበቃሻል ተብሎ አለነበረም ተሰምሮ የተሰጣት። በደም እና በአጥንት የተገነባ ወ/ሮ ሞንዳላ ምስለ – አድህኖ ነበር የገፆዋ ሆነ የቁመናዋ ተክለ – ተፈጥሮ። እንደ ዛሬው የጣሊያን ክህሎተ ባንዳነት አንገቷ ሳይቆረጥ። እስኪ የኔዎቹ የቀደመውን ካርታዋን ግርማ ሞገስ ከሌሎች ሀገሮች ጋር የለውን የካርታ ሞድ እዩት። እና ሃሳበዎት አዎንታዊ ነው – ለእኔ። የአምክንዮም አቅም አለው ባይ ነኝ።

ሌላው ሁለተኛው ነጥብ ያነሱት „የአካዳሚ ነፃነት ነው።“ እንደ እኔ እንዲያውም የአካዳሚ ነፃነት አብዮት ወይንም ንቅናቄ ቢባል ሁሉ እውዳለሁ። በኢትዮጵያ ብዙ ባለቤት የሌላቸው አመክንዮች አሉ። ለምሳሌ የፖለቲካ ማንፌስቶ ባሪያ ያልሆኑ የወጣቶች – የሴቶች – የህጻነት – የአቅመ ደካሞች ወዘተ … ስለሆነም ይህም የተገባ መንገድ ነው ብዬ አምናለሁ። የሐገር መሰረታዊ ህልውና አስቀጣይ ሁነቶች በክህሎት ላይ መመስረት ይኖርባቸዋል። ይህም ማለት በፖለቲካ ማንፌስቶ ተጠላይነት ሳይሆን በፋክት ምስሶነት። እስከዛሬ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ባለቤት ካልነበራቸው አምክንዮች ውስጥ ነበር ዕወቀትን መሰረት ያደረገው የነፃነት ጉዞ፤ ለዛውም መፍትሄ አመንጭነቱ እሳቤ ውስጥ ሳይገባ የተዘለለ። ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ አቅምን ገንብቶ እራስን ችሎ በተደራጀ ሁኔታ የሃሳብ ተፎካካሪ ሁኖ መውጣት ብቻ ሳይሆን ለፕሮፖጋንዳ ሰለባ ሆኖ ላለመውጣት የሚያስችሉትን ቅድመ መሰናዶ ሁሉ አሟልቶ ተቋም ሆኖ ቢወጣ ምኞቴ ነው። በጥናት እና በምርምር ሐገርን መምራት የሚማለዱ ሂደቶች እውቅና ካልተሰጣቸው ሥነ – ልቦናዊ ሃብቶች፤ የተፈጥሮ ሃብቶች፤ የሐገር ንብረቶች፤ አላግባብ የማይባክኑ አቅሞችን በ አቅም ውስጥ ማደራጀት ወቄት ሊወጣለት የሚቻል አይሆንም። በእኛ ዕድሜ እንኳን ያየናቸው ምግባሮች የአዎንታዊ ተወራራሽና ተሸጋጋሪነት፤ ትውፊታዊ መንገድ እዳሪ አዳሪ ነው የሆኑት። ይህ የመንፈስ ጽኑ መቋሚያ ለመፍትሄ አምንጭነት እንዲሆን በተጠና እና በተደራጀ መልኩ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋጋር በሚችል መልኩ በተከታታይ ቢሠራበት መልካም የሚሆነው ጠቃሚ እና አትራፊ በመሆኑም ነው። ሁሉንም በሁሉነት መሰረት ያጸናል። ጠንከሮችን በእርሾ ላይ ያነጽል። ደካሞችን በክህሎት አስተካክሎ ያበለጽጋል። በግልፍተኝነት ወይንም በጥላቻ፤ ወይንም በበታችነት ስሜት በስንት የህሊና እና የመዋለ ንዋይ ፍሰት የተገነቡ አንጡራ ሃብቶች ሃላፊነት በጎደለው መልኩ በጅምላ ማፍረስ እና ማቃጣል አይኖርም። ከሁሉ በላይ በሂደቶች የሰው ሃይል መስዋዕትነቶች ከቁሳዊ ትርፎች በላይ ናቸው። ከዚህ አንፃር ነው ሐገር – ትውልድ – ነገ ሊገነባ የሚገባው።

አሁን ባለው ሁኔታ በሙሁራዊ አገልግሎት የእንርዳችሁ ጥያቄን „ ዕውቀቱን እናካፍላችሁ፤ ሥልጣኑን እንካፈል አላልነም“ ይህ ያነሱት ጥልቅ ሃሳብ ለማስተናገድ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የጫካ ተመክሮ ቁመናው አይፈቅድም። ተፈጥሮው እንደዚህ ላለ በእውቀት ላይ የተመሰረተ የመፍትሄ ክኒን አይመቸውም። ይህ በተሟላ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ንጹህ አየር ሲኖር ብቻ ነው ቦታ ሆነ ዕውቅና የሚያገኘው። ለተረጋጋ ሀገራዊ የፌድራሊዘም የአፈጻጸምም ሂደት የቋንቋ፤ ወይንም ተፈጥሯዊ ክልሎችን መሰረት አድርጎ ለሚለውም ወሳኝ በትረ ጉዳይ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የተመሰረተበት የማንፌስቶው ምስለ ተፈጥሮ ብቻ ሳይሆን፤ የአንጀት ጉበቱ ተፈጥሮ በፍጹም ሁኔታ አይፈቅድም። ክቡርነተዎት ያነሷቸው ነጥቦች በተረጋጋ ሥርዓት፤ በተረጋጋ አዕምሮ፤ በበሰለ ውይይት ሊከወኑ የሚችሉ የተደሞ አናቶች ናቸው። አብሶ ከዚህ ከህብረተሰባዊነት ፍልስፍና ጋር በፍጹም ሁኔታ በአካልም በመንፈስም የመለወጥ የውስጥ አብዮት ጋር በእጅጉ የሚያያዝ ነው ጽንሰ ሃሳቡ። ይሄ ያደገ ምልክታ ሥር – ነቀል ነጻነት ለማድረግ ከቆረጠ እና በተግባርም ከሆነ፤ ሀገራዊ ትውፊቶችን ውስጥ ካደረገ ዕውነተኛ የብሄራዊ ስሜት መኖር ጋር የሚመጣ ነው። ለዚህ ምን ያህል ተዘጋጅተናል? እራስን በመመዘን ውጤቱን መለካት ይቻላል። በውስጡ በምንፈልገው ፍላጎት ስለመኖራችን ሆነ ለፍላጎታችን ታማኝነታችን ምን ያህል ስለመሆኑም የራስን ጓዳ መፈተሹ ግብረ ምላሹን ይሰጣል።

የማከብረዎት አሁን እርስዎም አንደሚያውቁት ኢትዮጵያ የምትነሳው በውጪው ዓለም በራህብ በተጎሳቆለ የህጻን ምስል ነው። ገናናነቷ ብቻ ሳይሆን ተፈሪነቷን የማይሹት „ኢትዮጵያ“ የሚለውን ሥያሜ ቅስሙን ለመስበር በመደበኛ እና በተከተታይ ይሠሩበታል። አሁን ሰሞናቱ ላይ ያለው መጽሐፍ ቅዱስን ወደ „ኩሽ“ የመለወጥ እንቅስቃሴም ያለው ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው። ምቾት አልሰጣቸውም ሃያላኑን። የእኛ አዲስ ትውልድ አባል የሆነው ደግሞ የማንነቴ መግለጫ „ድህነት“ ሀገሬ ደግሞ የተወለድኩበት „አዲስ አባበ“ እያለን ነው ጋዜጠኛ/ ጦማሪ በፈቃዱ ሃይሉ። እንግዲህ በኢትዮጵያ ስንት ዋና ከተሞች፤ ስንት የገጠር ከተሞች፤ ስንት የቀበሌ ገበሬ መንደሮች አሉ። እነሱ ሁሉ የሐገር የመወለጂያ የዜግነት መለያ እንዲሆኑ ነው የሚሻው ወጣቱ ፈላስፋ፤ ወጣቱ ተማራማሪ። ኢትዮጵያ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በዘጠኝ መንግሥታት፤ በአንድ የትግራይ ሥርዎ – መንግሥት ሥር የወደቀች ናት። ትግራይ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቷ እንደ ክልልም አንደ ሀገር መሪነትም ነው። ስለዚህ በድምሩ አስር መንግሥት አለ ማለት ነው። ረቀቅ ያለው ወጣት ደግሞ ከዚህም ባለፈ በሺህ ሸንሽኗታል። ኢትዮጵያን „ኢትዮጵያ“ የሚለው ሥያሜዋ አይመጥናትም መውረድ አለበት „ኢትዮጵያዊ ዜግነት“ መባል ቀርቶ „ድህነት“ እንባል እያለን ነው። ሀገርም „ኢትዮጵያ“ መባሉ ቀርቶ አጥቢያ አድባራት ላይ ይሁን ባይ ነው። ይህን ወጣቱ „ከብራና ራዲዮ“ ጋር ያደረገውን ክፍል አንድ እና ሁለትን ማድመጥ የሚችሉ ከሆነ፤ እንደ ሊቀ – ሊቅነትዎት ስሜቱን በዳበረ የእውቀትና የልምድ ተመክሮዎት ማዬት ያስችለዎታል ብዬ አስባለሁ።

ሌላው እውቀቴን አቀናለታለሁ የሚሉት የወያኔ ሃርነት የአፓርታይድ አገዛዝ „ኢትዮጵያ“ የሚል የጥበብ ምርትን እራሱ አይፈልግም። ስለምን ይመስለዎታል ጠቢቡ ቴወድሮስ ካሳሁን ጋር „ድምጽን በድምጽ ከመሻር ሙሉ ሥልጣን ጋር መንግሥነት“ ታክሎ አቲካራ ከአንድ ዕንቡጥ ከያኒ ጋር ግብግብ የሚገጥመው። „ኢትዮጵያ የሚሊዮኖች ድምጽ“ እንድትሆን አይፈልግም እና። በዚህ መንፈስ ውስጥ ነው „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ሊነበብ፤ ሊተረጎም ሊመሳጠር የሚገባው። እኔ እንዲያውም ትንሽ ገፋ አድርጌ የተመለከትኩበት መንገድ አለኝ። እኔ እንደማስበው „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ውስጡን ገብቼ እንዳየሁት የጠቢቡን ቴወድሮስ ካሳሁን ብሄራዊ ጥሪ በጥበብ እና በቅኔ የተቀበለ፤ ያጸደቀ፤ የተከተለ ደቀመዝሙር ለመሆን ከህሊናው የፈቀደ ሐዋርያዊ መልዕክት፤ ልዩ ተልዕኮን ፈቅዶ በራሱ ላይ የጫነ አድርጌ ነው የምቀበለው። አንድ ጸጋውን አብዝቶ የሰጣቸው „የአማራ“ በሚባለው ጉባኤ ላይ „ስለ ማር እሰከጧፍ“ አንስተው „ይህን የአማራ ሚዲያ ማቀንቀን ያልቻለ ማን እንዲቀነቅንለት ይፈልጋል?“ ሚዲያውን በማለት፤ እጅግ በሚፈትን፤ እጅግም ፋክትን በተነተራሰ ዕውነት ላይ የአማራን ሚዲያ ሞግተውታል። እኔ „ፍቅር አስከ መቃብርን“ 15 ጊዜ ተማሪ እያለሁ ሥራ ላይም ሆኜ አንብቤ የማልጠግበው ሩቅ ተመልካች ሥነ -ሕይወት ነው። በዬካቲት 66 የፖለቲካ ኢንስቲቱዩትም በዬክፍላችን በዬዕለቱ ትረካው በድምጽ ይቀርብ ነበር። እና ለእኔ ወጣትነቴን ብቻ ሳይሆን መክሊቴን አደበባይ ያወጣሁበት ንጹህ ውሃዬ ነው። አሁን በዛብህን፤ ሰብለወንጌልን፤ ፊታዋራሪ መሸሻን፤ ጉዱ ካሳን የወከሉት ገጸባህሪያት የት ተገኙ? የሚገርም ነው እኮ እራሱ በዛብህ፤ እራሱ ጉዱ ካሳ፤ እራሷ ሰብለወንጌል ያ ድንቅ ጥበብ ክህሎቱን ያሰረፈት መንፈስ ነበር። የእኔ ልዑቂት እንዴት ዳይሪክት እንዳደረገችው፤ በዛች ድንቅ የፊልም ዳይሬክተር እና ተዋናይት ወ/ሮ አምለሰት ሙጬ ነፍስ የብቃት ዕጹብና የማይማር ነፍስ ከቶ የት ይመደብ? ጎታው፤ ወራንታው፤ የቅቤ ቅሉ፤ ግሬራው፤ ፋጋው፤ ምድጃው … አባይ በርሃ፤ የገበሬው ለዛ እና ጠረን ስንቱ … ይህ ሁሉ ታሰረ። ይህን ማስፈታት እንደ ሚዲያ አለባቸው „አማራ“ ላይ ያሉ ትንታግ ጋዜጠኞች። በማይቻለው መቻልን የሚችሉ ዝማሬዎች ናቸውና። ባልመካም አብዝቼ እጸልይላቸዋለሁ።

https://www.youtube.com/watch?v=X4psTCJL1nY

Ethiopia የአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን የቴዲ አፍሮን ዘፈን አለማጫወቱ ጥያቄ አስነሳ | Teddy Afro

ወደ ቀደመው ሃሰቤ ስመለስ „ዜግነቴ ድህነት“ ሐገሬ „የተወልድኩባት አዲስ አባባ“ የሚለውን የፍልስፍና ጣሪኒያና ግድግዳ፤ የመንፈስ አቅም እና አቋም መንፈሱን በአሉታዊ ሳዬው፤ የዚህ ማራከሻ ነው ለእኔ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው። “ እንዲህ ዓይነት ዕሳቤዎችን ሁሉ ወጌሻ አልባ አድርጎ ውልቅልቁን ያወጣ፤ ፍርሃትን የተጸዬፈ፤ እጅግ ደፋር አምክንዮ ነው። ጤዛ አይደለም ግን ማንዘርዘሪያ ነው። ብዙ ስውር አጀንዳዎችን ሁሉ ነው ሰላማዊ በሆነ፤ ጸጥ ባለ መንፈስ ያራገፈው። ስለሆነም እኔ በተደሞ ሆኜ በውስጤ አስቀምጬ ስመረምረው እንደ መርህ፤ እንደ መንገድ ጠራጊ፤ እንደ አዳኝ መንፈስ አድርጌ ነው በግሌ የምቀበለው። ከዚህ ላይ ነው ከእርስዎ ሃሳብ ጋር በፍጹም ሁኔታ የምለያዬው። እርስዎ ያነሷቸው ሃሳቦች ጠረጴዛ ላይ በፋክት ሁነኛ ጠበቃነት፤ በተረጋጋ መንፈስ፤ በሙሉ ነፃነት ሁነኛ መፍትሄ ማግኘት የሚቻለው ሁሉም ኮተቱን ወለቅ አድርጎ፤ በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ መጠቃለል ሲችል ብቻ ነው። የግለሰቦች ሃሰብ እንደ ዜጋ ክብር፤ እንደ ዜጋ ግርማ ሞገስ አግኝቶ አድማጭ፤ አወያይ ሲያገኝ ለመፍትሄያችን ቅርበት ይኖረዋል። ለመንገዳችንም መሃንዲስ። ይህን እኔ እንደማስበው „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ የሁሉንም መንፈስ በእኩልነት ያስተናግደዋል የሚል ሙሉ ዕምነት እና ተስፋም ስለአለኝ ነው። እርስዎ እንዳሉት „ኦሮምያ ለኦሮምያ ብሎ ኢትዮጵያዊነት የለም ነው“ የሚሉት።  „ኦሮምያ ለኦሮምያ“  እዬተባለ በዚያ ላይ ጊዜ አላጠፈም ሰው መሆን ነው የሚበጀው ብለዋል።“ ስለዚህ „ሰው“ የሚለው መጠሪያ እሳቸውንም አይዘለም። አቶ ለማ መገርሳም የሰው ማህበርተኛ ናቸው። „ሰው“ በሚለው ተፈጥሮ ውስጥ አቶ ለማ መገርሳ አሉ። አቶ ለማ መገርሳም „ሰው“ ናቸው። ማህበረሰብ የሰዎች ማህበር ነው። አቶ ለማ መገርሳም የማህበረሰቡ አንድ አባል ናቸው። ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸው በሰውነታቸው የተሰጣቸው ክብር ነው። በተጨማሪም አይደለም እሳቸው ካቢኔያቸው „ኦሮምያን ለኦሮምያ“ አላለም። ይህ እንዲያዳምጡት በታላቅ ክብር እጋብዘወታለሁ። „ኦሮምያ“ ብለው ሥም ያወጡለት አቶ ለማ መገርሳ፤ ወይንም አቦ ሌንጮ ለታ አይደሉም። ጣሊያን ነው። የጣሊያን ቅዠትን መሬት ላይ የተገበረው ደግሞ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የነተጋሩ ማንፌስቶ ነው። እነ ማህበረ ባንዳ!

http://www.satenaw.com/dr-abiy-ahmed-oromia-speaks-truth/

Dr Abiy Ahmed of Oromia speaks the Truth

ይህ ሁሉንም የቀደመ ጤና አዳማዊ ጭብጥ ነው። ይህ ሙሉዑ የአምክንዮ ባለአቅም ፍለስፍና አይደለም ለኢትዮጵያ እኛ በመንፈሳችን ላገለልናት፤ እሷም አልሻችሁም ብላ ለገፋችን ኤርትራ ሳይቀር ተቆርቋሪ ነው። አይደለም አካላችን ለነበረችው ኤርትራ ለአፍሪካ ቀንድም መንፈሱ ተቆርቋሪ ነው። „እንኳን ደህና መጣችሁ“ የሚል የፍቅራዊነት ተመሳሌት ተፈጥሯዊነት ነው ያለው ካቢኔያቸው።

„ምራቂ“

ኦህዲድ በወያኔ ሃርነት የመንግሥት ፖሊሲ መመራቱ አንደተጠበቀ ሆኖ፤ ግን ብልህነቱን በምን አቅም እንደ ተካኑት ከልብ የእኔ ብሎ ቢከታተሉት ኢትዮጵያ ያለው አዲስ ትውልድ ያለውን ቅምጥ ሃብት ማየት፤ ማስተዋል፤ ተስፋ ማድረግ ይቻላል። በሌላ በኩል እኔ የት ነኝ ብሎ ሊቃናቱን ሁሉ ፈተና የሚያስቀምጥ አምክንዮ ነው።

https://www.youtube.com/watch?v=SMD2pmSYZ2k&t=240s

Social Capital

https://www.youtube.com/watch?v=P9nDRxHtL3s&t=172s

Ethiopia: Exclusive Interview with Dr. Abiy Ahmed on the direction of Ethiopian Politics

« የአካዳሚ ነፃነት » የመንፈስ ተቋማዊ ህልማችሁ እነኝህን ከዬትኛውም ብሄረሰብ ይምጡ፤ ከዬትኛውም አካባቢ ይሁኑ አዲስ ሙህራዊ ኢትዮጵያዊ ቡቃዬዎችን፤ የቅኔ አውድን መጸዬፍ ሳይሆን ማቀፍ አለበት ብዬ በጽኑ አምናለሁ። እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ሙሁር በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ የሚመዘነው በጎሳው፤ በሃይማኖቱ፤ በፆታው፤ በፖለቲካዊ አቋሙ፤ በሃብት አቅሙ፤ በጤናው፤ በቆዳው ቀለም በማግለል ሳይሆን፤ የእኛ ብሎ ከውስጥ መቀበል ሊኖርበት ይገባል በእናንተ ጥንስስ ውስጥ። ጌጥነቱ « የአካዳሚ ነፃነት ለኢትዮጵያውያን » እስከሆነ ድረስ ወጣት ሊቃናት ጌጣችን ሊባሉ ይገባል። እርሾ የለሽ እንዳይሆን ሃሳቡ ከመሰረተ አምክንዮው እንጂ ከጫፍ ወይንም ከውልብልቢት ሊነሳ አይገባውም። ወጣት የኢትዮጵያ ሙሁራን ፍልስፍናቸው፤ የቀደመና የዳበረ ራዕያቸውና መርሃቸው፤ መብለጣቸውም እንዲመራን ልንፈቀድለት ይገባል። ልንጸልይላቸውም ይገባል። ዕውቅናውንም በሙሉ ልባችን ልንፈርመበት ይገባል – ካለ ምንም ቅደመ ሁኔታ።

ለፕ/ ዶር. ዳንኤል ተፈራ ላስታውሰው የምሻው ታላቅ ሀገራዊ መልእክቴ ደግሞ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለጋዜጠኞች፤ ለጸሐፍት፤ በአጠቃላይ ለሥነ – ጹሑፍ፤ ለነፃ የሃሳብ አስተሳሰብ፤ ለሃያስያን፤ ለመናገር ነፃነት፤ ለቀደሙት የሃይማኖት መሪ ጸሎተኞች ሳይቀር ክብር፤ ግርማ፤ ሞገስ ዕወቅና የሰጡ የቀደሙ፤ እጅግም የበለጡ ብልህ ወጣት መሪ ናቸው ዶር አብይ አህመድ ማለት። ማስተዋሉን አብዝቶ የሰጣቸው። በሳቸው ውስጥ ክልል፤ ጎሳ፤ ሃይማኖት፤ የትውልድ ሥፍራ፤ ማንፌስቶ፤ ተወልጅነት ብጣቂ እራፊ ቦታ የላቸውም። ንጹህ ሆነው ነው የተፈጠሩ። በተፈጠሩበት የሰውነት ቅድስና ውስጥ ያሉ ድንቅ የእኛ ብሩኽ ተስፋ ናቸው። እግዚአብሄር እሳቸውን የመሰለ ብልህ ወጣት ሊቅ ስለሰጠነም አመሰግነዋለሁ – ተንበርክኬ።

ስለሆነም ኦህዲድ የመንፈስ ድህነት ካቢኖው የለውም። በመንፈስ ዲታ ናቸው። ዓውዳቸው በመልካም ነገር ጥንስስ ሙሉዑ ነው።አሁን በወጣቶች የሚመራው የኦህዲድ ካቢኔ ከሰብዕዊነት ውጪ የሆነ መንፈስ የለውም። የወያኔ ሃርነት ትግራይ አቅም የለውም ይህን የሚመጥን የመንፈስ ልቅና ለመምራት። ከውስጥ አደርጎ ሲያዳምጡት ብቻ ነው ብልሃቱ የሚገለጠው። ሴራ የበከተበት መንፈስ ሸፈን ተብሎ ቀርቧል ተብሎ አህዱ ቢል እንኳን፤ ድውይ መንሶች ፍንጭ በተገኘ ቁጥር ደንጋጣና ያልተረጋጋ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ እራሱን እዬገለጠ እዬተዝረከረከ ይመጣል። ወያኔ ይህ ስለ አስደነገጠው ብወዛ ሊያደርግ ይችላል። አንዱን አንስቶ አንባሳደር አድርጎ ሊሾም ወይንም ወደ ሌላ ቦታ ሊሸጉጥ ይችላል። ግን ነገር ግን ቅን መንፈሶችን የተቀበለው ሚሊዮን ከዚህ ማዕቀፍ ውስጥ በፍጹም ሊያወጣን አይችልም። በሌላ በኩል ብዙ ሰዎች በዚህ በአዲሱ የኦህዲድ ካቢኔ ባለባቸው ስጋት ምክንያት ይመስለኛል በሌሎች ሁኔታዎች አስገዳጅነት ይህ ወላዊ የሆነ ቀና አመለካከት የመጣ ይመስለዋል። ፈጠራ በራሱ በፈጣሪው ህሊና እንጂ በትውስት አይፈጠረም። በሌላ በኩል እርስዎም እንደ ፖለቲካ ትርፍነት መረማማጃ አድርገው አይተውታል። በፍጹም ሁኔታ አይደለም።

እነዚህ ወጣቶች እኮ ጠጥተው ያደጉትን ገንጣይ/ የጥላቻ ወተትን አጣጥመው፤ ግን መራራ መሆኑን በተጨባጭ ኑረውበት፤ መርምርምረው እግዚአብሄር ከላይ ባቀበላቸው መክሊት እና ቅባዕ አቅም መነሻነት ላይመለሱበት የቆረጡ የዘመናችን አራት ዓይናማ ጀግኖች ናቸው። ለእነኝህ ወጣቶች ቀስቃሽ ፕሮፖጋንዳ አያስፈልጋቸውም። ኑሮውን ኑሮዎታል፤ ህይወቱን አጣጥመወት ግን አሻም ብለው በሚያስደምም ብቃት ውስጣቸውን ከውስጣችን ጋር በኪዳን አዋውለውታል። ቅኖችም ልባቸውን ሸልመዋቸዋል እኔን ጨምሮ።

እንደ አቶ ለማ መገርሳ አይነት ካቢኔ የብቃት አቅማዊ ተወራራሽነት ያለው፤ ጠንቃቃ አቅም እስካሁን እኔ በዬትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ካቢኔ እንዲህ ጎልብቶ አላዬሁም። የነበሩ ቢኖሩም የወያኔ ሃርነት ትግራይ በሴራው መልምሏቸዋል። ይህ ዕጹብ ድንቅ አቅምም ከወያኔ ሃርነት የጫካ ተመክሮ እንደተቸራቸውም ይሰበካል። ኦሮሞ ፈላስፋ መሆን አይችልምን? ደግሞስ በምን አቅሙ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ይህን ጸደይ አምክንዮ የሚያመነጨው? ካለተሰጥዎ? እንዲያው በህልም እንኳን ቢሆን ይህን ልቅና አሳልፎ የሚሰጥ ማን ያበደ አለ። የራሱ ሃብት አድርጎ መወደስ እንጂ። ሊቆች እኮ አለው የወያኔ ሃርነት በውጪም በሀገር ውስጥም ግን ከጫካዊነት መንፈስ ፈቅ የለም። በአራት ማዕዘን በተጠረበ ሳጥን ውስጥ ናቸው።

በሌላ በኩል ግንዛቤው፤ ፍልስፍናው ነጠላ፤ ወይንም ጭፍጫፊ፤ ወይንም የተገለበጠ አይደለም። ኦርጅናል ነው። በፍጹም ሁኔታ ከበሰለ ህሊና የመጣ፤ የፈለቀ መረቅ ፍልስፍና ነው። መሰረት አለው። ይህም በመሆኑ ምንጩ አይደርቅም። ያለው ሰው ችግር የለበትም፤ ሁልጊዜም ለምልም ነው። አሁን ሥርጉተ መጻፍ ጸጋዋ ነው። አትዋሰውም። ደግሞም የሚያልቅ አይደለም። ለምን ሥጦታው የአንድዬ ስለሆነ። ስለሆነም የወጣቶቹ ግንዛቤ ግርድፍ ወይንም ግንጥል አይደለም። የተረጋገ፤ በውስጡ ሰላም የሰከነ፤ ምራቁን የዋጠ ብስል ግኝት ነው። ዕድሉን ካገኙ እነዚህ ወጣቶች ናፍቆታችን ዕውን ይሆናል። የተመጠነ ድንበር የለውም የእነሱ አቅም ጤናአዳማዊ ውስጠት አለው። ይልቅ የእኔ ሥጋት እነኝህን ብርቅ ብልህ ወጣቶች ለራሱ ለትግራይ ዓይኑ ሊሆኑ፤ ጠበቃ ሊሆኑ የሚችሉትን ወጣት የኦህዲድ ብላቴናዎችን በመርዝ፤ በመኪና ግጭት፤ በካቴና እንደ ሌሎቹ ሁሉ በስልጣን የታዋረው ማህበረ ጲላጦስ እንዳይቀድማቸው ነው፤ ልክ እንደ ኢንጂነር ሳይንቲስት ቅጣው እጅጉ። ብቃታቸው ሁለገብ፣ ሁልአቀፍ ሆኖ ተከታታይ የመሆን አቅሙ ደግሞ ከለመድነው የፖለቲካ መስመር ውጪ ነው ልዩ በጣም ልዩ ነው። … ይህ እኔ ስላልኩት ሳይሆን ነገ የሚታይ ይሆናል። ከሰነበቱልን። ደግሞም ሥራዬ ብዬ በመደበኛ እያጠናሁት ነው።

የኦሮምያ ሙሁራኑስ ምን ይለሉ ስለ አብሮነት፤ ስለታሪክ፤ ጊዜዎት በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ከሆነ፤ ይህንንም ቢያደምጡት አይከፋም። ምክንያቱም ተያያዥነቱን ማዬት ያስችለዎታል፤ ቁንጽል አይደለም የለወጥ ስሜቱ። በሌላ በኩል „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ነጠላ ዜማ አለመሆኑን፤ የአቅሙ ጉዝጓዝ በመንፈስ በሚገባ በዕውቀት ላይ የተደራጀ፤ መሬት የረገጠ፤ በፍጹም ሁኔታ የተረጋጋ ስለመሆኑ በጥልቀት ቢመረመሩት ይህን ይመስላል አድህኖ መንፈሱ የሙሁራኖቹ።

https://www.youtube.com/watch?v=xrUhwyeK0J8

የምሁራን ውይይት ስለ አማራ እና ኦሮሞ ህዝቦች ግንኙነት-በአማራ ቴሌቪዥን

ጭካኔ በከፋ ሁኔታ ስለመቀጠሉ …

ጭካኔው በከፋ ሁኔታ ይቀጥላል። ይህ አዲሱ የጵላጦስ የዶር. ደብረጽዮን ገብረሚኬኤል ካቤኔ በፍጹም ሁኔታ የቀረውን ሽረፍራፊ የተቆዬበትን ትዕግስት ሁሉ በማንአለብኝእነትና በትዕቢት እንደሚደፈጠፍጠው ከግምት ካልገባ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ትርጉም ሊገባን አይችልም። በጣም የከፉ ፈተናዎችን መጠበቅ አለብን። መጨረሻ ላይ ነው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማለት ባያስችልም፤ እንደ ድሮው የሚያሰማራቸውን፤ በደላላነት የተሰለፉ የቃላት ክምሮች ለጅምላ እና ለችራቻሮ ቢያቀርብ ረዥም መንገድ ሊያስጉዘው  ከቶውንም አይችልም። ካልስቻለው ደግሞ የሃይል እርምጃው በፈጠነ፤ በተቀናጀ፤ በሚዘገንን ሁኔታ ይቀጥላል። ነገር ግን ሁሉም መንፈስ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ላይ ከከተመ አቅምን በአቅም ማመጣጠን ይቻላል። እያንደንዱ በ ኢትዮጵያዊነት ሱስ ውስጥ ለመኖር ከፈቀደ ወንድሙን ስለምን ይገድላል? እህቱን ስለምን በክፉ ዓይኑ ይመለከታል? ይህ መንፈስ የውስጥን ሰላም በፍጹም ሁኔታ የሚያውጅ ነው። እውነት ለመናገር የተደራጀ የመንፈስ ተቋም አልነበረንም። ሁሉንም የሚያማክል ልቅም ያለ የተስተካከለ የመንፈስ አህታዊ የግንባታ የውሃ ልክ አልነበረንም። አሁን ግን ፈጣሪ በጥበቡ ሠራው። እርስዎ „ጊዜ ላጠፋበት አልፈልግም“ ቢሉም በረቅቅ ሁኔታ በአብዛኛው ልቦና ውስጥ ተገቢ ቦታ ብቻ ሳይሆን፤ ንቁ ትጉሃን ወታደሮችን አፍርቷል። ተከላካዮች አለንለት። ይህ በግብታዊነት ሳይሆን ውስጥን የገዛ፤ ለውስጥ ተደራሽ የሆነ ሙቅ ስሜት ያለው በመሆኑ ስጋታችን ያሸነፈ ንጥር አጽናኝ መንፈስ ነው። ታቦታችን ነው። ከአምላካችን የተላከልን የመዳኛችን አዲስ መጸሐፍ ነው። ሰው የራበውን ሲያገኝ ነገን ያስባል። ያ ራህብ የቦረቦረው አንጀት ከእህል ውሃ ጋር ከተገናኘ ደግሞ አቅም፤ ሃይል፤ ጉልበት ያገኛል። አቅም፤ ሃይል፤ ጉልበት ደግሞ የማሸነፍ ቅድመ ዋዜማ ነው።

ሌላው ያነሱት „የፖለቲካ ንግግር“ ነው ነበር ያሉት።

የእርስዎም አኮ የፖለቲካ ንግግር ነው። „የኢትዮጵያ መንግሥት የአደረጃጃት መርሁ ኢትዮጵያ በቀደመው ተፈጥሮን፤ ተራሮችን፤ ወንዞችን፤ የሥነ – ልቦና ትስስሮችን ያማከለ ደንበር እንጂ ቋንቋን ብቻ መሰረት ያደረገ መሆን አይገባውም“ ባይ ነዎት እኮ። በሌላ በኩል ፖለቲካ ከሰው ተፈጥሮ ውጪ ነውን? ፖለቲካ እኮ የተፈለሰፈው በሰው ህሊና ነው። ቃሉ እራሱ ከሰማዬ-ሰማዬት የወረደ አይደለም። ፖለቲካ የሰውን መንፈስ አደራጅቶ ለጋህዱ አለም ለህልውናው በሚጠቅም መልኩ መንፈስን የሚመራ፤ አካልን የሚያስታዳድር ፍልስፍና ነው። ስለሆነም ፖለቲካ ተፍጥሯዊም፤ ሰዋዊም ነው። እና አቶ ለማ መገርሳ ሰውም ተፈጥሮዊም በመሆናቸው በፖለቲካ ውስጥ ሃሳቡን ማፍለቃቸው ምኑ ነው ክፋቱ? የሰውን መንፈስ ለጋህዱ ዓለም ሊመራ የሚችል የተቃና ፍልስፍና እንደ ውስጣችን፤ እንደ ተፈጥሯችን ቢጠበቡበት ምኑ ይሆን ክፋቱ? ለመሆኑ እርስዎ እንደ አሜሪካ ኗሪነተዎት የአገልግሎት ጊዜያቸውን የፈጸሙት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለምርጫ የተወዳደሩበት „አዎን! እንችላለን“ የፕ/ ትራንፕን „አሜሪካ ትቅደም“ እንዴት ያዩታል? ከእኛ ከወገኖቻችን ሲሆን ነው የሚጎረበጠን? „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ለቅን ኢትዮጵውያን ከዚያ በላይ ነው። ምክንያቱም ከሀገር በላይ ምንም ፍቅር ስሌለ። ይህ መንፈስ እስረኛ ነበር። አሁን ግን ተመስገን ነው። ከእስር ተለቋል። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ፋሽስታዊ ማንፌስቶ ህልምም አይሆኑ ሆኗል።

„በዬሀገሮች የተዛቡ ሂደቶችን ለማስተካከል ጠንካራ ሰዎች ስለመነሳታቸው አምነዋል።“ እንዛም እኮ የፖለቲካ ሰዎች ናቸው። እና ያን ካመኑ ይህን ለመቀበል ምነው ተቸገሩ? አለመቀበል የተከበረ መብተዎት ነው፤ ነገር ግን አድማጭ ይህን መመዘን እንዲገባው ብዬ ነው እኔ ለመጻፍ የተገደድኩት። የእርስዎን ዕሳቤ እንደወረደ ሳይሆን፤ አድማጭ የእኔንም ዕሳቤ ግምት ውስጥ አስገብቶ ውሳኔውን ይሰጣል። የትኛው እንደሚበልጥበት ያውቃል። በአንድ ወንዝ ሂድ መባል የለበትም። አማራጭ ሃሳቦች ሊቀርቡለት፤ ሚዛኑን ሊያስጠብቁ የሚችሉ ሙግቶች መታከል አለባቸው። ከሁሉ በላይ ወዶ ገቡ ለውጪ ሀገር ሰላይነት በሚመስል መልኩ የሚተጉት የተከበሩ ፕ/መስፍን ወ/ማርያም የሚያነኩሩት ድርጅት አይደለም ኦሆዲድ። ይህ ብቻ ይበቃል። „ስለምናስፈልጋችሁ ብቻ ሳይሆን የምታስፈልጉን ስለመሆኑ ስላምንበት ነው“ ነበር አማራን ያሉት። የላችሁም ለምንበላው የሰማይ ታምር ነበር። የእስከ አሁን የሦስት የኢትዮጵያ መንግሥታት የፕ/መስፍን ወ/ማርያም ሴራ ወድቆ ተሰበረ – ተቀበረ – ተላከ ወደ እንጦርጦስ። ከተከበሩ ፕ/ መስፍን መስፍን መንፈስ ጋር ምንም ንክኪ የሌለው የፖለቲካ መንገድ ብቻ ነው የኢትዮጵያ መዳኛ መፍትሄው። እሳቸው የዞሩት አቅም ሁሉ እያደር ሰላላ መላላ ነው የሚሆነው። ተልዕኮ አላቸው …  የዕዳ። አሁንም ውጪ ሐገር የሆኑት የሚመለምሉትን መልምለው ለማርገፍ ያሰቡት ስላላቸው ነው። … ደግሞም ተሳክቶላቸዋልም። አቅምን መበተኑ።

በመጨረሻው ሶስተኛው ክፍል ላይ ያነሱት  አብይ ጉዳይ ነበር „ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን ይዘን ወደፊት መሄድ አንችልም። ማንነት ዜግነትን ይቃወማል። ስለዚህ አንድ የፖለቲካ ሹም ተነስቶ ሱስ ይዞኛል በኢትዮጵያ ስላለ ህዝቡ በሰላም ይኖራል ማለት አይደለም አከፋፈሉ እራሱ ዘጠኝ አገሮች አሉ ኢትዮጵያ ውስጥ“ በመጀመሪያ ነገር የማንነት ጉዳይ በአዋጅ እና በዘመቻ አይገነባም – አይሻርምም። መሬት ላይ በሚሰራ የበቃ የሥነ – ልቦና ተግባር እንጂ። „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ አሸነፊነቱን ግን በእርግጠኝነት ልገልጽለዎት እሻለሁ። እሳቸው ቢተውት እንኳን ሌላው ይከተለዋል። አጸደ ተክሉ አንድ ጊዜ በጸቀ ማዕልት ተተክሏል። ካርታው ላይ የሚታዬው ዘጠኝ ነው፤ ከዛም በላይ ነው መሬት ያለው እውነት። ማንነትም በዜግነት ውስጥ ነው። በዜግንትም ውስጥም ማንነት አለ። ስለማንነት እና ስለዜግነት ብዙም አልሄድበትም። የሆነ ሆኖ መንገዱ ለጠፋው ብትን መንፈስ አንድ አሰባባሳቢ መንፈስ ያስፈልገው ነበር። አምጦ የሚወልድ አቅም! ለአንድ የነጻነት ፈላጊ ማህበረስብ አታጋይ መርህ ያሻው ነበር። ያን ደግሞ አግኝተነዋል። „ዴሞክራሲ“ ከቃልነት ውጪ የሚታይ ተጨባጭ ነገር በታሪካችን አላዬነም። „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ነው ግን ዓራት ዓይናማው መንገዳችን ነው። ከውስጥ ፍላጎታችን እና ከስሜታችን የተነሳ ነው። ኢትዮጵያዊነት መኖሩ ነው እኮ እኛ ተሰደንም መሬት ያለን፤ ሐገር ያለን ህዝቦች መሆናችን ዕውቅና ያለው። ስለዚህ በዚህ ውስጥ መኖር ላለተፈቀደለት ዜጋ አሁን ይህ ጸሐይ ሲወጣ ክስተት ነው ለእኔ።  ሌላው ያነሱት „ወደ ታሪካችን፤ ወደ ባህላችን መመለስ ይኖርብናል“ በማለት መጨረሻ በክፍል ሦስት ያቀረቡትን ሐሳብ፤ ክቡርነተዎት ስለገፉት ነው እንጂ የአቶ ለማ መገርሳን ንግግር ቢያዳምጡት ወደ ታሪካችን ወደ ባህላችን እንመለስ በማለት አበክረው ስለገለጹት አብይ ጉዳይ ስለመሆኑም፤ የመንፈሱን ህዋስ ማግኘትም መመርምርም ይችሉ ነበር ከሚገፉት። እኛ የምንወደዎት ብቻ ሳይሆን የምናከብረዎትም ሊቀ-ሊቃውንት ነዎት።

https://www.youtube.com/watch?v=aim-D4EKMlI

Amhara and Oromo on Lemma Megersa’s speech

የአቶ ያሬድ ጥበቡን ዕያት በጥቂቱ።

አንደምን ሰነበቱ ጸሐፊና ፖለቲካዊ ተንታኝ፤ ሃያሲም አቶ ያሬድ ጥበቡ። ደህና ሰነበቱ? ከአሜሪካው ድምጽ የአማርኛ ፕሮግራም ጋር ያደረጉት ውይይት አውራንባ ታይመስ እዬመሰለኝ ነበር ያዳመጥኩት። መቼ ይሆን የጫካው 80 የሚቀደደውም ብያለሁ። „መገምድ“ የሚሉት ነገር  በአንድ አነሳ የጎሳ የበላይነት ያለውን „መገምድ“ እንዴት ሊያዩት እንደሚችሉ ውስጡ ለቄስ ነው። እነሱስ እነ ማህበረ – ጲላጦስ በዚህ በ“መገመድ“ ውስጥ የሌሉ ሆነው ነውን የዘር ማጥፋት ዘመቻው አና ብለው ያያዙትን? ወይንስ ለማፈናቀሉ እረፍት ሰጥተውት? ወይስ የትውልድ ምክንቱን ዶሴ ለይደር ቀጥረውት? ወይንስ ወረራው ከቶ የእርስዎን „የመገመድ“ ባዶ ቲወሪ በወያኔ ሃርነት ትግራይ እርቃኑን የቀረ የምላስ ሞረድ ሳይተላለፍ ቀርቶ?

ሌላው „ግጭት አያሰጋኝም“ ነው የሚሉት – እግዚአብሄር ይቅር ይበለዎት። ደግሞም ታድለዋል፤ እንቅልፍ ተኝተው ያድራሉ። እኔ ደግሞ ምጥ ላይ ነኝ። ሦስት ሰዓት ብቻ ነው የምተኛው። አይደለም ዛሬ ነገረ – ማግሥት የወዮ ቀን ናት። ቀኗን አዝለን፤ ቀኗ የምትልክልነን የማስጠንቀቂያ ትልቅ ባለድርብ ደወል መንፈስን አላዬሁም አለስማሁም እስካልነው ድረስ ነገ የራሷ ቀን አለመሆኗ ብቻ ሳይሆን፤ የነገ ተ-ነገወዲያ የሆድ ዕቃ ብጭቅጭቅ አድርጋ ትጥለዋለች – ባለአውሊያዋ ብስጭት። አያድርገው እና በወያኔ ትግራይ አገዛዝ አሁን የኢትዮጵያ ሉዕላዊነት የሚፈታተን የውጪ ሃይል ቢነሳ በእጅ እፍኝ የሚሞላ የተሰባሰበ የመንፈስ ሃብት አለን? እንደ ባድመው አሁን ተነስ! ታጠቅ! ቢባል ማነው የሚነሳው? ወይስ አማራን ለመጨፍጨፍ የሚያሰማራቸው የተጋሩ ሠራዊት ብቻ ተዋግተው ሀገርን ከጥቃት ሊታደጉት ይችላሉን? የአልበሽር ካቢኔ ሰሞኑን ከራሽያ ጋር መክሯል። ገርድፈን ነው ያለፍነው ወይንስ ሰልቀን? ኢትዮጵያ እኮ በሃሳብ ብቻ ነው ያለችው። ውስጧ የለም። በአንድም በሌላም ብኩን ሆኗል መንፈሷ። ነገን ለማቆዬት ቀኗ ሳታልፍ የሚወስነው የመፍትሄ አሰጣጥ አቅማችን ልባዊነት እና ቅንነት ስንመግበው ብቻ ነው። በዚህ ላይ በቀጥታ ከፕ/ዳንኤል ተፈራ ጋር እስማማለሁ።

ሲበዛ እኮ ማርም ይጎመዝዛል። ሰውነትን የሚፈታተኑ፤ ሰብእናን የሚያፋጥጡ ጥጋቦች፤ ፋታ የለሽ ጭካኔዎች፤ ያላባሩ ጭራቃዊ አስተዳደሮች ያንገፈገፈው ምልዕት ቁጣውን የሚገለጽበትን መንገድ ልንቀምረው፤ ልናቅደው፤ ወይንም እንደ ሂሳብ ፎርሙላ ልናወጣለት አንችልም። የትግል ስልቱን ጠፍጥፈን፤ አንቦልቡለን በዚህ መስመር ሂድ ልንለው በፍጹም ሁኔታ አንችልም። አመጻዊ ተነሳሽነቱን በምን ሳቢያ ሊሆን እንደሚችልም መገመት እንኳን አንችልም። ቀኑንም አናውቀውም። የሚፈጠርበትን ሁኔታም ቀድምን መተንበይ አንችልም። የስኳር አብዮት ሊሆን ይችላል … ወይንም የጉርሻ አብዮት … ወይንም የሰንበሌጥ አብዮት … የተቆጣ ህዝብ ህግ አይገዛውም። ብስጩን መንፈስ ሽበት አይመራውም። የሸፈተን ልቦናዊነት ሽምግልና አያሰተዳድረውም። በፍጹም ሁኔታ ከቁጥጥር ውጪ ነው። አሁን ጸጥ ለጥ አድርጎ የሚገዛው ህገ – ጲላጦስ በዛች ሰዓት ለራሱ መደበቂያ ትንሽዬ ቁጥቋጦ ፈላጊ ነው። ይህን አዳጋ በቅብ ምስለ ጥገና ለውጥ ይተጋሳል ብሎ ማሰብ ጨረቃ ጸሐይን ተክታ የቀን ብርሃን ትሆናለች ማለት ነው። የችግሩ ምንጭ ፍልስፍናውን መሠረት ያደረገው የወያኔ ሃርነት ማንፌስቶ ነው። የትግራይ የበላይነት እና ጠቅላይነት ነው። ይህን ማንፌስቶ መሠረት አድርገው የተረቀቁ ህጎች ሁሉ በጥገና ሳይሆን በሥር ነቀል ለውጥ መፍትሄ ካለገኙ ፍንዳታው አይቀሬ ነው። ለዛ ግን መሸጋገሪያውን እናክብር ቢባል ያስኬዳል። ድልድያችን ደግሞ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ቢሆን የመፍትሄ ትኬታችን ነው። አቻም የለውም „ለኢትዮጵዊነት ሱስ ነው።“ ይህ ፍልስፍና ሰብዕዊም ነው። ከአፍቅሮተ ማንፌስቶም በላይ ነው። ከሶሻሊስቱ አይዶሎጂም በላይ ነው። ከጎሰኝነትም በላይ ነው። ከልላዊነትም በላይ ነው። ሱስ ለሆነህ ነገር አይዶሎጂ ገዢው ቀርቶ ጎረቤቱም ሊሆን አይችልም። በፍጹም። „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነውን“ እርስዎም ተቀብለውታል ግን በዛ ዝልብ የኢሕአዴግ ጃኬት ውስጥ እንደ ለመደው ይማቅቅ፤ ይዛግጥ፤ ይንቦጫረቅ፤ ሃብትነቱ ለታላቋ ትግራይ ቀጣይነት መዋለ ጊዜ ይስገድ፤ ይባክንም ነው የሚሉት። እኔ ደግሞ ጋዜጠኛ ኤርምያስ ለገሰ ባለው መንገድ ከበከተው ማህበረ ጫካዊ ተመክሮ መውጣት ነው የሚያስፈልገው ኦህዲድ ባይ ነኝ። በሁሉም አቅሙ መጣኝ እና ፍለስፍናው ህሊናን የማስተዳደር አቅሙ አንቱ ነው ባይ ነኝ። የእርስዎ አምልኮተ ዝንጥል የኢህአፓ አውሊያ ባለቁራኛ የሆነው የባህርዳሩም እንኮሸሽሌም ጭምር በዚህ መንፈስ ክተት ቢል ለራሱም ይጠቅመዋል ያን የጫካ የበከተ የጭካኔ ጭንቅላት ማንፌስቶ የሙጥኝ ከሚል። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ጊዜያዊ የማጥቂያ ከተማ ሲያገኝ በወገራ በዳባት ዙሪያ፤ በስሜን ደባራቅ ዙሪያ፤ በወቅን ከተማ « ማሌሊት ያሸንፋል » ብሎ በዓይነ ምድሩ ግድግዳውን፤ ወንበሩን ሰሌዳውን ሁሉ ለቅልቆ ይለቅ ነበር። ት/ቤቶችን በሙሉ አቃጥሎ ክሊኒኮችንም አቃጥሎ፤ ድልድዮችን አፍርሶ። ይህን በስማ በለው ሳይሆን እኔ በዓይኔ ያዬሁት ነው። ዛሬ « ስለልማታችን፤ ህዳሴ ግድብ » ሲል ይደንቀኛል። ይገርመኛል 26 ዓመት ሙሉ ይህ ላንቁሶ ደመነፍስ መምራቱ … ብልህ ሰው ጠፍቶ፤ ኢትዮጵያ የወላድ መካን ሆና።

„እስክንድር „ምናመን?“ እ …

ዕድሜ ጠገቡ ፖለቲካኛው አቶ ያሬድ ጥበቡ ድምጸዎት የእርስዎ መሆኑን እስክጠራጠር ድረስ ነበር ይህን ማህጸን የሚቀድ መመጻደቅ የሰማሁት። ጆሮዬ ይሆን ብዬ እዬመላለስኩ 5 ጊዜ አዳመጥኩት። ወይ አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ያሬድ ጥበቡ በቃ ለእኔ እና ለእርስዎ ነጻነት ተማጋጁ አባ ትርጉም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፤ አባቱ „ምናንምን“ የሚል ሆነን መድፊያው? እንዴት ያማል። እንዴት ያቆስላል? ይገርምል። ይደንቃል። ምን አለ ለህጻን ናፍቆት እስክንድር መንፈስ ቢጠነቀቁ። ነገ እኮ ኢትዮጵያ የእነ ናፍቆት እስክንድር ናት። ትውልድ እንዲህ ነው በጥንቃቄ እና በስልት የሚያዘው አሉዎት? እርስዎስ ለመሆኑ ከነማህበረ ጲላጦስ በምን ይሆን የሚለዩት? የተጎሳቆለ መከረኛ ትውልድ የሥነ – ልቦናውን ጥቃት እንዲህ ነው የምናክመው? ይህ ነው አጽናኝ መንፈስነት?  በዓለም በዘርፈ ብዙ ጽናት እና ትእግስት ዕውቅና ያገኘውን ጋዜጠኛ አንድ ዕውቅ የፖለቲካ ሰው የነጻነት አርበኛውን ጋዜጠኛ እስክንድን ነጋን የአባቱን ሥም ጠፍቶባቸው „እስክንድር ምናምን“ አሉት ብለን ለሰብዕዊ መብት ግሎባል ተሟጋቾች ብንነግራቸው ምን ሊሉ እንደሚችሉ አላወቅም። ፈተና ነበር። እና ፈተናውን ወደቁ – ዘጭጭጭ። ግን የት ነው ያሉት? ከማን ጋር ነው መንፈሰዎት የከተመው – ከአውራንባ ታይመስ? ግራ ገብቶኛል። አባ ትርጉም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የመጀመሪያው ጋዜጠኛ ነው። በታሪክ ምቾትን አክን እንትፍ ብሎ፤ ስደትን ተጸይፎ ወደ ትውልድ ሐገሩ ሄዶ መከራን፤ ሰንቆ ሰቆቃውን በፈቃዱ የተቀበለ የቁም ሰማዕት ነው። የመጀመሪያው ጋዜጠኛም ነው ከትዳር አጋሩ ከዛች የልብዬ ጋዜጠኛ ሰርካለም አዲስ ጋር እስር ቤት የነበረው። የመጀመሪያ ጋዜጠኛም ነው የበኽር ልጁን ጽንስ እስር ቤት ኑሮውን አባትና ልጅ፤ የትዳር አጋርም በቤተስብ ደረጃ የተጋሩበት፤ ይህ በታሪክ ሆኖ አያውቅም። ሌላ ሐገርም አንብቤ አላውቅም።  „የቤተሰብ ጨዋታ“ እያለ ደግሞ የማህበረ – ጲላጦስ ሚዲያ ይቀልዳል። „የቤተሰብ እስር ቤት ቀራንዮ“ ቢል አንዴት ባማረበት። በዚህ ጲላጦሳዊ ሂደት ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሐገር ናት። ጽንሱ እስሩን መጋራቱም ብቻ ሳይሆን ከተወለደ በኋዋላ ከወላጅ እናቱ ከጋዜጠኛ አራስ ሰርካለም አዲስ ርጥቡ ደም ተለይቶ ፍዳን የከፈለ። ርጥቡ ደም እናቱንም አባቱንም በእስር ቤት በቅዱስ መንፈሱ ያሰበ ህፃኑ ጭርቆስ ነው፤ የጸለዬላቸውም ለግፉዕን ወላጆቹ በርጥብነቱ ነው። የአራስ ወጉ ያልደረሳት እናቱን ህፃኑ ጭርቆስ በተለዬ ሁኔታ ሱባኤ ይዞላታል። የዛ ለጋ ደም ሥነ – ልቦናው በጨካኞች እስር ቤት አልበቃ ብሎ ዛሬም ስደት ላይ የሚገኘው የናፍቆት እስክንድር አባት አባ ትርጉም እስክንድር ነጋ ይባላል። „እስክንድር ምናምን?“ እግዚኦ! እግዚኦ! እግዚኦ! ሰውነት እንዲህ ነውን? ማቀለል ከፈለጉ በወል „ጋዜጠኞች“ በማለት መግለጽ ይችሉ ነበር። ግን በቀለዎትን ማስተላለፍ ይፈልጉ ነበር። ጉሽ¡ ይህ ፖለቲከኛ ለሚባለው ህጻናት ኢትዮጵያዊ አይደሉምን ብለው ይሆን የሚያምኑት? የመጀመሪያው መሪ ናቸው አቶ ለማ መገርሳ ስለህጻነት ህይወት ተቆርቋሪነትን ሲያሳዩ „ሁሉን ነገር በትምህርት ቤት መስጠት አንችልም፤ ቤተሰብ ላይ ስለ ሀገራችን፤ ስለ ሥነ-ምግባር ማስተማር አለበን“ ሲሉ። እኔ እንዲያውም በ2016 ለመሆኑ ማንፌስቷችሁ ስለህጻናት የሚለው ነገር አለውን ብዬ ነበር። ኢትዮጵያዊ ማንደሌ ዶር. መራራ ጉዲና ወደ ሞት የገሰገሱ በሚለው ጹሑፌ ላይ። ታዛቤ … ታዝቤ። ሐገር የተወረረ እስኪመስል ድረስ ያን ያህል የጦር መኪና ለካቴናዊ ህይወት አቀባባል ሲያደርግላቸው ልጆች በመንፈሳቸው እንዴት ሊሰቃዩ እንደሚችሉ ውስጤን ስለ አቆሰለው። … ህጻናትን መንፈሳቸውን ቅርጥም አድርጎ የበላውን ጭካኔ ቢያንስ ለእንሱ እንኳን ትንሽ ብጣቂ ሰው … ሰው የሚሸት ጠረን እንዴት ይድረቅበዎታል? ቢያንስ እንደ ዶልፊን … ወይንም እንደ ታማኝ ፈረስ፤ አዝናለሁ።

እስረኛን አስረኛ ሊያስፈተው ይችላልን?

ይህንንም መጠዬቅ የምሻው እርስዎን። አቶ ያሬድ ጥበቡ አንጋፋው ፖለቲከኛ፤ ሃያሲ በዝቀሽ ተመክሮ የተካኑት የእርስዎን ጉዳይ በአንድ ነገር ልከውነው „እስረኛን አስረኛ“ ሊያስፈታው ይችላልን? ፕሬዚዳንት ዶር ሙላቱ ተሾመ ነጻ ፕሬዚዳንት ናቸውን? እንኳን እሳቸው ጠ/ሚር ሃይለማርያም ደሳለኝ ነፃ ናቸውን? ኢትዮጵያ እራሷ አልታሰረችንም? ወንዙ – ተራራው – ሸለቆው – ምድሪቱ ከእስር ነፃ ናቸውን? ፕሬዚዳንቱ አቅም ቢኖራቸው እስረኛዋን ኢትዮጵያ ባስፈቱ – በእሷ ሥም አይደል ፕሬዚዳንት የሆኑት። አሁን እራሱ እንደ ቅርበተዎት የወያኔ ሃርነት ትግራይ የመከረውን አያውቁም ሆነውን? ትምክህተዎት በዚህ የሰው ደም በዛለበው ጃኬት „የኢሕአዴግ“  ቀጣይነት እራሱ የሚገርም ነው። አሁን „የኢሕአዴግ“ ዕውን ነፃ ስብስብ ነውን? ወይንስ የፓኬት መጠቅለያ ወረቀት? ስለማን ነው አሁን እዬተከራከሩ ያሉት? ስለማንስ ነው እርስዎ ጥብቅና የሚቆሙት? የትኛውን መንፈስ ነው ለመበተን የነተነሱት ? ስለ ወጣት ገዳዩ ስለጲላጦሱ የዶር. ደብረጽዮን ገብረሚኬኤል ካቢኔ? መጋቢት ላይ ሊያዩት ይችላሉ?

መንፈስዎት ግን በእውነት ያሳዝነኛል ሁልጊዜ ከእነሱ እግር ሊጠፉ አለመቻለዎት፤ የህሊናወት መቅኖ ጥገኛ መሆኑ፤ በራስዎት ውስጥ ጸንተው መቆም አለመቻለዎት፤ ለነገሩ ለአማራ እኮ የሰጡን መሪ አቶ አዲሱ ለገሰን ነው አይደል? የጥገና ለውጥ ራህብተኛው የአቶ ያሬድ ጥበቡ ከተጠማኝ መንፈስ ጋር መቼ ይሆን የሚፋታው? እንቆቅልሹ ይሄ ነው። ከፈርዖናዊ ማንፌስቶ ደጅ ጥናቱስ መቼ ይሆን በቃኝን የሚያጣጥመው? እንዴት ነው ነገሩ የስሜት ቢዝነስ ተከፈተን ወይንስ እንደ እርጥብ ጨርቅ እዳሪ ተሰጣ በሽቦ ገመድ። አይመጣም ያ ተፈጥሮን የሚፈታታነው የሴት እህተዎት ጥፍር ሲነቀል፤ የሰቀቀኗ የምሬት ጩኽት፤ ወንድመዎት እኮ ዛሬ እኔ ወንድ ነኝ እንደ እርስዎ ለማለት የሥነ – ልቦናው አቅም ይኖረዋልን? ስቅስቅ ብሎ ያለቀሰበት ህማማት ዕውን እረፍት ይሰጣልን? የአቶ ያሬድ ጥበቡ ሰውነት ለመሆኑ አድርሻህ ከቶ የት ይሆን? አይዋ ሽበትስ? አቶ ልምድስ?

ያ የእርስዎ የትምክህት ቀፎ የኢሕአዴግ በለተለይም በምከክር ከኢህአፓ ዝንጥል ፍላጎት ወደ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከነቀፎው ሽግግር ያደረገው ምሰለ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ጭንብል ቁመናው እና ሆድ ዕቃው ምን እንደሚመስል ቋቅ ሊለዎት ቢችልም አሁን ብርድ ነው እና የአውራንባ ታይመስን ካሊመዎትን ከነብነብ ብለው ያዳምጡት ዘንድ በትሁት መንፈስ እንሆ … „https://www.youtube.com/watch?v=oC49pPlr-Ok የአማራ ክልል ጋዜጦኞች ጥያቄ እና የብአዴን መልስ“

ሌላው በስተመጨረሻ በቃለ ምልልስ ቆይታ የማነሳው ጉዳይ አቶ ያሬድ ጥበቡ ከሚያቀነቅኑት የጥገና ለውጥ፤ ወያኔ ሃርነት ትግራይን ሥርዎ መንግሥት የጣሊያን ማንፌስቶ ተማህጽኖ ይልቅ፤ በዛ ሰሞን ጋዜጠኛና ፖለቲካ ተንታኙ አቶ ኤርምያስ ለገሰ ያካፈለን አንድ ብልህ እሳቤ/ ግኝት ነበር። „ነፍስ ያለው ኦህዲድ ከጃኬቱ የኢሕአዴግ ካቴና ተላቆ ነጻነቱን ቢያውጅ፤ ነፍሱ ባትኖርም በደመንፈስ የሚራመደው የኢህአፓ ዝንጣፊ የባህርዳሩ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የልብ ማህተም የኦህዲድን እርምጃ በተግባር መሰረት ቢያስዝ።“ እኔ ደግሞ የማክለው በእሱ ሃሳብ ላይ ያው ቀጣዩ ጠ/ሚር ቦታውን በጲላጦሱ በዶር ደብረ ጽዮን ገብረሚኬል እስከሚወራረድ ድርስ ቁሞ ጌታው በረድ በለኝ ከሚልም፤ የደቡብ ህዝቦች ብሄርና ብሄረሰቦች ድርጅት እንደተኛ ወጀቡ ሽምጥ ሳይጋልብበት፤ የሲዳሞን ቡና ለሊቃናቱን ቢግት እና በዚህ መንፈስ ውስጥ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ መንፈስ ውስጠት አብሮ ቤተኛ ቢሆን የወያኔ ሃርነት ትግርይ ማንፌስቶ ግብዕቱ ይፈጸማል። ትግራይም ታርፋለች። ከጥርስም ትወጣለች። የትግራይ ህጻናትም በመንፈሳቸው መንፈስ ቅዱስ በሚያቀብላቸው የእውነት መልዕክት ከመባነን ይድናሉ። ኢትዮጵያም ወህ ትላለች። አሁን ያለው የተጋድሎ ጉልህ መስክ የትግራዊነት ዜግነት እና የኢትዮጵያዊ ዜግነት ነው። ትግራይም ቁንጣኑ አላስችላት ብሎ ከምትጨናነቅ፤ ካለልክ ተንጠራርታ ከምትፈነዳ እንደ አቅሟ፤ እንደ ቁመናዋ በልኳ በተሰፋ ልብስ፤ ኢትዮጵያም ደግሞ አንደ ሐገርነቷ ሙሉ ወርዱን ቀሚሷን ዘው አድርጋ እቅፍ ታደርገናለች … ብስል ከቀሊል፤ ደቂቅ – ሊቅ ሳትል … እንደ ዘመነኛው የእውቅና ማህተም የተማራ – ያልተማረ ሳትል፤ የማንፌስቶ ማህበርተኛ እና አልቦሽ ሳትል …

ንጽጽር።

መቼም መከረኛ ጎንደር ያልተሸከመው ፖለቲከኛ አልነበረም። ከነዚህም ውስጥ አንዱ ነበሩ አቶ ያሬድ ጥበቡ። ምሽጋቸው፤ ስንቃቸው፤ ክንዳቸው … ቋንቋቸውን፤ ብሄረሰባቸውን፤ የፖለቲካ አቋማቸውን፤ ሃይማኖታቸውን ሳይጠይቅ እቅፍ ድግፍ አድርጎ ለዚህ አብቅቷቸዋል – ጎንደር። ታዋቂ ፖለቲከኛ ሆነው በየመድረኩ ሲጽፉ፤ ሲጠዬቁ አዳምጣለሁ፤ አነበላሁም። አማራጭ ሃሳቦችን ማድመጥ ስለምወድ። ያ ገድለኛ የጎንደር አብዮት በሳቸው ልቦና ቤት አልነበረውም። ተጋድሎው ብሄራዊ ነበር። በውጭም ሆነ በሀገር ውሰጥም እንዲህ ሁሉንም ችግር ውስጡ ያደረገ የሠለጠነ፤ በፍጹም ሁኔታ በህሊና በብቃት የተደራጀ መንፈስን ይዞ የተካሄደ ህዝባዊ እንቅስቃሴ አልነበረም። እና ሲጀምሩ አጠንከረው እና አብክረው የገለጹት የኦሮሞ ንቅናቄን ብቻ ነበር። ግንጥል ጌጥ ወይንም ግማሽ ራስ ሹሩባ። አዎን እነሱማ የሚታይ ሰው አላቸው። የሚፈራ ሰው አላቸው። የሆነ ሆኖ በአቶ አስራት አብርሃ የዛ ሰሞን ወግ የጎንደሩን የአማራ ማንነት የተጋድሎ አብዮት ምንጭ የወልቃይትና የጠገዴ ጉዳይ የገብያ ግርግር አድርገው መውስድ ብቻ ሳይሆን፤ ሀገራዊ ፋይዳውን አጣብቀው፤ አኮስምነው ነበር እንኩትኩቱን ያወጡት። የተጋሩ ወራሪነቱ ስለሚነካባቸው። በመቀጠልም እዛው የሚያልቅ ለዛውም ነገ ሲሉ ነበር የተሳለቁበት፤ እጅግ በሚደንቅ በሚገርም ሁኔታ ነው የወልቃይትና የጠገዴ ጉዳይን ሲዳሞ ተወልደው ያደጉት ፕ/ ዶር. ዳንኤል ተፈራ መንፈሳቸው ማድረጋቸው ብቻ ሳይሆን የመፍትሄ ምንጭ አፍላቂውን አምክንዮ ዕውቅና የሰጡት፤ ስለሆነም በዚህ ሊቀ ልቅና የአቶ እስራትን ስላቅ ብቻ ሳይሆን የሁሉንም የትግራይ ሊቃናት አከርካሪ የሰበረ የፋክት ሰቅ ነበር – ተደሞው። ከማዕከላዊ የችግሩ አስኳል ነበር የተነሱት ፕሮፌሰር ዶር. ዳንኤል ተፈራ። ስለዚህም ለመፍትሄ አምንጭነት ቅርብ ሆነው አግኘቻቸዋለሁ። ከእኔ ጋር ያልተስማማንበት ወደ መፍትሄው የሚያድረሰን፤ መፍትሄውንም የሚያዘልቅልን የጉዞ ትኬት መቁረጥ ይቀድማል ነው እኔ የምለው። „ኢትዮጵያዊነት ሱስ“ ነው ለእኔ ዘላቂ ድልድይ፤ ቋሚ መሸጋጋሪያ ብቻ ሳይሆን ማማ ነው ባይም ነኝ። ያ የጉዞ ትኬት ነው የነገን የኢትዮጵያዊነትን ልዑዕላዊነት ሊያስጠብቅ የሚችል ከሚለው ላይ ብቻ ይሆናል። ይህን „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ የትኛውም ሶሻሊዝም ርዕዮት መርሁ የሆነው ድርጅት ሁሉ ደፍሮ ቃሉን ለማውጣት ቃር ይይዘዋል። አንጋፋው ኢህአፓ ሳይቀር። „የብሄረሰቦች መብት እስከ መገንጠል“ አይደል የሚለው። ይህም ብቻ አይደለም እራሴ በተገኘሁበት ስበሰባ የዛን ጊዜ ጸሐፊው አቶ እያሱ አለማዬሁ „በባድመ“ ጉዳይ ላይ እንደ ሱማሌ የኢትዮጵያ ወረራ ተመሰሳይ መልእክት፤ ተመሳሳይ ፕሮፖጋንዳ ነበር መግለጫ የሰጡት፤ መነጠራቸውን ከራሳቸው ላይ አድርገው። እኔ እራሴ ያን ጊዜ የሚከፈለኝ የራዲዮ ጋዜጠኛ ስለነበርኩ „ታሪክ እራሱን ደገመ“ ብዬ ነበር ዘገባውን የሰራሁት። የሆነ ሆኖ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ በቅኖች ልቦና የተከተበ አዲስ ግኝተ ነው። ስለሆነም ዘብ አቆምለታለሁ። እነ አቶ አስራት አብርሃ፤ እነ አቶ ገብሩ አስራት፤ ተቀቡልት – አልተቀበሉት። አሁንም ቃለ ምልልሳቸው ሆነ የሚያንዣብበት የላቀውን መንፈስ አፈር ድሜ ለማስጋጥ ነው። ግን አይችሉም። በበሰበሰ ፍላጎት ውስጥ ቀን መግፋት እንጂ መዝለቅ አይቻልም።

የኢሳቱ እፍታ እና የኦህዲድ የምልከታ ሚዛን።

„የኦህዲድ ካቢኔ መግለጫ እንዲያወጡ ቢገደዱስ“ ስለሚለው ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እንዳለው ሊደንቀን አይገባም ነው እኔም የምለው። እንዲያውም እሱ ያለውን እንደ መርህ ብንቀበለው መልካም ነው። „አናስደንግጣቸው!!!“ ዋው! ከልቅና በላይ የሆነ፤ ምራቁን የዋጠ የማስተዋል ቆመስነት። ተባረክ!

በነፃነት ትግሉ ውስጥ በብዛት ያሉት ወጣቶች በመሆናቸው „ኢትዮጵያዊነት ሱስ“ ነው በሚመለከት ኢሳት የሰጠው ሽፋን ላይመቻቸው ይችላል። ወጣቶች ተሎ ማዬት የሚሹት ጭብጥ ስለሚሹ። ነገር ግን ይህ ብሂል አቶ ለማ መገርሳ ቢተውት ወይንም ቢሸሹት ሌላው የእኔ ብሎ ማስቀጠል አለበት። የጎሳ፤ የዕምነት፤ የጾታ፤ የእድሜ ፤ የእወቅት፤ የኑሮ ደረጃን ልዩነትን፤ ግላዊነትን ስለተጸዬፈ። እኛ የመንፈስ መሰባሰቢያ አቅም ያለው አምክንዮ ድህንት የነበርብን፤ ግን ነጻነት የናፈቀን ነበርን። አብዛኛውን መንፈስ ሊያሰባስብ የሚችል መንፈሳዊ ሃይል እስከሌለ ድረስ ምንም ያህል የፖሊሲ ጥራት ቢኖረንም እንኳን፤ የለንም እንጂ አንድ እርምጃ ወደፊት መራመድ አላስቻለንም። አዲስ ሃሳብም „ለዴሞክራሲ“ ከሚለው ውጪ። አንድ የነጻነት ትግል ቀልብን የሚገዛ፤ አብዛኛውን ስሜት የሚያስተዳድር የትግል አሰባባሰቢ መሪ መርኽ ሊኖረው ይገባል። ለዚህም „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ክስተት ነው እኔ የምለው። አዲስ – ገጽ፤ አዲስ ምዕራፍ ነው። አዲስ ዘመን ነው። ነገ ነው። ትውልድ ነው።

የቅድመ ሁኔታ ገመድ እና የጋዜጠኛ ኤርምያስ ለገሰ ነገር። ግን ለምን እናትዬ?

እናትዬ ምን ሆነህ ነው አሁን ከሆነ ቅድመ ሁኔታ እምታበዛው? የጤና ነውን? በውነቱ አልገባኝም። ስንቱ ነገርስ? የትኛውንስ ቁም ነገር ነው ቅደመ ሁኔታ የሚያስፈልገው? ዕለታዊ ማህበራዊ ኑሯችን? ባህላዊ ትስስራችን? የጋብቻ ህይወታችን? ለምሳሌ የፈርኦኒት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር እና የአቦ አባ ዱላ ገመዳ ልጅ ቢፋቀሩ ላይጋቡ ነውን? አቤት የፈተናችን ብዛቱ? እርግጥ ነው በማንኛውም የግንኙነት መሥመራችን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ህዋሶች አሉ ከነመርዛቸው? ግን ፈርተን፤ ሸሽተን ሳይሆን በአቅም ልቅና በልጠን፤ በመቻቻል አቅል ጎልተን መሆን አለበት ብዬ አምናለሁ።

„አቦ አባ አዱላ ገመዳ ከአቶ ጌታቸው እረዳ ጋር ቢቀመጡ“ ስለም ብለን ልንጠይቅ አይገባንም? ወይንም „ከፈርኦኒት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር ጋር አቶ ለማ መገረሳ ጎን ለጎን ቢቀመጡ“ እንዴት ተደርጎ ልንል አይገባም? በሃሳብ መግባባት ሌላ ነገር ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይ የመርህ የፖለቲካ ድርጀት ስላልሆነ የሚታሰብ አይደለም። ኢትዮጵያን ወያኔ እንዴት ነው የሚያያት? እንደ ባላንጣ እንደ ተፎካካሪ። በዚህ መንፈስ ውስጥ ያሉትን አሉታዊ መስመሮች ሁሉ በአንድ ጋላሪ ውስጥ ማስቀመጥ ይገባል። በወያኔ ሥር ሆኖ አብሮ መቀመጥ ግድ ነው። ጥሩ ሥርዓት ቢኖረን ምግባራችን መላቅ አለበት ከገዳዮች። እናትዬ አንተስ እንደ ፈረደብህ ከፈርኦኒት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር ጋር አብረህ ሠርተህ የለም፤ ያውም የበታች ሰራተኛ ሆነህ? የጎንደር ሰው እኮ ወንድምዓለም ወዶ፣ ፈቅዶ፣ ደስ ብሎት ነው ከባለ 6 በላይ ሪጅኖች ካለቸው ዘመነኛ ትግራይ ጋር ከሥሯ በታች የወደቀችው ህመምተኛዋ ጎንደር ላይ ገዳዮቿን እኮ አስተናግዳለች። የኢትዮጵዊነት ትርክትም አዳምጣለች እኮ በተደሞ ሆና። ይህ እኮ የግድ ሊሆን የሚችል ጉዳይ ነው። ወያኔ እኮ ሥራዓት ነው። ወያኔ እኮ „መንግሥት“ ነው፤ ሁሉ ያለው፤ በግልም የክትና የዘወትር አውሮፕላን የሚገዙ አባላት ያሉት። አውሮፕላን የሚሸልሙ ተጋሩ ያሉት – የዲታዎች ማህበር። ስለሆነም እነዚህ የኦህዲድ ሰዎች በተለያዬ ሁኔታ በነበራቸው ግንኙነቶች ላይ ተመስርቶ የምናያቸው፤ የምናዳምጣቸው ነገሮች ቢኖሩ፤ ሃራም! አላይህ! አልስማህ! የአቋም ለውጥ አደረጉ ብለን ልንከሳቸው፤ ልንወቅሳቸው፤ ቅናዊ መንፈሳቸውን ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ ልንከተው አይገባም። በዘመናት የተገነባ ልዩነትን እኮ ነው „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ሁሉንም ካቴና በጣጥሶ ሞትን ፈቅዶ፤ መሰዋእትነትን ወዶ ሰማዕትነትን ያለመ እኮ ነው – መንፈሱ። ይህ ብቻ ታላቅ ሥጦታ፤ ብርቅ ሽልማት አይደለምን?

የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ለማስወገድ እኮ ልቡ በሸፈተው ህሊና ውስጥ መፍትሄ አመንጭ የነፃነት ተጋድሎ ፍልስፍና አልነበረንም። በወያኔ ማንፌስቶ ልባችን ሥነ – አእምሯችን ሸፈተ፤ ግን ወላዊ የሆነ ችግኝ አልቦሽ ነበር። አሁን ለዛ ወላዊ ለሆነ ችግኝ አልቦሽ ለነበረ ሥነ – አዕምሯችን ለሚሊዮኖች ዘር ተዘራ። ከዚህ በላይ ሊጠበቅ የሚችል ሰብል ያለ አይመስለኝም። ከዚህ በላይ ሊጠበቅ የሚችል ክስተት ሊኖር አይገባም። እነዚህ ሰዎች ሳይሰደዱ እዛው ሆነው፤ መከራን ለመቀበል የወሰኑ ድንቅ ወገኖቻችን ናቸው። ትውልዱን አዳኑት። ሰው አይደለም መጠላት ያለበት መንፈሱ ነው። ለተሳሰተው ሰው መሳሳቱን እንዲወቅሰው መዶሻ ሆኖ እረፍት እንዲነሳው ማደረግ የሚቻለው በአቅምህ ውስጥ መቻቻልን አስገድደህ ስትግተው ብቻ ነው። አብረው ለመሥራታቸው በወያኔ ሥር ባለ ሥርዓት በቅደመ ሁኔታ መታሰር በፍጹም ሁኔታ የለበትም። ስልት ያስፈልጋል። ጥበብ ያስፈልጋል። ጊዜን ማድመጥ ያስፈልጋል። ወቅትና ሁኔታን ማጥናት ያስፈልጋል። ፖለቲካ መርጋትን ይጠይቃል። ከስሜታዊነት በፍጹም ሁኔታ መውጣትን ይሻል። አለስፈላጊ የሆነ መስዋዕትነትም መክፈል አያስፈልግም። ወልዲያ ላይ ራሳቸው እነታጋሩ በጥጋባቸው በፈጠሩት መንጠራራት ኢትዮጵውያን በመንፈስ ጦርነት ገጠሙ። ማን ታሠረ? ማን ታፈነ? ማን ነገን በፍዳ ያወራርዳል? ይህን ደም፤ አቅም የለሹ የወልድያ አማራ እዬተገላበጠ ያዋራርዳል። ትግራይ ላይ በጠፋው ጥፋት አንድ ወጣት አይታሠርም፤ ምን አልባት አማሮች አነሳሱት ሊባል ይችል ይሆናል፤ ቀጣዩም ፈተና ወደዬት እንደሚጓጓዝ አይታወቅም። ቢታሰሩ እንኳን የትግራይ ወጣቶች በወንጀል እንጂ „በሽብርተኝነት“ አይሆንም። አማራ ግን „በሽብርተኝነት“ ነው። ቀፎ እንደተነካ ንብ የተጋሩ ወጣቶችን ያስነሳቸው የሚሊዮኖች መፈናቀል፤ የዘር ጥፋት፤ የሚሊዮኖች የእስር ሰቆቃ አይደልም። ዕንባ በኛ በትግራይ ሥረዎ መንግሥት እኛን መንካት አይገባውም ነው። በቃ! እግዚአብሄሩም ካለው ጋር  እዬመከረ ነው። ቀኑን አራቀው። 26 ዓመት ቀርቶ 26 ቀን ምን ይከብድ?

አሁን ወደ ቀደመው እንደ አቨው፤ እጅግ የማከብርህ ጋዜጠኛ ኤርምያስ ለገሰ ባለፈው ዓመት የአውሮፓ ኮሚሽን በጠራው ስብሰባ ላይ ከግ7 ሊቀመንበር ከሆኑት ከአርበኛ ፕ/ ብርሃኑ ነጋ ጋር ተቀመጥክ ተብለው እኮ ነው ኢትዮጵያዊው ማንዴላ ዶር. መራራ ጉዲና የታሰሩት። አሁን ዶር. መራራ ጉዲና የኬሚስተሪ ወይንም የባይሎጂ ሊቅ አይደሉም። የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌስር ብቻ ሳይሆኑ ኢትዮጵያ በታሪኳ በፖለቲካ ዕውቀት ላይ የተመሰረት ፓርቲ መሪ ሲኖራት የመጀመሪያው ናቸው። ይህም ብቻ ሳይሆን መሬት ላይ በሙያቸው የዞጋቸውን ፓርቲ መሥርተው የሚታገሉ ሰላማዊ ታጋይ ናቸው። እሳቸው የፖለቲካ ሊቅ ስለሆኑ ማናቸውንም የፖለቲካ ሃሳብ እንደ ሱቅ ዕቃ፤ እንደሚገዛ ሸሚዝ ወይንም ጫማ የሚሸምቱ አይደሉም። አማተር ወይንም የጫካ ፖለቲከኛ አይደሉም። ዕወቅቱ ብቻ ሳይሆን ዕድሜያቸው ፖለቲካ ነው። ግን አቅም የለሹ፤ በሁሉም ዘርፍ በበታችንት ስሜት የሚናጠው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሐገር የተወረረ እስኪመስል ድረስ በጦር ሃይል ነበር ተቀብሎ እስር ቤት ያስገባቸው። እሱ ብቻ አይደለም እኒያ ሊቅ ወደ እስር ቤት ሲሄዱ በካቴና ታስረው ነበር። ሐገር እራሷ በዚህ ድርጊት ታፍራላች። ደግማ የማታገኛቸው ዕንቁ ናቸው እና። ህገ መንግሥት የሚባለውም እንደ ፕላስቲክ ከእሳት የገባ ነው የሆነው በዚህ አሳፋሪ ድርጊት። እና ነገ የኦህዲድ መሪዎች ከአዲሶቹ የጵላጦስ ምላጮች ከእነ ፈርኦኒት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር ሆነ ከእነ አቶ ጌታቸው እረዳ ጋር ስበሰባ ላይ አብረው ሲቀመጡ እንደ ወንጀል ልናይባቸው ይሆን? ይህን ካልን ወያኔ ሃርነት ትግራይ በዶር. መራራ ጉዲና ላይ የወሰደው እርምጃም ትክክል ነው ማለት ነው። ደግሞ እኛ ከዬትኛው እስር ቤት ይግቡ ብለን እንፈርድባቸው ይሆን ያሰኛል? ስንገርም። እኛስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አለማወጃችን ምስክራችን ከቶ ምን ይሆን? „አናስደንግጣቸው!“

የፖለቲካ ህይወት „የማን ደም ፈሰሰ“ የምንልበት በፍጹም ሊሆን አይገባም። ዘላቂ ራዕያችን ይሄን የፈንግጪው ግንፍል ስሜት እንዲጎበኘው በፍጹም ሁኔታ መፍቀድ የለበትም። ሰከን ብሎ ማዬት ያስፈልጋል። የትኛው ነው የሚቀድመው? የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ከሥሩ ያነወጸው አዲሱ ፍልስፍና ‚ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ወይንስ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ያን ጥቃቱን፤ ያን መበለጡን ለመለበጥ የሚወስዳቸው ቀጣይ አስገዳጅ ቅብ እርምጃዎች? የወያኔ ሃርነት ትግራይ እነኝህን ወገኖች በተለያዬ ሁኔታ ሊያጠፋቸው እኮ ይችላል። ስልታዊ መሆን ካልቻሉ። እራሱን ወያኔ ሃርነት ትግራይን እኮ መንፈሳቸው ተለማማጭ እንዲሆን ያደረገው፤ ሳይወዱ በግድ ቋቅ እያላቸው „የኢትዮጵያን“ ሥም እንዲጠሩ ያስደረገው እኮ ሰከን ያለው የወጣቶች ጉዞ ነው። ይህም ለማዘናጋት ሆን ተብሎ የተቀዬሰ ነው።

አልፎ አልፎ ከንቀትም፤ እስኪ እናያለን ሲቀጥል፤ ግብታዊነት ነው፤ ለፖለቲካ ዕውቅናን ለማግኘት የሚሉ ሃሳቦችን አነባለሁ ከሰማያዊ ፓርቲ ሳይቀር። ይገርማል። ከውስጥ ስለመሆኑ፤ ከጥቃቅኗ መነሳታቸው፤ ጠብቀው ካቆዮዋቸው የዕውነት አውዶች ስለመሆኑ፤ ቀስ እያሉ ጊዜ እዬጠበቁ፤ ሁኔታን እያዳማጡ በቁጠባ፤ በልክ እዬተራመዱ ስለመሆኑ መንፈሱን ከውስጥ አድርጎ ለሚመረምር ሰው ፍቹን ያገኘዋል። በጥልቀት እኔ ሂደቱን በግሌ እያጠናሁት ነው። ፍትሃት ስለሆነ። በተከታታይም ቅን መንፈሳቸውን እየተከታተልኩኝ እሰራበታለሁ።

ወንድሜ ጋዜጠኛ ኤርምያስ „ፋሽስት“ አሉት ብለኽ ያነሳኸው ምንጭነት። ያማል ልበለው ይገድላል? አንደኛ፤ እሳቸው የቤተ መንግሥት ውርሰኛ በነበሩበት ወቅት ብዙ ሰው ጽፎታል ‚ቃሉን“። ያው ሚዲያ የሚናገርለት ያለው ያቺን ቃል ገልብጦ ሲጽፋት ወይ ሲናገራት ካለ ኮፒራይት እንደ እሱ አፍላቂነት ይታያል እንጂ። ይሄ የወያኔ ሃርነት ፋሽስትን ለማጠቃሻነት የተጠቀሰው ድርጊቱን ቢገልጸውም ነገር ግን መጀመሪያ „አማራ አለ“ ብሎ ከሚነሳ ማንነት ላይ ቢሆን አያቆስልም – ምንጩ። „አማራ የለም“ ከማለት ውጪ ምን ፋሺስትንት፤ ምን ናዚዝም አለና ቀድሞ ነገር። ትናትም በሚሊዮን በሚቆጠር መስዋዕት ለሆነ „አማራ“ ዛሬም ጫካ ላይ እናት ነፍሱጡር አዲስ ህጻን እስከመገላገል ድረስ፤ በሁለቱም አንጋፋ ሃይማኖቶች ሰፊ የሆነ ሀገራዊ ድርሳን ያበረከተ ማህበረሰብ፤ በሀገር በማናቸውም ግንባታ ዘርፍ ብቁ ተግባር የከወነን ባላውለታ ማህበረሰብ „የለም፤ አልነበርክም፤ ዘረቢስ ነህ፤ ታሪክ የለህም በኢትዮጵያ መሬት“ ከማለት በላይ ፋሽስትነት የለም። ዛሬም ጥፍር የሚወለቀው፤ በገጀሞ የሚከተከተው፤ የሚንኳላሸው፤ እሳት የሚለቀቅበት አማራ ሳይሆን „እንሰሳ ነህ“ እንደማለት ነው፤ ይህ ለእኔ Discrmnation ነው። ሰብዕዊነትም ከዚህ መነሳት አለበት። ኢትዮጵያዊነትም ከዚህ መነሳት አለበት። አፍሪካዊነትም ከዚህ መነሳት አለበት። ከዚህ ያፈነገጠ ኢትዮጵያዊነት ግንጥል ጌጥ ነው። ስለዚህ ማመሳከሪያ ያደረከው የተከበሩ ፕ/ መስፍን ወ/ማርያም አባብል ሳልደብቅህ መንፈሴን አቃጥሎታል፤ ማህጸኔን ቀዶታል። በሰብዕዊነት አንኳን ጋዜጠኝነት ፍሬ ነገሮችን መፈተሽ ካልቻለ … እንጃ ነው። እሳቸው ሰብዕዊ አይደሉም። ኢትዮጵያን አሸማቆታል።

አዬ እሳቸው ኢትዮጵያን መንፈሷን ሲሰልሉ፤ ሲሰለስሉም የኖሩ ብቻ ሳይሆን ጉልበታማ መንፈሷን በስውር የሸጡ የውስጥ አርበኛ ናቸው። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ቢቃጠል፤ ሌላ መዝሙር ይዘው ብቅ ይላሉ፤ ዕድሜውን ከሰጣቸው። እስኪ የሳቸው መንፈስ አርፎበት በተፈጠረው ቀስተደመና ፓርቲ ውስጥ ወጥ አማራዊ መንፈስ መዋቅሩ ውስጥ ነበርን? ቅንጅት ማዕከላዊ ሥ/አ/ ውስጥስ አንድ የጎንደር ልጅ ነበርን? አንድነት አንድ ብሎ ሲጀምር እሱም የከርሸሌ ሲሳይ ሆነ። ይህ ከሳቸው እራስ የማይወርድ እንቆቆ ነው። ዛሬም የሚታዬው ይኼው ነው። አቅም አለው ካሉት ይጠጋሉ፤ በመንፈስ እዬኮረኮሩ እርቃኑን ሲቀር ከትከት ብለው እየሳቁ ገልበጥ ይላሉ …

በአጽህኖት የምገልጸው „አማራ የለም“ ከማለት ወዲያ የጸና ፋሽስትነት፤ ዘረኝነት ለእኔ የለም። አማራ የለም ከተባለ ወያኔ ዘሩን ያጠፋው ማህበረሰብ የለም ማለት ነው። አማራ ደመ ከልብ እንዲሆን ታስቦ ነው። የወያኔ ማንፌስቶም ሥራ ላይ አልዋለምም ማለት ነው። ይሄም ብቻ አይደለም የወያኔ የማንፌስቶ መንፈስ በኢትዮጵያ ላይ ተግባራዊ መፈተኛ አለሆነም ማለት ነው ጠለቅ ብለን ስንመራምረው። ምክንያቱም „በአማራ መቃብር ላይ ነው የትግራይ ሪፕብሊክ እንመሰርታል፤ የትግራይ ተራሮች የአማራ መቃብር ይሆናሉ“። አድርገውታል። ታላቋ ትግራይም በተሟላ አቅም እና ዕወቀቅና ተመሥርታላች እኮ የህልም ሐገራቸው።

ማውጫ እምናደርጋቸውን መንፈሶች የሚሊዮኖችን ህሊና እንዳይጎዱ እንደ አንድ ሚዲያ ጥንቃቄ ቢደረግ መልካም ነው። ይሁን እያልን የምንልፋቸው ነገሮች እንደ ተጠበቁ ሆነው። የሰብዕዊ መብት ተሟጋች አድርጎ እሳቸውን ለማቅረብ አቅም ያንሰዋል ፍልስፍናቸው ሆነ ሰብዕናቸው። አላዝንም ስለቃሉ። በእኔ ውስጥ እምኖረው እኔ እንጂ ሌላ አይደለምና። የጉዳቴን ልክ እማውቀው እኔ ብቻ እና እኔን መሰል ስለ ሰብዕዊነት የሚታገሉ ጋዜጠኞች፤ ሚዲያዎች፤ ደጋግ የሰብዕዊ መብት ተሟጋቾች፤ ተጠቂው እራሱ የአማራ ማህረሰብ ብቻ ነው።

ሰሞኒት።

ሌላም በሰሞናቱ የተነሳች አዲስ ፍልስፍና አለች ። የኦህዲድ ካቢኔ በህዝብ እቅፍ ውስጥ መሆኑን የተረዱ አጀንዳ የሾለካቸው „ እኛ ኦሮሞዎች ወደድክም ጠላህም እንገዛሃለን“ እያሉ ነው። ይህ ያን የተስፋ ካቢኔ አቅሙን ለማሳሳት ታስቦ ከወያኔ ሃርነት በላይ እዬታገለ ያለ ድውይ መንፈስ ነው። „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ወንፊት አንድርጎታል ድብቅ አጀንዳውን ሁሉ። እንዲያውም ዘገባ ላይ ሥማቸውን ለመጥራት አቅም አንሶ „የኦሮምያ ፕሬዚዳንት“ ሆኗል ጨዋታው። ዲል ያለ ድል ማለት ይሄ ነው። ስለሆነም ለድንቁ መንፈስ ድንቅነሽን መስጠት በልግስና ይሁን። ብልህነት ይሸመት። ማስተዋል ይገዛ። ሥነ -ልቦናዊ አቅም ይዳብር። አምላካችንም ይርዳን አሜን!

https://www.youtube.com/watch?v=R_kzF3c67QU

ESAT Efeta December 2017

መነሻዬ ሚዲያ መድረሻዬም ሚዲያ እንደ መከወኛ።

„የሕወሐት አዳዲስ መሪዎች ከሌሎች የኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች መሪዎች ጋር የሚኖራቸዉ ግንኙነት እና የሚያሳርፉት ተፅዕኖ እስከ የትእነት ለአሁኑ በግልፅ አይታወቅም። ባለፉት ሁለት ዓመታት በኦሮሚያ፤ በደቡብ እና በአማራ መስተዳድሮች የሚደረጉ ሕዝባዊ ተቃዉሞችን፤ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚነሱ የሙስና፤ የኑሮ ዉድነት፤ የፍትሕ፤ የሰብአዊ መብት ጥያቄዎችን ለመመለስ አዳዲሶቹ መሪዎች አዲስ ዕቅድ መንደፋቸዉም አይታወቅም። መቀሌ ተሰበሰቡ፤ ከቀመሌ ነዋሪ ቢያንስ አንዱን ሻሩ፤ አዲስ አበባ ነዋሪ፤ አድዋ ተወላጆችን መረጡ። አበቁ። እንዴት የልብ የሆነ አገላለጽ ነው። ቅቤ ያጠጣል። ወይ ቤተ – ዶቸቬሌ እንዲህ ጨዋታ ያውቃል ለካንስ „እኛም እናብቃ“ አለ ዶቸቨሌ እኔም ላብቃ ….

 

ማስታዋልን ቢያንስ አንቅረበው።

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

እልፍ ነን እና እልፍነታችን በተግባር እልፍ እናድርገው።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ። መሸቢያ ጊዜ።

መቋሚያ (ሥርጉተ – ሥላሴ)