ሬክስ ቴለርሰን ከስልጣን ተሰናበቱ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 4/2010) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የውጭ ጉዳይ  ሚኒስትራቸውን  ሬክስ ቴለርሰንን ከስልጣን አሰናበቱ ፡፡

በምትካቸውም የሲ አ ይ ኤ ዳይሪክተር ማይክል ፖምፒኦን  መተካታቸውን አስታውቀዋል።

ሬክስ ቴለርሰን ኢትዮጵያን ጨምሮ 5 የአፍሪካ ሃገራትን ጎብኝተው በተመለሱ ማግስት ነበር የስንብታቸው ዜና የተሰማው።

የዩኤስ አሜርካው ሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ  የአሜሪካው የሰለላ ድርጀት ዳይሬክተር  የሆኑትን የ54 ዓመቱን ማይክል ፖምፒኦን  የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገው መሾማቸውን ያስታወቁት ዛሬ ማለዳ በቲዊተር ገጻቸው ነው፥ የሪክስ ቴለርሰንን ስንብት ያወጁትም በምስጋና  ነበር፡።

አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክል ፔምፖ ድንቅ ሰራዎችን ይከውናል በማለት ከወዲሁ ተስፋ ያደረጉት ዶናልድ ትርምፕ፣ ለሲ.አይ. የኤ ዳይሬክተርነትም የ61 ዓመቷን  ጂና ሃስፔልን መሾማቸውን አስታውቀዋል።የሲ አይ ኤ ምክትል ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ ያሉት ጂና ሃስፔል የመጀመሪያዋ አንስት የሲ.አይ.ኤ  ዳይሬክተር አንደሚሆኑም ታውቋል። ሪክስ ቲለርስን ከአፍሪካ ጉዟቸው መልስ የተሰናበቱብትን ምክንያት  ዶናልድ ትራምፕ አልተገለጹም።ሪክስ ቲለርሰን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት ለአንድ አመት ብቻ መሆኑንም መረዳት ተችሏል።

 

The post ሬክስ ቴለርሰን ከስልጣን ተሰናበቱ appeared first on ESAT Amharic.

ሬክስ ቴለርሰን ከስልጣን ተሰናበቱ