ፍትህ ለግፉአን ! ልጃቸውን ለመፈለግ በወጡበት የ66 አመቷ አዛውንት በአግአዚ የጥይት ራት ሆነዋል ።

እናት ለልጇ ስትል ….! (በላይ ማናዬ)

ከሶስት ቀን በፊት ጥር 2010 የጥምቀት በዓል ላይ ተቀስቅሶ ለቀናት በሰነበተው በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የተለያዩ ቦታዎች በዘለቀው ህዝባዊ ተቃውሞ ግፍ የተፈፀመባቸውን ንፁሃን ዝርዝር አቅርቤ ነበር።

ከግፍ ሰለባዎች መካከል የ66 አመት እናት ወ/ሮ ዝይን ንጋቴ ይገኙበታል። ወ/ሮ ዝይን የ6 ልጆች እናት ነበሩ። ወ/ሮ ዝይን በተቃውሞው ወቅት ወልዲያ ላይ ልጃቸውን ፈልገው ቤት ይዘው ለመግባት በወጡበት ሳይመለሱ የጥይት እራት ሆነው ቀርተዋል።

መቼም ሥርዓቱ በንፁሃን ላይ ለሚፈፅመው ግፍ ጉልህ ማሳያዎች እናቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀመው አሰቃቂ ድርጊት ዋናው ነው። እስኪ አሁን ወ/ሮ ዝይን ላይ የተፈፀመው ግድያ በምን ሊሳበብ ይችላል? በምንም! ወ/ሮ ዝይን በዚህ የእርጂና ዘመናቸው ጧሪ ይሆነኛል ያሉትን ልጃቸውን ፍለጋ ወጥተው በዚያው አስቀሯቸው።
ፍትህ ለግፉአን!

ግፍ ይብቃ!!

ፍትህ ለግፉአን ! ልጃቸውን ለመፈለግ በወጡበት የ66 አመቷ አዛውንት በአግአዚ የጥይት ራት ሆነዋል ።