ለ ወንድሜ መምህር  አምባቸው ደጀኔ – ወልድያ (ከአባዊርቱ)

በመጀመርያ ክብር ለኢትዮጵያ መምህራን ይሁንልኝ በያላችሁበት ቦታ፤፤  በመቀጠል ለዚህ ቤት አስተዳዳሪዎች ከፍ ያለ ይቅርታን እየጠየኩ ድንገት ሁላችን እንማማርበት ዘንድ ይህን የመጨረሻ ለግለሰቦች መልክቴን ታወጡልኝ ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ፤፤
አምባቸው ሆይ እኔም አንተ ብዬ ልበልህና አስቀድሜም በ እንዲህ ልጀምር፤፤ አሁን እየተጠነቀቅኩ እንድፅፍ ልታረገኝ ነው፤፤ የኔው እንደወረደ ነበርና፤፤ አማርኛው ደግሞ ሁለተኛ ቁዋንቅዋ በተለይ  ለሆነው ላለመበለጥ እያልን  ጥንትም እንተጋ ስለነበረ የ ልጅነት አስተማሪዬንም አስታወስከኝና አስፈገግከኝ፤፤ በጣምም  ከልብ አመሰግናለሁ ስለ እርምትህ፤፤ እንዲህ ነው መማማር የሚጀምረው፤ እስቲ አንተም ኦሮሚፋን ልመድ፤፤ እንዴት ቀና መሰለህ፤፤  መቼስ ወልድያ ሆነህ ይህን አታጣውም ከሚሴ ሩቅህ አይደለምና፤፤ እኔ የኦሮማራ ጥምረትና መናበብ ለአገራችን ትንሳኤ ወሳኝ ነው ከሚሉት ጎራ ነኝና፤፤
ወደ አነሃሳቸው ፍሬጉዳዮች እንግባ እስቲ፤፤ እኔ በመጀመርያ የጎሳ ፖለቲካ አድናቂም አይደለሁም የጎሳው ፖለቲካ የወለዳቸውንና ካሉቱ ቅን የመሰለኙን ግን አዎ አድንቄአለሁ አደንቃለሁምም፤፤ ከነዚህ ውስጥ በተለየ ለዶር አቢይና ቲም ለማ ለተባሉት ሁሉ አማሮቹንም እነገዱንና አስተዋዩን ደመቀን  ጨምሮ አድናቆት አለኝ፤፤ ለምን አደነኩዋቸው እነዚህን ሰዎች? በጎሳም ይምጡ እንጂ ኢትዮጵያዊነት ከስሞ በጠፋበት ዘመን የኢትዮጵያዊነትን ፀጋ ተላብሰው ብቅ በማለታቸውና እስካሁን ከምሰማውና ከምረዳው በአመዛኙ ምግባራቸውም ይህንኑ ስለሚነግረኝም ነው፤፤ ምናልባት አንተ በቅርብ ያለኅው ከኔው የውቅያኖስ ማዶ እይታ ሊለይ ይችላል፤፤ ሆኖም ካዩትም ከሰሙትም የምረዳው ደሞ  ይህንኑ ነው፤፤ ሰርፀም አንተም የምትነካካልኝ አገሪቱ ወደ አስከፊ የብሄርተኛ አክራሪነት እየሄደችን ነው፤፤ ከሆነም እንግዲህ እስከምርጫው መሆኑ ነው እንደሚገባኝ፤፤ መቼስ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስምሪት ስንገባ ይህ የብሄር ልክፍት ይከስማል ብለን እንጠብቃለን ፤፤ ይህ ከሆነ ይህ የተፈራው የኦሮሞ ብሄርተኛ አክራሪነት (በአቢይ አስተዳደር ውስጥ አለ እንኩዋ ቢባል) መክሰሙም አይደል? የኔው ፍራቻ ማ ሊያሻግርን ታቅዱዋል ከነዚህ በፈጣሪና በህዝብ ግፊት «የተወለዱትን» ሰዎች በቀር ነው እያልኩት ያለሁት፤፤ ወደ ሁዋላ በተለይ በዚሁ ሳተናዎች መድረክ ፅሁፎቼን ብትመረምር ለአክራሪዎች የማልመች ነኝ፤፤ ለምን? በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ አቁዋማቸውን ስለማልወደውና ስለማልደግፈው፤፤ አደለም ለኢትዮጵያዊነት ለኦሮሞነትም ጠንቅ መሆናቸውን ጠንቅቄም ስለምረዳ፤፤ ከውጭ ከስደቱም ገና እንደገቡ ወይም ሳይገቡም በፊት ከነቲም ለማ አብረው እንዲሰሩ ስማፀን ሳስጠነቅቅም ነበር፤፤ አንዱ ግብዝ እዚሁ መድረክ ላይ (መቼስ የነተኩላዎቹ አፈቀላጤ መሆን አለበት) የሆነ ከነ ዶር አቢይ ዳረጎት የምፈልግም አስመስሎ ብሎኛል፤፤
መቼስ የሌባ እናት ልጁዋን አታምን እንደሚባለው ሆኖ ሁሉ እንደራሱ ሆድ አደር ስለሚመስለው ምንስ ይገርማል፤፤ እናም የነዚህ አክራሪዎች በመንግስት ላይ ተፅኖ ፈጣሪነት እጅግ እየከረረ የሚስተጋባው በፅልመቶቹና ውላጆቻቸው ሆኖና ድምፃቸው ከፍ በማለቱ እንጂ የእነዚህን ሰዎች የስካሁኑን ስራቸውን ላየ በኔ በኩል ይህ ይሆናልን አልተቀበልኩም፤፤ ወንድሜ ሆይ! አደለም በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ባልኖረበት አገር በታላቁዋም አሜሪካ «ጋራንቲ» የሚባል አለመኖሩን ደግሞ እነሆ በትራምፕም አይተነዋል፤፤ ያነሳሃቸውን ስጋቶች ሁሉ እጋራለሁ፤፤ ሁሉም ደሞ ገደል አይደለም፤፤ ሰርፀ የሚለን እኮ ከባድ አካሄድ ነው፤፤ ዶር አቢይን አደባባይ በሚሰሩትና በሚናገሩት አይኔ እያየ በፅንፈኞች ሃይጃክ ተደርገዋል ወይም ኦሮሞ በንግድ ባንክ ማኔጅመንት  ቁጥሩ ጨመረ ብዬ እንቅልፍ አላጣም፤፤ ዋናው እኔ የማየው ያሉንን ቀና አያመላከትን በሃሳብም እየረዳን ትክክለኛና ገንቢ ትችትም እያቀበልን በመላ እንዲያሻግሩንን ነው፤፤ ባሁኑዋ ጊዜ የኢትዮጵያ ጠላቶች አድፍጠው ውድቀቱዋን በሚጠብቁበት ጊዜ ከአቢይ ጋር አላስፈላጊ «ጦርነት» አክሳሪ ነው እንደሃገር፤፤ ዛሬ አንተው በገለፅከው በየጎጡ የሰከረን ሃገር አቢይ ና ቲም ለማን ዛሬን ብትሸኛቸው ማን ነው ክፍተቱን ሞልቶ በሰላም አሻግሮ ወደምንፈልግበት የሚያደርሰን?  እባክህን ጥንት ወያኔዎቹም እንዲህ ይሉን ነበር ኢትዮጵያ ግን ሰንብታለች እንዳትለኝ ብቻ፤፤ ይህ የሚለየው በስመ ነፃ «ዴሞክራሲ» ሁሉ አደባባይ የወጣበትና ያንኑ ያህልም የፅልመትን ክፉ አዝመራ መቃመስ የጀመርንበት አስፈሪ ጊዜ ነውና፤፤ ያሉን መሪም ሃይል እንዲጠቀሙ እስከመማፀን የደረስንበት ጊዜም ነውና፤፤ ስለሆነም እንዲህ አይነት ለየት ያለን  መሪ በታሪካችን ስለተከሰተ እስቲ እንየው ከሚሉት ጎራ ነኝ፤፤ ምነው መለስ ይሁኑ አሁን መሽገው መቀሌ ካሉት አንዳቸው እንኩዋ እንዲህ አይነቱን ቅንነት በተላበሱና ከትግራይ ሆነው እኔ ዖሮሞው እንዲህ በተከራከርኩላቸው ኖሮ፤፤ ያልተፈጠረባቸውን ከዬትስ ያምጡት? በነገራችን ላይ  አንዱ የነዚሁ  የተኩላዎቹ ድሮን ሳይሆን አይቀርም አጋዚያን ተመልሰው ያሻግሩን አያለልህ ነው፤፤ ወታደሩ ጣልቃ ይግባ እያለ፤፤ ነገ ደሞ አንዱ ፅንፍ ይነሳና «እኛ አያለን?» ይለሃል፤፤ እንኩዋንስ ከ 28 አመታት በሁዋል እንዲህ ተካርረን ቀርቶ ጥንትም በንጉሱ ጊዜ ኢትዮጵያን ያስተዳድሩት የነበረው በመላ ነበር፤፤ እናም አንዳንድ ከንቱዎች እንዳሰቡኝ አቢይ ወይም ለማን በብሄር ታጥሬ  በጭፍን ሆኖ አይደለም፤፤ ገና ዳይስፖራው ሲመለስ አደራ ሌላው ቢቀር የኪራያችሁንና አስቤዛችሁን ሳትችሉ ተቃዋሚ ሆነ ተቃራኒው አገር አትግቡ ብዬ የተማለድኩ ሰው ነኝ (በሳተናው ታገኘዋለህ)፤፤
ለህሊናዬ ተገዢም ነኝ፤፤ ያየሁትን ትክክሉን ትክክል፤ የማይሆነውን ደሞ ርካሽነቱን ለመናገር ደቦ አልፈልግም፤፤ የኦነግን ከንቱነት የምናገረው ለኢትዮጵያዊ ተብዬው ጆሮ ልዩ  የሙዚቃ ቃና እንዲሰጠው ሳይሆን ከንቱነቱን ስለምገነዘብም ጭምር እንጂ፤፤ ደሞ ዬትም አይደርሱም፤፤ ታየዋለህ፤፤ ፅንፍ የአማራውም በለው የኦሮሞው በለው እንደፀነፈና እንደጨነገፈ ይቀራል እንጂ አብላጫው ህዝብ አይቀበለውም፤፤ በዬትም አለም እንዲሁ ነው፤፤  ግን ሰርፀን ወይም አንተን ወንድሜን ደስ ይበላችሁ ብዬ ህሊናዬ የማይቀበለውን የጅምላ ፍረጃን አላደርገውም፤፤ ሰርፀ እኮ ኦነግንና ዖሮሞን ልክ እንደተመጋጋቢ ገባር ወንዝ ነው የወሰዳቸው፤፤ሁሉ ኦነግ ኦሮሞ ሊሆን ይችላል ሁሉ ዖሮሞ ግን ከቶ ኦነግ ሊሆን አይችልም፤፤ አገራችን አዘቅት የገባችው እነፅልመቶች የጎሳ መርዝ የቀመሙልን ጊዜ ነው፤፤ ዛሬ እንተን ልብህን ሰብሮ ለኔ ማመልከቻ ያፃፈህ እኔም በአደባባይ ምላሽ የምሰጥህ የዛ መርዝ ተቁዋዳሽ ሳንፈልገው ስለሆንም ነው፤፤ የምናልመውንና የምንመኝውን ትክክለኛ ዴሞክራሲ ለማምጣት በየሰውም ጫማ መግባትን ይጠይቃል፤፤ ካልተቻለን ቢያንስ እንድ ትውልድ በዚሁ የጎሳ ቀውስ ሰለባ ስለሆነብን ትእግስትንና ፅናትን ይጠይቃል በሰላም ለመሻገር፤፤ እያንዳንዱዋን የጎረበጠችን እናለስልስና እንራመድ ካልን እንኩዋንስ ዴሞክራሲን ልንገነባ ቀርቶ በጉርብትናም አንድ ምድር ላይ አብረን ላንቆይ ነው እንደህዝብ፤፤ ሁሉ ፈላስፋና ልደመጥን ከፈለገ ማ ማንን ሊሰማ ነው? ለዚች ከንቱ አለም እንዲሁ አንተም እንደተከፋህ እኔም እንደተከፋሁ ማዶ ለማዶ መቅረታችንም አይደል? አነ አቢይንና ቲም ለማን የማየው ማዶ ለማዶ ያለንን ለማቀራረብ መጣራቸውን ብቻ ነው፤፤ ከባዱ የስራ ድርሻው ያለው በአንተው አይነት መምህሩና በኔ ቢጤው ተራው ዜጋ ነው ብዬ አስባለሁ፤፤ በየሚዲያው የሚለቀለቀውን ስታይ ሁሉ ፅንፍ ይዞ ሲባላና ሲያባላ እንጂ ቆም ብሎ እንዴት ብረዳና በቀናነት እራሴን ብመረምር ትንሽዬ እንኩዋ የበኩሌን እወጣለሁን  ቁጥሩ አይን አልገባ አለኝ፤፤ በዚህ ላይ በክፍያም በለው በውዴታ እነዚህ ጨለምተኞች ተመልሰው እንዲመጡ ከፍተኛ ዘመቻ ተከፍቱዋል፤፤
ፍትግያው ከፅልመትም ከአክራሪም ከአውቆ አበድ ምሁርም ሆነና ምስቅልቅላችን የወጣ ይመስለኛል፤፤ ስንቱን አንስቼ ስንቱንስ እጥለዋለሁ፤፤ በትንሹም ቢሆን የተረዳኅኝ ይመስለኛልና፤፤ ከመሰናበቴ በፊት በምኞት ደረጃ ያ የሱማሌ ክልል ሙስጠፌና የአኝዋኩ ቅን ዜጋ ኦባንግ  ከነ ዶር አቢይና ቲም ለማ በፌዴራል ደረጃ ቢቀላቀሉና ግምባር ቢፈጥሩ ትልቅ ስራ ይሰራሉ ብዬ አስባለሁ፤፤ እንዳሁኑ ኢሃዴግ ቁመና ባይሞክሩት ይሻላል፤፤ በሚቀጥለውም ምርጫ እኒሁ የጠቀስኩልህ ቢመረጡ አገራችን ከገባችበት መአት አዝግማም ቢሆን በ 10 አመታት ውስጥ ከፍ ያለ ለውጥ ይመጣል ብዬ አስባለሁ፤፤ ከውጭ የተመለሱት ውስጥ ሆነ አገርቤትም ካሉት በ ኢሃፓና መኢሶን ፖለቲካ ህይወት ያለፉትን ለኢትዮጵያ አስተዳዳሪነት አልመኝም፤፤ እነዚህ ሰዎች እጅግ መልካም ምን ቀና ቢሆኑ የ 28ቱ አመታት ትውልድ ከፍተኛ ጥንቃቄን የሚፈልግ ነው ብዬ እሰጋለሁ፤፤ የየጎሳ ፖለቲካ ፖለቲካ ሳይሆን የወጣት አይምሮ ወይም ያልተነካካ ትውልድ አይምሮ ሊያሽረው የሚገባ መርዝም በመሆኑ፤፤ እነዚህ የጠቀስኩልህ ሰዎች ይህን ይወጡታል ብዬም አምናለሁ፤፤ ይቅርታ አበዛሁብህ፤፤
ሰላም ሁን
መልካም የስራ ዘመንም ይሁንልህ

The post ለ ወንድሜ መምህር  አምባቸው ደጀኔ – ወልድያ (ከአባዊርቱ) appeared first on ሳተናው: የዕለቱ ዜናዎች እና ሰበር ዜናዎች – መረጃ ማግኘት መብትዎ ነው!.

ለ ወንድሜ መምህር  አምባቸው ደጀኔ – ወልድያ (ከአባዊርቱ)