በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተው እሳት ሙሉ ለሙሉ ቁጥጥር ስር አለመዋሉ ተገለጸ

በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተው እሳት ሙሉ ለሙሉ ቁጥጥር ስር አለመዋሉን የፓርኩ የህብረተሰብና የቱሪዝም ሓላፊ አቶ ታደሰ ይግዛው ገልጸዋል፡፡

በዛሬው ዕለት እሳቱን ለማጥፋት በሄሊኮፕተር በመታገዝ ውጤታማ ስራ ሲከናወን ውሏል፡፡

ሆኖም አመሻሽ ላይ በተደረገው ቅኝት በሁለት ስፍራዎች ላይ ጭስ መታየቱ ተገልጿል፡፡

የእሳቱ ጭስ በገደላማው አካባቢ የታየና ወደ ሌላ ስፍራ የማይዛመት በመሆኑ የከፋ አደጋ እንደማያደርስ የሄሊኮፕተር አብራሪው ገልጸዋል፡፡

ይሁንና፣ የፓርኩ የህብረተሰብና የቱሪዝም ሓላፊ አቶ ታደሰ ይግዛው የእሳቱ ጭስ ጠንከር ያለ በመሆኑ ትኩረት ይሻል ብለዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ነፃነት ወርቁ

The post በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተው እሳት ሙሉ ለሙሉ ቁጥጥር ስር አለመዋሉ ተገለጸ appeared first on ሳተናው: የዕለቱ ዜናዎች እና ሰበር ዜናዎች – መረጃ ማግኘት መብትዎ ነው!.

በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተው እሳት ሙሉ ለሙሉ ቁጥጥር ስር አለመዋሉ ተገለጸ