ሱዳን ውስጥ የሚታተመው የኢትዮጵያ ብር ህትመት ጉዳይ አሳሳቢ ነው

የትግሬ-ወያኔ መንግስት እስከምናውቀው ድረስ የኢትዮጵያን ብር የሚሳትመው ሱዳን ውስጥ ነው፡፡ ትግሬ-ወያኔ ይኽን ያደረገበት ምክኒያት ግልጽ ነበር፡፡
አሁን መጠነኛ ለውጥ ከመጣ በኻላ አብይ ብሩን እንዲቀይር ብዙ ግፊት ቢደረግም የሚሰማ አእምሮ አልተገኘም፡፡በተለይ አሁን የወያኔው የነገር አባት በሽር ስልጣን ወርዶ ሱዳን ቀውስ ውስጥ መሆኗ እየታወቀ እነ አብይ የብሩን ህትመት በተመለከተ ጸጥ ማለታቸው ያሳዝናል፡፡ የበሽር ደጋፊ የጸጥታ አባላት የሱዳን አዲስ ኖቶችን አትመው ካርቱም ውስጥ እየረጩ ነው፡፡ የኢትዮጵያንም ብር እንዲሁ አትመው ቢረጩ ምን ዋስትና አለ? ዛሬ የሱዳን ጦር ሀይሎች ካርቱም ላይ ከድሮ የጸጥታ መስሪያ ቤት ጠቅላይ መምርያ ውስጥ የያዘውን አዲስ የሱዳን ኖቶች ቪዲዎ ተመልከቱ፡፡
Adane Atanaw

The post ሱዳን ውስጥ የሚታተመው የኢትዮጵያ ብር ህትመት ጉዳይ አሳሳቢ ነው appeared first on ሳተናው: የዕለቱ ዜናዎች እና ሰበር ዜናዎች – መረጃ ማግኘት መብትዎ ነው!.

ሱዳን ውስጥ የሚታተመው የኢትዮጵያ ብር ህትመት ጉዳይ አሳሳቢ ነው