የኦሮሚያና አማራ ክልል የህዝብ ለህዝብ መድረክ ተሳታፊዎች አምቦ ከተማ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያና አማራ ክልል የህዝብ ለህዝብ መድረክ ተሳታፊዎች አምቦ ከተማ ገብተዋል። ነገ ለሚካሄደው የህዝብ ለህዝብ መድረክ የሁለቱ ክልል እና የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከሁለቱ ክልል የተወከሉ ተሳታፊዎች ወደ ከተማዋ ገብተዋል።

በዛሬው እለትም በፍቼ በኩል ለገቡት ከአባይ ወንዝ ጀምሮ፣ በደብረ ብርሃን በኩል ለገቡት ደግሞ በየከተሞቹ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። መድረኩ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን በማጠናከር ባልተገባ ትርክት ህዝብን ለማጋጨት የተወጠኑ ሴራዎችን በማክሸፍና ወንድምና እህት ህዝቦች በጋራ በመቆም ሀገራዊ ለውጡን ለማስቀጠል የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል።

የምዕራብ ሸዋ ዞንና የአምቦ ከተማም እንግዶቻቸውን በመቀበል ለነገው መድረክ ቅድመ ዝግጅታቸውን ማጠናቃቸው ተገልጿል።

The post የኦሮሚያና አማራ ክልል የህዝብ ለህዝብ መድረክ ተሳታፊዎች አምቦ ከተማ ገቡ appeared first on ሳተናው: የዕለቱ ዜናዎች እና ሰበር ዜናዎች – መረጃ ማግኘት መብትዎ ነው!.

የኦሮሚያና አማራ ክልል የህዝብ ለህዝብ መድረክ ተሳታፊዎች አምቦ ከተማ ገቡ