Menu

የአራት ኪሎዎቹን መንትያ ሕንፃዎች የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ተመለሰ

የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ በአዲስአበባ አራት ኪሎ አካባቢ የሚገኝና በደርግ መንግሥት የተወረሱባት ባለ12 ፎቅና ኹለት መለስተኛ ሕንፃዎች ተመለሱላት፡፡ ሕንጻዎቹ በልዩ ፖሊቲካዊ ውሳኔ እንዲመለሱላት መወሰኑን፣የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

ሕንጻዎቹን በአቡነ ቴዎፍሎስ አመራር፣ እስከ 10ኛ ፎቅ ከገነባች በኋላ ነበር በደርግ የተነጠቀችው፡፡ በመኖሪያነት የሚጠቀሙበትም ኾነ በንግድ የተሠማሩት ተከራዮች ባሉበት ይቀጥላሉ ተብሏል፡፡

የጠ/ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ በሰጡት አስተያየት “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቤተ ክርስቲያኗ ባላቸው አክብሮት በቃላቸው መሠረት ያስፈጸሙት ነው፤ …“የቤተ ክርስቲያንን ገቢ በማጎልበት የልማት ራእይዋን በራስዋ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዙ ናቸው፤”

ቤተክርስቲያኗ ከተወረሱባት ቤቶችና ሕንፃዎች ውስጥ፣ ከ830 በላይ አስመልሳ እያስተዳደረች ትገኛለች፤ በቀደሙት አባቶች የተሠሩት ሕንጻዎች ኪራይ፣ ከዋነኛ የገቢ ምንጮችዋ አንዱ ነው፤በአሮጌው ቄራው እቴጌ መስክ፣ 2 ባለ9 ፎቅ ሕንፃዎችን በ50 ሚሊየን ብር እያስገነባች ነው፤

ቤተክርስቲያኗ በ2010 ታክስን ጨምሮ 81 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ገቢ ሰብስባለች፤ በ2011ዓ.ም 85 ሚ.ብር ገቢ ዐቅዳለች፤

(ምንጭ፡-ሐራ ተዋህዶ)

የአራት ኪሎዎቹን መንትያ ሕንፃዎች የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ተመለሰ

بازی انفجار