በመጅሊስ ታሪክ የመጀመሪያው የተባለለት ሰላማዊ የስልጣን ርክክብ ተደረገ

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ታሪክ የመጀመሪያው የተባለለት ሰላማዊ የስልጣን ርክክብ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡ የምክር ቤቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሐጅ ሙሐመድ አሚን ጀማል ኃላፊነታቸውን ለቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ኡመር ኢድሪስ በይፋ አስረክበዋል፡፡

የስልጣን ርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ አዲሱ የኡለማና ባላደራ ቦርድ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት መከናወኑን ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

EBC

The post በመጅሊስ ታሪክ የመጀመሪያው የተባለለት ሰላማዊ የስልጣን ርክክብ ተደረገ appeared first on Satenaw – ሳተናው የዕለቱ ዜናዎች-መረጃ ማግኘት መብትዎ ነው!.

በመጅሊስ ታሪክ የመጀመሪያው የተባለለት ሰላማዊ የስልጣን ርክክብ ተደረገ