በስሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ቃጠሎ የተጠረጠሩ ሰዎች ላይ ክስ ተመሰረተ

በስሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ከአንድ ወር በፊት የተከሰተዉን የእሳት ቃጠሎ ተሳተፉዋል በሚልበተጠረጠሩ አካላት ላይ ክስ መመስረቱን የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የምርመራ ክፍል ሃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ያይኔ አስማማዉ እንዳሉት ተጠርጣሪዎችን በ3 መልኩ ከፍለው እያጣሩ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡

አንደኛ ሃላፊነታቸዉን ያልተወጡ አምስት የሳንቃበርና የአይና ሜዳ እስካዉቶች /የጥበቃ ሰራተኞች በጥርጣሬ ታስረዋል፡፡ ምርመራዉም ወደ ዞን ፍትህ መምሪያ ተልኳል ብለዋል፡፡

ተጠርጣሪዎች የክስ መዝገቡ እስኪጣራ ድረስ በስምንት ሽህ ብር ዋስትና ተፈቅዶላቸዉ ወጥተዋል ነው ያሉት፡፡

ሁለተኛው በልዩ ልዩ መድረኮች ፓርኩን እናቃጥለዋለን እያሉ ሲዝቱ የነበሩ አምስት የግጭ ማህበረሰብ ክፍሎች ተጠርጥረው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ቀሪዎቹ 3ቱ የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸዉ እስካሁን ግን አለመያዛቸዉ ጠቁመዋል፡፡

ሶስተኛዉ የምርመራ ዘርፍ ደግሞ ጥበቃዎቹ እንዲነሱ ትእዛዝ የሰጡት አካላት ሲሆኑ ለምን ትዕዛዝ እንደሰጡና እንዴት ቃጠሎዉ እንደተፈጸመ ምርመራዉ በመጣራት ላይ ነዉ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

እስካሁን ዋናዉን ቃጠሎዉን የፈጸመዉን አካል በዉል ለይተን ማወቅ ባንችልም፤ ምርመራዉ ገደብ የለሽ በመሆኑ ከክልል እስከ ዞን የተዋቀረዉ ቡድን መንስኤዎቹን በየዘርፉ ለይቶ የማጣራት ስራዉን እየተከታተለዉ መሆኑን ተገልጿል፡፡

ምንጭ፤ የሰሜን ጎንድር ዞን ከሚኒኬሽን

The post በስሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ቃጠሎ የተጠረጠሩ ሰዎች ላይ ክስ ተመሰረተ appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.

በስሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ቃጠሎ የተጠረጠሩ ሰዎች ላይ ክስ ተመሰረተ