ጌታቸው አሰፋ ለመቶ ሚሊዮን ህዝብ ወንጀለኛና ገዳይ ነው

ጌታቸው አሰፋን መንግስት በህግ ቁጥጥር ስር ካላዋለ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በመንግስት ላይ ለተቃውሞ መዘጋጀት አለበት። ጌታቸው አሰፋን መንግስት የማያስረው ተሆነ ወንጀለኛው ጌታቸው አሰፋ ሳይሆን ሀገሪቱን እመራታለሁ የሚለው አካል ነው። የመቶ ሚሊዮን ህዝብን መብት የነጠቀ፣ ላለፉት 28 አመታት የበርካታ ኢትዮጵያዊኖችን ህይወት አምክኗል።
ጌታቸው አሰፋ የፈፀማቸው እና ያስፈፀማቸው ወንጀሎች፣
በሰው ልጂ ብልት ውስጥ አቃጣይ በርበሬ እና ጥምጥም ሺቦ በማስገባት፣
የሰውን ልጂ አርቃኑን ዘቅዝቆ እና ገልብጦ በመግረፍ መግደል፣
የሰውን ልጂ በጥልቅ ጉዱጓዲ ውስጥ በማስገባት እንደ ጃርት በጢስ አፍኖ መግዴል፣
የሰውን ልጂ ጥፍር በፔንዛ መንቀል፣
በወንድ ልጂ ብልት ላይ ሃይላንድ ውሃ በማንጠልጠል የዘሬ ፍሬን ማኮላሸት፣
ልጂን አባት ፊት ሚስትን እባል ፊት መዲፈር እና ማስደፈር፣
በጨለማ ክፍል ውስጥ የሰውን ልጂ በብረት ሃዲዲ ላይ እንዲከባለል በማድረግ ማስገደዲ፣ የተንከባለለ ላይ ከባዲ ድብደባ መፈፀም፣ ያልተንከባለለን ወዳው መረሸን፣
ዜጎችን ለረዝም ወራት ከጉንዳን ጋር በማሰር ልዩ የሆነ ቅጣት መቅጣት፣
በሰው ልጂ ገላ ላይ ሲጋራ ማጥፋት እና የሰውን ሎጂ በመፀዳጃ ቤት አርቃኑን ለሰዓታት ማስቀመጥ፣
በመደብደብ ብዛት እራሳቸውን የሳቱ ዜጎችን በሌሊት ወደ ጫካ በመውሰዲ ጥልቅ ውሃ ውስጥ በመጨበር መረጃ እንዲሰጡ ማስገደዲ፣
በዲብደባ ብዛት ለከፋ የአካል ጉዳት እና ለከፍተኛ ህመም የተጋለጡ ዜጎች ህክምና እንዳያገኙ ማገዲ፣
ከእስራት ቢወጡ መረጃ ያወጡብኛል ብሎ የጠረጠራቸውን ዜጎች ወዳው መረሸንና የመሳሰሉት ከባዲ ወንጀሎች በንፁሃን ላይ የፈፀመ አረመኔ የክፋት አባት ነው።
ይህ ግለሰብ የእራሱ የሆነ ማሰቃያ እስር ቤት ያለው ሲሆን ወደ እሱ የማሰቃያ እስር ቤት የተወሰደ ሰው በህይወት መመለስ ፈፅሞ አይቻልም። ወደ እሱ የግል ማሰቃያ እስር ቤት የተወሰዴ ሰው እንደው እደለኛ ነው ከተባለ በቶሎ የተገደለ ነው።
መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ እኔ ስለ ጌታቸው አሰፋ የፃፍኩት ከመቶ ፐርሰንት 25% ወይም የወንጀሉን ሲሶውን ነው። የእሱ ወንጀል መቶ በመቶ ለህዝብ የሚገለጠው በህግ ቁጥጥር የዋለ ቀን ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ መንግስት ይህንን ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር ካላዋለ ወንጀለኛው መንግስት መሆኑን አውቀህ ለተቃውሞ ሠልፍ እንዲትዘጋጂ በአፅንኦት አሳስብሃለሁኝ።
ጌታቸው አሰፋ በአለም አምሳያ የሌለው ከባዲ ወንጀለኛ ነው።

አሰፋ

The post ጌታቸው አሰፋ ለመቶ ሚሊዮን ህዝብ ወንጀለኛና ገዳይ ነው appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.

ጌታቸው አሰፋ ለመቶ ሚሊዮን ህዝብ ወንጀለኛና ገዳይ ነው