ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የኔዘርላንድስ ንግስት ማክስሲማንን ተቀብለው አነጋገሩ

ንግስቷ አካታች የሆነ የፋይናንስ ስርዐት እንዲጎለብት ለሚያደርጉት ጥረት ምስጋና ያቀረቡት ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ አካታች የፋይናንስ ስርዐትን እውን ማድረግ የሚኖረው ፋይዳ በሌሎችም ዘርፎች ላይ በጉልህ የሚንጸባረቅ ነው ብለዋል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ የአካታች ፋይናንስ ልማት አምባሳደርነታቸው በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት ንግስት ማክስሲማን በበኩላቸው ኢትዮጵያ ዘርፉን ለማጎልበት የምታከናውናቸውን ተግባራት ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር መወያየታቸውን ነው የተናገሩት፡፡

አሁንም ግን ውጤታማ የሆነ አካታች የፋይናንስ ስርዐት ለመዘርጋት የሚደረገው ጥረት በተለይም ሴቶችን ያቀፈ ማድረግ እንደሚገባና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ተግባራት በለየ መንገድ መሰራት እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡

ምንጭ :-ፕሬዘዳንት ፅ/ቤት

The post ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የኔዘርላንድስ ንግስት ማክስሲማንን ተቀብለው አነጋገሩ appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የኔዘርላንድስ ንግስት ማክስሲማንን ተቀብለው አነጋገሩ