ኢ/ር ታከለ ኡማ የፊታችን እሑድ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የፅዳት ዘመቻ የመዲናዋ ነዋሪዎች እንዲሳተፍ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ የፊታችን  እሑድ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የፅዳት ዘመቻ መላው የአዲስአበባ ነዋሪ በመሳተፍ የአካባቢውን እና የከተማውን ፅዳት እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።

በተለይም መጪው ጊዜ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከተማዋ ለዘመናት ከነበረባት ውስብስብ ችግር አንፃር ለጎርፍ ተጋላጭ በመሆኗ የፅዳት ዘመቻው መሰል ችግሮችን ለመከላከል የከተማ አስተዳደሩ የሚያደርገው እንቅስቃሴ አካል ነው ብለዋል።

ህብረተሰቡም የጎርፍ መውረጃ ቦዮችን በማፅዳት እና የውሀ መተላለፊያዎች ላይ ቆሻሻ ባለመጣል የበኩሉን እንዲወጣ ኢንጂነር ታከለ ጥሪ አቅርበዋል።

የክፍለ ከተማ እና የሴክተር ሃላፊዎች በበኩላቸው የፅዳት ዘመቻውን በ116ቱም ወረዳዎች ለማካሄድ ዝግጅት አጠናቀዋል ነው ያሉት።

በፅዳት ዘመቻው የወጣት ማህበራት፣ መምህራን፣ የቅዱስጊዩርጊስ እና ቡና  ክለቦች እንዲሁም የጉዞ አድዋ ተጓዦችን ጨምሮ ሌሎች የመዲናዋ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉ መሆኑን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

 

 

ኢ/ር ታከለ ኡማ የፊታችን እሑድ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የፅዳት ዘመቻ የመዲናዋ ነዋሪዎች እንዲሳተፍ ጥሪ አቀረቡ