ከገባንበት የፖለቲካ አጣብቂኝ እንዴት እንላቀቅ!! (አንዷለም አራጌ)

“”እስከ ዞንና ወረዳ በዘለቀ መልኩ ውይይት በማድረግ አገሪቱ ከገባችበት አጣብቂኝ እንድትወጣ ማድረግ ይቻላል ብየ አምናለሁ። ይህንን ማድረግ ባለመቻላችን ለውጡ ባለበት ቆሟል””

አቶ አንዷለም አራጌ የኢዜማ ምክትል መሪ።
-=-

በአፍሪካ የምጣኔሀብት ኮሚሽን ፅ/ቤት አዳራሽ በጠቅላይ ሚንስትሩ ፅ/ቤት አዘጋጅነት ለአምስተኛ ጊዜ ዛሬ በተደረገው ውይይት ላይ ነው አቶ አንዷለም አራጌ ያዘጋጁትን የጥናት ወረቀት ሲያቀርቡ ይህንን የተናገሩት።
-=-=-

ውይይት ማድረጉ መልካም ነው። ከአሁን በዃላ በውይይት ብቻ የሚፈታ ችግር ይኖራል ብየ ግን አላምንም። ችግሩ ሊፈታ የሚችለው ተገቢና የማያዳግም ፍትሀዊ ውሳኔ በመስጠት ብቻ ነው።
-=-=-

ውሳኔ አንድ:
-=-=-=-=-=-

በባንቱስታኒስትና አፓርታይዲዝም ቀመር ህወሐትና ኦነግ በሳሉት ካርቶግራፊ ላይ ተመስርቶ በ2/3 ኛው የሀገሪቱ ህዝብ ጉሮሮ ላይ የቆመውን ፌዴራሊዝም አፍርሶ ፍትሀዊ የሆነና ለአስተዳደር የሚበጅ የፌደራል ስርዓት መመስረት።
-=-

ውሳኔ ሁለት፡
-=-=-=-=-=-

2/3 ኛውን የሃገሪቱ ህዝብ ባገለለ መልኩ በህወሐት እና ኦነግ የተደረሰውን “ህገ መንግስት” ቀዳዶ በመጣል ሁሉም ዜጎች በእኩልነት ተወክለው የተሳተፉበት እና አርቅቀው ያፀደቁት ህገ መንግስት ማዘጋጀት።

ይሄው ነው።
-=-=-

ከዚህ ውጭ ያለው ውይይትና እስከአምስት ሚሊዮን ብር የወጣበት የእራት ግብዣ ያለፈውን ፋሽስት የህወሐት ቅኝ ግዛታዊ ስርዓት ለማስቀጠል የሚደረግ ከንቱ ድካም ነው።
-=-=-

ጠቅላይ ሚንስትሩ በተደጋጋሚ እንደገለጡት ያሳለፍነው 27 አመት በኢትዮጵያ ሃገራዊ ነባራዊነት በጨለማ ዘመንነቱ በታሪክ የሚመዘገብ አሳዛኝ ክስተት ነው።
-=-=-

ከጨላማው ዘመን መላቀቅ የሚቻለው ደግሞ የጨለማውን ዘመን ታሪክ ከነጨለማው አዳፍኖ አዲስ ታሪካዊ የብርሀን ዘመንን በመሻት ነው።
-=-=-

ፌደራሊዝሙን አፍርሶ አዲስ ህገመንግስት ማፅደቅ ለምንመኘው የብርሃን ዘመን ያለምንም ቅደመሁኔታዎች ሊተገበር የሚገባው የመጀመሪያ ስራ ነው።
-=-=-

ከዚህ ውጭ ያለው ከንቱ ድካም እኔን እስከሚገባኝ ድረስ የራሱን የወደፊት ዕጣ ፋንታ በዕራሱ እጆች ለመፃፍ ቆርጦ የተነሳውን የአማራ ብሄርተኝነት ለማሰናከልና ለማዘናጋት የታለመ እኩይ ሴራ ነው።
-=-=-

The post ከገባንበት የፖለቲካ አጣብቂኝ እንዴት እንላቀቅ!! (አንዷለም አራጌ) appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.

ከገባንበት የፖለቲካ አጣብቂኝ እንዴት እንላቀቅ!! (አንዷለም አራጌ)