የአጼ ምኒልክ ሕዝባቸውን ይጋብዙበት የነበረው የግብር አዳራሽ

ይህ  የምንመለከተው አጼ ምኒልክ ሕዝባቸውን ይጋብዙበት የነበረው የግብር አዳራሽን ነው። በአጼ ምኒልክ ዘመን በዚህ አዳራሽ ውስጥ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በየቀኑ 3ሺህ ሰው እየገባ ሲመገብ እሁድ እሁድ ደግሞ ከሌላው ቀን ላይ 1ሺህ ተጨምሮ 4ሺህ ሰው ገብቶ ከምግቡ ይሳተፍ ነበር።

አጼ ምኒልክ ግብዣ በሚያደርጉበት ወቅት ሁሌም ቢሆን ምገባው የሚጀምረው ከጥበቃዎች ነበር። ከእነሱ ቀጥለው ቄሶች ከቄሶቹ በመቀጠል መንገደኞች እነሱን ተከትሎ ነጋዴዎች ከዚያም ሕዝቡ እየገባ ይመገባል ለእያንዳንዱም ሰው አንድ እንጀራ፣ አንድ ትልቅ ጭልፋ ቀይ ወጥ እና ሙዳ ሥጋ ከአንድ ኩባያ ጠጅ ጋር ይቀርብለታል።

ያ ሁሉ ሕዝብ ተመግቦ ሲያበቃ ጠብቀው አጼ ምኒልክ በተራቸው መኳንንቷቻቸውን ይዘው ገብተው ይመገቡ ነበር። አጼ ምኒልክ ይህን ልማዳቸውን የትም ቢሆን ዘንግተውት አይውቁም መኳንንቶቻቸው ቤት ተጋብዘው ሲሄዱ እንኳን ቅድምያ የበታቾቻቸው በልተው ሳይጠግቡ እርሳቸው ምንም እህል አይቀምሱም ነበር ። ለዚህም ደግነት ሕዝቡ እንዲህ ብሎ ገጠሞ ነበር
“ቀድሞም ጠቢብ ነበር ሰለሞን ባባቱ
ምኒልክ በለጠ ሰው ይዞ መብላቱ ”

እንግዲህ ይህ የአጼ ምኒልክ የግብር አዳራሽ አሁን ላይ በዶ/ር አብይ የአስተዳደር ዘመን ታድሶ ዛሬ የመጀመሪያውን ግብዣ አምስት ሚሊዮን ከከፈሉት እንደሚጀምር ተሰምቷል።

United state of Ethiopia .

The post የአጼ ምኒልክ ሕዝባቸውን ይጋብዙበት የነበረው የግብር አዳራሽ appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.

የአጼ ምኒልክ ሕዝባቸውን ይጋብዙበት የነበረው የግብር አዳራሽ