“በትግራይ የፖለቲካ ሥርዓት ለውጥ የሚመጣው የትግራይን ሕዝብ ጥቅምና መብቶችን መሠረት አድርጎ ከራሱ ከትግራይ ሕዝብ ውስጥ ሲመነጭ ነው

“ከትግራይ ውጭ ባሉ ኃይሎች የሥልጣንና የገንዘብ ማባበያነት በተፅዕኖ የሚመጣን “ለውጥ” ግን የትግራይ ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ ሊቃወም ይገባል፡፡” 3ቱ ጄኔራሎች

“በትግራይ የፖለቲካ ሥርዓት ለውጥ የሚመጣው የትግራይን ሕዝብ ጥቅምና መብቶችን መሠረት አድርጎ፣ ከራሱ ከትግራይ ሕዝብ ውስጥ ሲመነጭ ነው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ከተለያዩ አቅጣጫዎች በገንዘብና በሥልጣን ኃይል፣ ከራሱ ከሕዝቡ ያልበቀለና በሕዝቡ ተቀባይነት የሌለው “ለውጥ” በሕዝቡ ላይ ለመጫን የሚደረግ ሙከራ እንዳለ ይሰማል፡፡ ይህ በትግራይ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንደማይኖረው እንተማመናለን፡፡ ቀደም ብሎ እንደተገለጸው ትግራይ ውስጥ ፖለቲካዊ ችግሮች አሉ፡፡ እነዚህን ፖለቲካዊ ችግሮች በውስጣችን ታግለን እንፈታቸዋለን፡፡ ከትግራይ ውጭ ባሉ ኃይሎች የሥልጣንና የገንዘብ ማባበያነት በተፅዕኖ የሚመጣን “ለውጥ” ግን የትግራይ ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ ሊቃወም ይገባል፡፡ ምክንያቱም ከሕዝብ ውስጥ የማይመጣና ከውጭ በተፅዕኖ የሚመጣ ለውጥና ይህንን እናሳካለን የሚሉ “የለውጥ” ደላላዎች ሁሉ፣ ከሁኔታዎች ጋራ በመለዋወጥ ቀጣይ አደጋ ውስጥ ስለሚከቱን ነው፡፡ ችግሮቻችንን አይፈቱም፡፡ ይልቁንስ ይበልጥ ያባብሱታል፡፡ ለተጨማሪ የተወሳሰበ ችግር ያጋልጡናል፡፡ ስለዚህ የፖለቲካ ሕይወታችንን ራሳችን መቆጣጠር ይኖርብናል፡፡ ከየትኛውም አቅጣጫ በሥልጣን ሆነ በገንዘብ አማካይነት ለውጥ አመጣለሁ የሚል ኃይል ነገ ገንዘቡን ወይም ሥልጣኑን የሚሰጠው ኃይል ሲጠፋ ለሌላ ጌታ ያድራል፡፡ ጌታው እስካለ ድረስ ደግሞ የጌታውን በሽታ በሙሉ ይዞልን ይመጣል፡፡ ኪሳራው ከባድ ነው፡፡ በፅናት እንቃወመው፡”

ፀሃፊዎቹ፡ ሌ/ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳዔ ፣ ብ/ጄኔራል ታደሰ በርሄ እና ብ/ጄኔራል መስፍን አማረ

ናሁሰናይ በላይ

The post “በትግራይ የፖለቲካ ሥርዓት ለውጥ የሚመጣው የትግራይን ሕዝብ ጥቅምና መብቶችን መሠረት አድርጎ ከራሱ ከትግራይ ሕዝብ ውስጥ ሲመነጭ ነው appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.

“በትግራይ የፖለቲካ ሥርዓት ለውጥ የሚመጣው የትግራይን ሕዝብ ጥቅምና መብቶችን መሠረት አድርጎ ከራሱ ከትግራይ ሕዝብ ውስጥ ሲመነጭ ነው