ስንሰባሰብ፣ አንድ ስንሆን የሚኖረን ውበት ስንነጣጠል አይኖረንም – ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ

በንግግራቸው ሙስሊሙ ማህበረሰብ በአንድነት ሲያፈጥር በመመልከታቸው ደስታ አንደተሰማቸው ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ ሙስሊሞችን ማገልገል የሚችል እስላማዊ ባንክ እንዲቋቋም መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቀ፡፡

የረመዳን ወር በፆም ስናሳልፍ በፍቅር፣ በአንድነት በቅንነት ሊሆን እንደሚገባ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕከት የተናገሩት፡፡

የረመዳን ወር ከውሸት እና ከማሳበቅ በመራቅ ፍሬያማ ፆም ማድረግ እንደሚገባ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሙስሊሙ አንድነትና ሰላም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይጠቅማል ብለዋል፡፡

የረመዳን ጾም ሊጠናቀቅ አንድ ቀን ሲቀረው በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች የመስገጃ ቦታዎችን እና መስጊዶችን ለማፅዳት ተዘጋጅተዋል ነው ያሉት፡፡

የሙስሉሙ ማህበረሰብም ዕለቱን ያላቸውን ለሌላቸው በማካፈል እንደሚያሳልፉት እምነቴ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በጀማ የሚሰግድበት እና የመላው አለም ሙስሊሞችንም ትኩረት የሚስብ መስጊድ ለመገንባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ባረቡት ጥያቄ መሰረት መንግስት ድጋፍ ዝግጁ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

በዚህ ግንባታ እንደ ነጃሺ መስጊድ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንደነበራቸው ተሳትፎ በዚህኛው ግንባታም መላው የኢትዮጵያ የክርስቲያኖች ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀርበዋል፡፡

የሙስሊሙ ማህበረሰብ 4 ቢሊየን የዛፍ ችግኞችን ለመትከል ከአንድ ወር በኋላ በሚደረገው ሀገር አቀፍ ዘመቻ ንቁ ተሳታፊ አንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በኤፍሬም ምትኩ

ስንሰባሰብ፣ አንድ ስንሆን የሚኖረን ውበት ስንነጣጠል አይኖረንም – ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ