ቦይንግ ለፓይለቶች አስተያየት ትኩረት ቢሰጥ ኖሮ በኢትዮጵያ የደረሰውን አደጋ ማስቀረት ይቻል እንደነበር የአብራሪዎች ማኅበር አስታወቀ

ቦይንግ ኩባንያ በአውሮፕላኑ ደህንነት ዙሪያ አብራሪዎች ያቀረቡትን የደህንነት ስጋት ቢያዳምጥ ኖሮ የደረሱት ሁለት ከባድ የበረራ አደጋዎች አይከሰቱም ነበር ሲል የአሜሪካ አየር መንገድ የአብራሪዎች ማኅበር አስታውቋል።

በቅርቡ በአውሮፕላኖቹ የአብራሪ ክፍሎ የተቀረጹ እና አብራሪዎች በአውሮፕላኖቹ ደህንነት ላይ ያለውን ችግር ሲወያዩ የተቀረጸው ድምፅ ከወጣ ወዲህ ቦይንግ ላይ የሚደረገው ጫና እየበረታ መጥቷል፡፡

የቦይንግ የሶፍትዌር ችግርን በተመለከተ የአሜሪካ አየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪዎች ከኩባንያው ጋር በህዳር 2017 ባደረጉት ስብሰባ ስጋታቸውን ገልፀው እንደነበር አስታውሰዋል።

ስብሰባው የተካሄደው የላየን ኤር አደጋ ከተከሰተ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ከመከሰቱ ከጥቂት ወራት በፊት ነበር።

ቦይንግ በማህበሩ ውሳኔ ላይ ምንም አስተያየት እንዳልሰጠ ነው የተገለፀው።

ምንጭ: -ሲኤንኤን

The post ቦይንግ ለፓይለቶች አስተያየት ትኩረት ቢሰጥ ኖሮ በኢትዮጵያ የደረሰውን አደጋ ማስቀረት ይቻል እንደነበር የአብራሪዎች ማኅበር አስታወቀ appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.

ቦይንግ ለፓይለቶች አስተያየት ትኩረት ቢሰጥ ኖሮ በኢትዮጵያ የደረሰውን አደጋ ማስቀረት ይቻል እንደነበር የአብራሪዎች ማኅበር አስታወቀ