የተወዛገቡ አክቲቪስቶች ለችግሮቻችን መፍትሔ ከመፈለግና ስለመፍትሔ ከመመካከር ይልቅ በብሽሽቅ ፖለቲካ ታጅበው ብሽቆች ሆነዋል

ፖለቲካችን ብስለት ይጎለዋል።የተወዛገቡ አክቲቪስቶች ለችግሮቻችን መፍትሔ ከመፈለግና ስለመፍትሔ ከመመካከር ይልቅ በብሽሽቅ ፖለቲካ ታጅበው ብሽቆች ሆነዋል።አክቲቪስትነት በገንዘብ አይሸጥም አይለወጥም። አክቲቪስትነት የገቢ ምንጭ አይደለም። አክቲቪስትነት ዘረኝነት አይደለም። አክቲቪስትነት በፖለቲካ መነቋቆርና መበሻሽቅ አይደለም። አክቲቪስትነት ስለሰው ልጆች መቆምና መቆርቆር ነው።አክቲቪስት ማለት የመቻቻልና የመፍትሔ ሰራተኛ ነው።

አንዱ ተነስቶ እነ እንትና ሊታፈሱ ሊታሰሩ ሊገደሉ ሊታፈኑ ነው ሲል ሌላው ተነስቶ ሰርግ ላይ የተተኮሰ ጥይት ቪዲዮ ይለቃል። ሌላው ብድግ ይልና አካኪ ዘራፍ ይላል ሌላው ተነስቶ ፌክ ደብዳቤዎችን ያከፋፍላል። ምን ያህል የወረድን እንደሆነ ማሳያችን መስታወታችን ማሕበራዊ ሚዲያ ነው። አክቲቪስት በፌክ መረጃዎች ታጥሮ አይወዛገብም።

አንዱ ተነስቶ የራሱን ሃይማኖት እያቆለጳጰሰ ካለሱ ሰው ያለ ካለሱ ሃይማኖት እውነት ያለ አይመስለውም። የሌላውን ሲያናንቅ እና ራሱን ሲያሰለጥን ስለ መቻቻልና ስለ መከባበር ሃይማኖቱ ውስጥ ትምሕርት የሌለ እስከሚመስል እንደ አሕያ ሲያናፋ ይውላል። አክቲቪስት በፌክ መረጃዎች ታጥሮ አይወዛገብም።

ሌላው ሳትጠይቀው ሲቀባጥር ይውላል አንዲት ነገር ለሕዝብ እና ለሃገር ሳያበረክት የተግባር ሰዎችን ሲተችና ሲሳደብ ይውላል። ሌላው አፉን ቂቤ አድርጎ ሴራ ሲጎነጉን ይውላል። ይህን እና ሌሎች ተጨማሪ የማይረቡ ጉዶችን የምናየው በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ ነው። አንዳቸንም ስለመፍትሔ እና ስለ ጠቋሚ መፍትሔዎች ሃሳብ ማመንጨት ሳይሆን ፍንጭ ለመስጠት አንፈልግም።አክቲቪስት ማለት የመቻቻልና የመፍትሔ ሰራተኛ ነው። በሃሳብ ማእድ ዙሪያ ተሰባስቦ መፍትሔ ለመፍጠር የምንተጋ ያድርገን።

#MinilikSalsawi

The post የተወዛገቡ አክቲቪስቶች ለችግሮቻችን መፍትሔ ከመፈለግና ስለመፍትሔ ከመመካከር ይልቅ በብሽሽቅ ፖለቲካ ታጅበው ብሽቆች ሆነዋል appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.

የተወዛገቡ አክቲቪስቶች ለችግሮቻችን መፍትሔ ከመፈለግና ስለመፍትሔ ከመመካከር ይልቅ በብሽሽቅ ፖለቲካ ታጅበው ብሽቆች ሆነዋል