የታክሲ አሸከርካሪውን አርደው በማምለጥ ላይ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።  (በተሻገር ጣሰው)

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ስሙ ካዲስኮ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቀን 13/9/2011 ዓ/ኝ ምሽት 12:30 ገዳማ ኮድ1 35555 አአ የሆነ የስታር ሜትር ታክሲ አሽከርካሪውን አርደው ለማምለጥ ላይ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች እንደገለፁት የታክሲው አሽከርካሪን አንገቱን ታርዶ ወዲያውኑ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን ድርጊቱን የፈጸሙ ግለሰቦች በመኪናው ለማምለጥ ሲሞክሩ በተለምዶ ኩርባ ተብሎ በሚጠራው መንገድሲያቋርጡ ከቆመ ኖቤድ መኪና ጋር ተጋጭተዋል።

በግጭቱ አንዱ ተጠርጣሪ እግሩ የተቆረጠ ሲሆን ሌላው ሩጦ ለምምለጥ ሲሞክር ሳሪስ አዲስ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመኪና ጥበቃ ስራ ላይ የነበረ ግለሰብ አሯሩጦ ሊይዘው ችሏል።

በአሁኑ ሰዓት ተጠርጣሪውቹ ሳሪስ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር ውለው በምርመራ ላይ ይገኛሉ።

The post የታክሲ አሸከርካሪውን አርደው በማምለጥ ላይ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።  (በተሻገር ጣሰው) appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.

የታክሲ አሸከርካሪውን አርደው በማምለጥ ላይ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።  (በተሻገር ጣሰው)