ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የማዕከላዊ ምክርቤት ፲፩ኛ መደበኛ ስብሰባ የአቋም መግለጫ

 ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
ዐርብ ግንቦት ፳፫  ቀን ፪ሺህ፲፩ዓ.ም.    ቅጽ ፯ቁጥር ፲
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የማዕከላዊ ምክርቤት ፲፩ኛ መደበኛ ስብሰባ
የአቋም መግለጫ

እኛ የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት (ሞወዐድ) ማዕከላዊ ምክር ቤት አባላት፣ በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የማዕከላዊ ምክር ቤቱን  ፲፩ኛ (11ኛ)መደበኛ ስብሰባ ቅዳሜ ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ሽ፲፩ ዓ.ም. (Saturday May 25, 2019) አድርገናል። ስብሰባው የተከፈተው ባለፉት 28 ዓመታት በግፍ የተጨፈጨፉትን ዐማራ ወገኖቻችንን በማስታወስ የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት በማድረግ ነበር። በመርሐ-ግብሩ መሠረት፤ የሞወዐድ ሥራ አስፈጻሚኮሚቴ ያቀረበውን የ6 ወራት የሥራ እንቅስቃሴ  ሪፖርት በሰፊው ተወያይተን አስፈላጊ ማስተካከያዎችና ጭማሪዎች አድርገን ሪፖርቱ የድርጅቱ ቋሚ ሰነድ ሆኖ እንዲያዝ አጽድቀናል፡፡ ቀጥሎም፣ የድርጅታችን የፋይናንስ መምሪያ የሂሳብ አያያዝ ዘገባ እና የልዩ ልዩ መምሪያዎች ሪፖርቶች ቀርበው ተወያይተናል። ከዚህም በላይ፣ የሚቀጥለው 6 ወር የሥራ እቅድ ላይ በጥልቀት ተወያይተን የሥራ እቅዱን እንዳለ ተቀብለነዋል። በመጨረሻም፣ በወቅታዊ የአገራችን አሳሳቢ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዩች ላይ ስፊ ጊዜ ወስደን በዝርዝር ከተወያየን በኋላ ይህን የአቋም መግለጫ አውጥተናል።

 

  1. ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት፣ የዐማራን ነገድ ከፈጽሞ ጥፋት የመታደግና ድምፅ አልባ ለሆነው ዐማራ ድምፅ ለመሆን ለቆመለት ዓላማ ስኬት ዕውን መሆን፣ የዐማራው ድምፅ ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ እንዲያስተጋባ፣ የዓለም ማኅበረሰብ በዝምታ፣ የነገዱ ምሁራን ደግሞ በቸልታ የሚመለከቱት የዘር ጥፋትና የዘር ጽዳት ወንጀል እንዲቆም፣ ወንጀለኞች ለፍትሕ እንዲቀርቡ እገዛና ድምፅ የሚሆን «ዐማራ ድምጽ ራዲዮ (ዐድራ) የተሰኘ የራዲዮ ጣቢያ ላለፉት ሶስት ዓመታት  ሳይቋረጥ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ይህ የራዲዮ ጣቢያ  በቅርቡ በአገራችን በተፈጠረው አንጻራዊ ሁኔታዎች በመጠቀም ወደ አገር ቤት ገብቶ ለዐማራው ወገኖቻችን ብሎም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተጨማሪ አማራጭ የመረጃ ምንጭ ከመሆን ባሻገር፣ ድምፁ ለታፈነው የዐማራው ነገድ ልሣን እና አንደበት እንዲሆን በማሰብ ድርጅታችን ሕዝብን ለማንቂያ፣ ለማስተማሪያ፣ ለማሳወቂያና ለማደራጃነት  ጅምር ጉልህ ሚና በመጫዎት ላለፉት ሶስት ወራት “ዐማራ ሚዲያ መዕከል” (Amara Media Center) “ በሚል ስያሜ ኢንተርኔት ቲቪ ከአገር ቤት መላውን ዓለም እየደረሰ ከፍተኛ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በዚሁ አኳያ፣ የ “ዐማራ ሚዲያ መዕከል” (Amara Media Center) ቁመና ተጠናክሮ በሳትላይት አማካኝነት በኢትዮጵያ አንዲሰራጭ ሆኖ የሚያድግበትን መንገድ ዳር ለማድረስ ቆራጥ እርምጃ ለመውሰድ ቃል እንገባለን።
  2.  ዐማራውን የማደራጀት፣ የማንቃትና አንድ ሕዝብ ታሪኩን፣ ባሕሉን፣ ቅርሱ፣ ኃይማኖቱንና ማንነቱን አስጠብቆ ለተከታታይ ትውልድ ማሸጋገር የሚችለው፣ የእርሱ ተቃራኒ ከሆኑ የጥፋት ኃይሎች ራሱን መጠበቅና መከላከል ሲችል እንደሆነ ይታመናል። ለዚህም ዋናው ሥራ ትውልዱ አኩሪ ታሪኩን፤ ባህሉን፣ ቋንቋውን፣ ሃይማኖቱን፣ ፣ ዕሴቶቹን፣ በአጠቃላይ ማንነቱን በቅጡ እንዲያውቅ ሲደረግ ነው። ትውልዱ ወዳጅና ጠላቱን የሚለይበት፣ ከተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር የተጣጣመ የታሪክ ግንዛቤ በተከታታይ እንዲቋጥር መሠረታዊ ዕውቀት ሊጨብጥ ይገባዋል። በተለይም ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ዐማራ የሆኑ ቡድኖችና ግለሰቦች ዐማራውን ታሪኩንና ማንነቱን ጥላሸት ከመቀባት አልፈው፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል እየተፈጸመበት የሚገኝ መሆኑን ዓለም ያወቀው ገሃድ ሃቅ ነው። በዛሬው ዘመን ግን የዐማራው ነገድ ትውልድ ዕውነታውን ባለማወቁ በአባቶቹ ማንነትና ታሪክ ከማፈር ወጥቶ፣ እንዲሸማቀቅና ከማንነቱ የመራቅ አዝማሚያ እንዲያሳይ የጣለብትን መረብ በመበጣጠስ ላይ እንዳለ እየተስተዋለ ነው። ይህን በሚመለከት ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት አጥብቆ ከተዋጋቸው ጉዳዮች አንዱና ዋናው በመሆኑ፣ የዐማራው ወጣት ትውልድ በአባቶቹ ማንነትና ታሪክ የሚመካና የሚኮራ እንዲሆን፣ ይህንም አስጠብቆ ለትውልድ እንዲያሸጋግር፣ የዐማራውን ማንነት፣ ታሪክና ለኢትዮጵያውነት የከፈለውን መስዋዕትነት ባላቀ ደረጃ በከፍተኛ ስትራቴጂና ታክቲክ የዐማራው ትግል እንዲቀጥል ለዐማራው ነገድ አባሎች በእውቀትና እውነት ላይ በተመሰረቱ ቀስቃሽ መግለጫዎችን እና ጥናታዊ ጽሑፎችን በማሰራጨት፣ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ዐማራው በመረጃ የታገዘና የተጠናከረ ትግሉን እንዲያፋፍም የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁነታችን እናረጋግጣለን።

 

  1. ምክር ቤቱ  ዐማራው የገጠመውን ችግሮች፣ በአንክሮ መርምሯል። በመሆኑም ዐማራውም መስቀለኛ መንገድ ላይ ሆኖ ፊት ለፊቱ አፍጦ የሚያዬውን ፍጅትና እልቂት መላ ለማለት ትውልዳዊ የቤት ስራውን ለማጠናቀቅ በእልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ መጠመዱንም ተገንዝቧል ።የዐማራው ተጋድሎ በግንባር ቀደምትነት ያነሳቸው የዐማራ ኅልውና እና ማንነት ጥያቄዎች ያለተመለሱና ግባቸውን ያልመቱ ስለሆነ፤ ፀረ-ዐማራ ኃይሎች ይኸን ሕዝባዊ ትግሉ ለማዳፈን በየአቅጣጫው በመሯሯጥ ላይ ስለሆኑ በይበልጥ ትግሉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እናሳስባለን።
  2. የዐማራው ሕዝብ አጽመ-ርስት የሆኑት መተከል፣ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት እና ራያ ለማስመለስ ሕዝባችን ትግሉን በቆራጥነት እንዲያጧጥፍ የትግል ጥሪ እናቀርባለን፤ እኛም የበኩላችንን የትግል ድርሻችንን እናበረክታለን።
  3. የተበታተኑት የዐማራ ድርጅቶች ወደ አንድ አሰባሳቢ ማዕከል በመሰባሰብ ከፍተኛ የሕዝብ መሠረት ያላቸው ቆራጥ፣ ታግለው የሚያታግሉ፣ የዐማራ መሪ ድርጅቶች እንዲቋቁሙ፤ እንዲሁም የተለያዩት የዐማራ ሚዲያዎች ተናበው እንዲሰሩ የትግል ጥሪያችንን እናቀርብን። ከተቋቋመ አንድ ዓመት ያልሞላው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የዐማራውን የኅልውና እና የማንነት ጥያቄዎችን፣ ዐማራው ባልፉት 28 ዓመታት የደረስብትን የዘር ማጽዳትና የዘር ጭፍጨፋ፣ እንዲሁም የደረሰበትን ከፍተኛ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ድቀት፣ የስነ-ልቦና ስብራት በግንባር ቀደምትነት በአገራችን መሬት ላይ በመጀመሪያው ረድፍ በመሰለፍ በየአቅጣጫው የተከፈተበትን የፕሮፖጋናዳ ጦርነት፣ በየትግሉ መንገድ የተዘረጋበትን አሻጥርና ተንኮል እየተቋቋመ ለዐማራው ወገናችን ያደረገው እና በማደረግ ላይ ያለውን ተጋድሎ እያደነቅንና እያበረታታን፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለማገዝ ከጎኑ የተሰልፍን መሆኑን ቃል እየገባን የትግል አጋርነታችንን እናረጋግጣለን።
  4. ለ28 ዓመታት ዐማራ ሕዝባችንን የምድር ገሃነብ እና ሲኦል ሕይወት እንዲኖር የዘር ማጽዳት  (Ethnic Cleansing)  እና የዘር ጭፍጨፋ(Genocide)  በመፈጸም ወደ 5.5 ሚሊዮን ዐማራ የጨፈጭፉ የትግሬ-ወያኔዎች እና የእነርሱ ተባባሪ ባንዳ ወንጀለኞች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ፤ የዐማራው ሕዝብ ለደረሰበት የዘር ማጽዳት እና የዘር ጭፍጨፋ የዶ/ር አብይ አሕመድ መንግሥት ካሳ እንዲከፍልና በይፋ በዐማራው ሕዝብ ላይ የዘር ማጽዳት እና የዘር ጭፍጭፋ እንደተካሄደበት ይፋዊ እውቅና እንዲሰጥ አጥብቀን እንጠይቃለን።
  5. ለ28 ዓመታት በተለያዩት የኢትዮጵያ ክፍሎች አሁን በቅርቡ ደግሞ በአጣየ፣ በከሚሴ፣ በራያ፣ በጎንደር፣ በቤንሻንጉል እና ጉሙዝ፣ በአዲስ አበባና አጎራባች ከተማዎች፣ በጅማ፣ በወለጋ፣ በሐረር እንዲሁም በሌሎች ቦታዎች በዘራቸው እየተለዩ ለብዙ ዓመታት ከኖሩበት ቦታ ቤት ንበረታቸው እየፈረሰና እየተቃጠለ እንዲሁም በገጀራና በቀስት እየተገደሉ ለሚፈናቀሉት ዐማራ ወገኖቻችን በዶ/ር አብይ አሕመድ የሚመራው የኢህአዴግ መንግሥት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈልግለት እና ለሟች ቤተስቦች ካሳ እንዲሁም ቤት ንብረታቸው ለወደመባቸው አስፈላጊው የኑሮ መቋቋሚያ እንዲደረግላቸው እንጠይቃለን።
  6. ዐማራው ሕዝባችን ተወካይ እንዳይኖረው ተደርጎ በከፍተኛ ሴራ በተገገለለበት ሁኔታ አጽመ-ርስት መሪቶቹን ተቀምቶ የተከለለበት አከላለል፤ ያለተወከለበት ሕገ-መንግሥት እና የሳጥናኤል መገላጫ የሆነውን አርማ ያዘለው ፀረ-ክርስቲያንና ፀረ-እስላም የወያኔ ሰንደቅ-ዓላማ የዐማራ ሕዝባችን የማይቀበለውና የሚያወግዘው መሆኑን እናሳውቃለን። እንዲሁም፤ ፀረ-ኢትዮጵያ እና ፀረ-ዐማራ የሆነው የትግሬ-ወያኔ እና ኦነግ ያረቀቁት አሁን በስራ ላይ ያለው ሕገ-መንግሥት እስካልተወገደ ድረስ፤ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ለማየት የማይቻል መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።
  7. አሁን በቅርቡ በምስራቅ ጎጃም ብቸና ከተማ ላይ የሙስሊም ዐማራ ወገኖቻችን ለአምልኮት በሚገለገሉበት በተቀደሰው መስጊድ ላይ የደረስውን ጥቃት አጥብቀን እናወግዛለን። ይኸም ሆን ተበሎ የዐማራን ሕዝብ በሃይማኖት ለመከፋፈል  ፀረ-ዐማራ ኃይሎች የሚደርጉት ተንኮል መሆኑን መላው ዐማራ እንዲገነዘበው እያሳሰብን፤ “አንድ ዐማራ ለሁሉም ዐማራ፣ ሁሉም ዐማራ ለአንድ ዐማራ” በሚለው የዐማራ ሕዝብ የትግል ትብብር ጥሪ መሠረት፤ በአካባቢው የምትኖሩ ከርስቲያን ዐማራዎች የትግል አጋር ወንድሞቻችሁን መስጊድ ወደነበረበት ይዞታና ሁኔታ በመመለስ  የተለመደውን አገልግሎት እንዲሰጥ አስፈላጊውን ትብብርና እርዳታ እንድታደርጉ በዐማራው ወገናች ስም አጥብቀን እንጠይቃለን።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
ቅዳሜግንቦት፲፭ቀን፪ሺ፲፩ዓ.ም
Saturday, May 25, 2019
Attachments area

The post  ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የማዕከላዊ ምክርቤት ፲፩ኛ መደበኛ ስብሰባ የአቋም መግለጫ appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.

 ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የማዕከላዊ ምክርቤት ፲፩ኛ መደበኛ ስብሰባ የአቋም መግለጫ