Menu

በድሉ ህንጻ

ከ 1950 ዎቹ አጋማሽ አንስቶ ይስሩ የነበሩ ህንጻዋች በዘመናዊው የኢትዮጵያ የህንጻ አርክቴክቸር ታሪክ ቅድሚያ የሚስጣቸው ነው፤ ይህ ህንጻ ንብረትነቱ የቀኝ አዝማች ይልማ በድሉ ነበር፤ የህንጻውንም ስያሜ ያደረጉት በአባታቸው በ አቶ በድሉ ነው ፤ ጃንሆይ በህንጻው ውበት በመደነቃቸው ለ ይልማ በድሉ የቀኝ አዝማች ማዕረግም ስጥተዋቸዋል ።

ከዚህ ህንጻ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ብዙ ታሪኮች አሉ:: ደቡብ አፍሪዊቷ አቀንቃኝ ማሪያ ማኬባ በአንድ ወቅት ወደ ኢትዮጵያ ብቅ ትላለች ፤ ማሪያ ማኬባ ” ሜሪ አርምዴ የምትባል እንዳንቺ ያለች ጎበዝ ድምጻዊት አለች “ስትባል ሜሪ አርምዴን ካላገኘሁ ብላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፓሮቶኮል ስዎችን ታስቸግራለች ።

የውጭ ጉዳይ ሰዎችም እንግዳዋን ወደ ሜሪ ቤት ከመውስዳቸው በፊት የቤቷን ሁኔታ ለማየት ሜሪ ወደ እምትኖርበት ቤት ሲሄዱ ባዩት ነገር እጅግ ደነገጡ በወቅቱ ሜሪ በድህነት ነበር የምትኖረው ።

የውጭ ጉዳይ ስዎቹም “ማኬባ እዚህ አትመጣም ማኬባ ሜሪን በዚህች ቤት ውስጥ ሆና ብታያት ለገጽታችን ጥሩ አይደለም ስለዚህ ሌላ አማራጭ እንጠቀም ” ብለው ሜሪን በድሉ ህንጻ ውስጥ አስገብተው የሚያስፈልጉ ነገሮች ሁሉ በመንግስት እንዲሟሉ ተደርጎ ሜሪ ልክ እቤቷ ውስጥ እንዳለች ሆና እንግዳዋን ጋብዛ የሸኘችው በዚሁ በድሉ ህንጻ ላይ ነው።
የበድሉ ህንጻ አርክቴክት ኢጣሊያዊው Henri Chalmette ናቸው ፤ ሄንሪ ባንኮ ዲ ሮማ ህንጻንና የንግድ ባንክ ክቡን ህንጻንም ዲዛይን ያደረጉት እሳቸው ናቸው ።

በአሁን ስአት የህንጻው ግርማ ሞገስ ከአጠገቡ በተስራው የመስታወት ህንጻ እና እንዲሁም እድሳት ባለማግኘቱ የተነሳ ደብዝዟል የከተማ አስተዳደሩ ባህልና ተሪዝም ቢሮ የከተማዋ ቅርሶች ሲወድሙ የአዞ እንባ ከማንባት ይልቅ እንደዚህ ያሉ ጥንታዊ ውብ የአርክቴክቸር ጥበብ የሚታይባቸው ህንጻዋች እድሳት እንዲያገኙ የማድረግ ሀላፊነቱን ይወጣ ።

በድሉ ህንጻ

بازی انفجار