አማራና ታሪካዊ ጠላቶቹ (ሙላት በላይ)

ሀ/   የዉጭ ጠላቶች አዉሮፓዊያን  እንዱስትሪዎቻቸዉ  ለማምረት የሚፈልጉት ጥሬ እቃ በርካሽ ዋጋ አፍሪካ ገዝቶ በመዉሰድ እና የተመረተዉን ዉጤት ወደ አገራቸዉ ለመዉሰድ መመላለሻ መንገድ በመፈለጋቸዉ   1ኛ  የሲዊዝ ካናልን    2ኛ  የቀይባህርን መቆጣጣር ሲፈልጉ ኢትዮጵያን መቆጣጠር ፈለጉ፡፡ ለዚህም እንዲመቻቸዉ የሲዊዝ ካናልን ፈረንሳይና እንግሊዝ በአክሲዮን ገዙና መጠቀም ጀመሩ፡፡

ለዚህም መነሻ ምክንያቱ በእንግሊዝ የጥጥ ፋብሪካ በመስፋፋቱና ሲጠቀሙበት የነበረዉ የደቡብ አሜሪካ ጥጥ በማቆሙ በምትኩ ግብጽ ዉስጥ የአባይን ተፋሰስ ተጠቅሞ ጥጥ ለማምረት ታስቦ ነዉ፡፡ይሁን እንጂ የአባይን ተፋሰስ እንደልብ ለመጠቀም አባይን ከምነጩ መቆጣጠር፤ አባይን ለመቆጣጠር ኢተዮጵያን መቆጣጠር አስፈላጊ መሆኑን አምነዉ ኢትዮጵያን በግብጽ እና በኢጣሊያን በኩል በተደጋጋሚ ለመዉረር ሞክረዉ ሰይሳካ ቢቀርም ኢትዮጵያን ለማጥፋት የማይቦዝኑ መሆናቸዉን ለኢትዮጵያ አንድነት የቆሙ ሁሉ አዉቀዉና ነቅተዉ መጠበቅ አለባቸዉ፡፡

በ1888ዓ.ም በአደዋ ጦርነት ነጮች በጥቁሮች መሸነፋቸዉ በአፍሪካኖች ላይ የነጻነት ስሜት የጫረ በመሆኑ ለቅኝግዛት እርምጃቸዉ እንቅፋት ሁኖ ማግኘታቸዉ፡፡ለአዉሮፓ ህዝቦች የአፍሪካ ዘመቻ የኋላቀር አገርን ህዝብ ነጻነት ለማስተማር ነዉ የምንሄደዉ የሚሉትን ህዝባቸዉን መልስ ለነጻነት ታጋይ የሆነዉ ኢትዮጵያዊ በማክሸፉ የነሱ ፕሮፖጋንዳ ዉድቅ በመሆኑ፡፡የአድዋ ድል በኢትዮጵያዊያን ህዝብ መካከል የነበረዉን አንድነት አጉልቶ በማሳየቱ፡፡ለነጮች የታሪክ ስብራት በጥቁር መሸነፋቸዉ የጣሊያን መሸነፍ ነዉ ብለዉ ወሰዱ፡፡ ስለሆነም አማራን የጋራ ጠላት አደረጉ፡፡

ለ/ የዉስጥ ጠላቶች አዉሮፓዊያን ኢትዮጵያን በተለያየ ጊዜና በተደጋጋሚ ለመዉረር በሞከሩበት  ጊዜ ኢተዮጵያን ለማጥፋት ከጠላት ጋር  ተሰልፈዉ አገራቸዉን የወጉ ባንዳዎች ልጆችና የልጅልጆች  የአማራዉ ታሪካዊ ጠላቶች ናቸዉ፡፡ከባንዳ የተወለዱ ባንዳዎች እድገታቸዉ የዉጭ ወራሪዎች እንዴት እንደመጡ፣ ለምን እንደመጡ፣ በማን ድጋፍ እንደተደረገላቸዉ፣ ማን እንደተዋጋቸዉ፣ ለምን እነደተሸነፉ በምደጃ ዙሪያ በአባቶቻቸዉ እና በናቶቻቸዉ እየተማሩ ያደጉት ስለአገር በባእዳን መወረር ቁጭት የሚፈጥር ሳይሆን ለኢትዮጵያ እየተዋጉ ወራሪዉን ማሳደዳቸዉ በዚህም ፍትጊያ ወለጆቻቸዉ የደረሰባቸዉን ጉዳት ከወራሪዎች ሲያገኙት የነበረዉን የገንዘብ ጥቅም መቋረጥ እና የአባቶቻቸዉ ጌቶች ተሸንፈዉ ተመተዉ ኢትዮጵያን ሳያጠፉ መቅረታቸዉ የሚያስቆረቁር ቁጭት ነበር ከእናት ከአባቶቻቸዉ እየተማሩ ያደጉት፡፡

የነዚህ ትዉልድ ነዉ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከዚህ ደረጃ ያደረሳት፡፡አማራ የኢትዮጵያ ሌላዉ ገጽ በመሆኑ እነዚህ የባንዳ ዘርአዝርት ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተጠቀሙበት ስልት በቅድሚያ አማራዉን ማጥፋት ነዉ ብሉዉ የሚመሩበት መረሀ ግብር ነድፈዉ የሚያስፈጽሙበት ህገመንግስት አዉጥተዉ የሚፈጽምና የሚያስፈጽም ባነዳዎችን ገዝተዉ አማራዉንና ንጹሁን ኢትዮጵያዊ እየገደሉ ከዚህ ደረሱ፡፡ አሁንም በመግደል ላይ ያሉት  ወደፊትም ለመግደል በነበረዉ ፖሊሲና ህገመንግስት ለመስራት የመጣዉን የህዝብ አመጽ በጥግንግን እና በሽፍንፍን ሊሰሩበት ሲጥሩ የሚታዩትን የባንዳዎች ዘርአዝርት ዘመናዊ ትምህርት ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ የጌቶቻቸዉን ታሪክ ከወላጆቻቸዉ ትርክት ጋር አዛምዶና አጣጥሞ ተግባራዊ ለማድረግ እድል ሰጣቸዉ፤ አመቻቻቸዉ፡፡ የዓለም ህዝብ የካፒታሊስትና የሶሻሊስት እርዮተ ዓለም በሚል ሽኩቻ ዉስጥ ሲገባ ይህን አጋጣሚ ተጠቅመዉ የኢትዮጵያ አብዮት የሚል መሰረቱ መደብ ሳይሆን የነገድ ጥላቻ የሆነ የግራዉን የፖለቲካ ሀይል በሽፋን  በመጠቀም የአማራዉን ህዝብ ለመጨፍጨፍ ዓልመዉ በመነሳት እየጨፈጨፉት የሚገኙት፤ ወደ ፊትም በልጆቻቸዉና በልጅ ልጃቻቸዉ ለማስጨፍጨፍ እቅዳቸዉን በመለስ ኑዛዜ ያራዘሙት ፡፡ስለዚህ አማራ ቋሚ የዉጭ እና የዉስጥ ጠላቶች ያሉብህ መሆኑን አዉቀህ በቋ ሚነት  ጠንካራ ድርጅት መመስረት አለብህ፡፡ የአማራ ህልዉና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት አማራዉንና ለኢትዮጵያ አንድነትና ደህንንት የሚታገለዉን ሁሉ በወጥነትና በጠነከራ ድርጅት ለማሰባሰብ ያላሳለሰ ጥረት ያደርጋል እያደረገም ነዉ፡፡

ሙላት በላይ

ቁጥር 4 ይቀጥላል

 

The post አማራና ታሪካዊ ጠላቶቹ (ሙላት በላይ) appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.

አማራና ታሪካዊ ጠላቶቹ (ሙላት በላይ)