“በተደነገሰንልን የጥፋት መንገድ አንጓዝም” (ዮሐንስ ቧያለው የአዴፓ ፅ-ቤት ኃላፊ)

Satenaw: Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!

በዛሬው ዕለት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ላይ የተሞረው ህገ ወጥ ድርጊት ፍፁም ኋላቀር የአማራን ህዝብ የስነ ልቦና ልዕልና ዕድገት የማይመጥን ለስልጣን ሳይሆን በእያንዳንዳችን ስብዕና ላይ እና ህዝባችን መስዕዋት ሆኖ የተጎናፀፈውን ነፃነት በድጋሜ ለመንጠቅ የተቃጣ የጥፋት ሴራ በመሆኑ የአካባቢው ወጣቶች ህዝብን በማረጋጋት ከመንግስት ጎን በመቆም የሰላም ዘብ ሆናችሁ በዚህ ህገ ወጥ ድርጊት ላይ የተሳተፉ ወንጀለኞችን ለህግ በማቅረብ አንድነታችንን እንድናሳይ ጥሪዬን እያቀረብሁ።

ከጀርባ ሆነው ይህንን የጥፋት ሴራ የመሩትንና ያስተባበሩትን ዝርዝር መረጃ ለህዝብ የምናደርስ መሆኑን እየገለፅሁ ቀዳሚው ስራችን ህዝብን የሚያሽብሩ መረጃዎችን ከማስተላለፍ ተቆጥበን ቆመንለታል የምንለውን ታላቅ ህዝብ የማረጋጋት ስራ ላይ እናተኩር።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ…!

ዮሐንስ ቧያለው የአዴፓ ፅ-ቤት ኃላፊ።

The post “በተደነገሰንልን የጥፋት መንገድ አንጓዝም” (ዮሐንስ ቧያለው የአዴፓ ፅ-ቤት ኃላፊ) appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.


“በተደነገሰንልን የጥፋት መንገድ አንጓዝም” (ዮሐንስ ቧያለው የአዴፓ ፅ-ቤት ኃላፊ)