አንዳንድ መሰረታዊ ጥያቄወችና የገለልተኛ መርማሪ አስፈላጊነት ጥሪ – ጌታነህ ይስማው

Satenaw: Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!

አንዳንድ መሰረታዊ ጥያቄወች
=====••••••••========

እስኳሁን ከመንግስት በሰማነው መሰረት (ሁኔታወች ገና ይቅያየራሉ:: ስለዚህ እስካሁን ባለኝ መረጃ ጥያቄ ማንሳት እፈልጋልሁ::ከተሳሳትሁ ለመታረም ዝግጁ ነኝ)::

ሀቅ 1) የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ቅዳሜ ከቀኑ በ10 ስዓት ስብሰባ ባህርዳር ተቀመጡ::

ሀቅ 2) ከ ቀኑ 11 ስዓት አካባቢ ታጣቂወች ወደ ስብሰባው ቦታ (ርዕሠ-መስተዳድር ጽ/ቤት ህንጻ) ገብትው ተኩስ ከፍተው የክልሉን ርዕሠ-መስተዳድርና ከፍተኛ አማካሪያቸውን ሲገድሉ: ሌላ ባልስልጣንን (አቶ ምግባሩን) ክፉኛ አቆሰሉ(እሳቸውም ዛሬ አረፉ::)

ሀቅ 3) ከምሽቱ ሶስት ስዓት ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ጄነራል ሰአረ መኮንን በጠባቂያቸው በመኖሪያ ቤታቸው ከጡረተኛ ጀኔራል ጏደኛቸው ጋር ተገደሉ::
ሀቅ 4) የጀኔራል ሰአረ ገዳይ “በቁጥጥር” ስር ውሏል ከተባለ ከ36 ስዓት በኃላ “ራሱን አጥፍቷል” ይላል መንግስት እንደ የቢቢሲ-አማርኛ ዝገባ::

የሁሉንም ነፍስ እግዚአብሔር ይማር::ለቤተሰብና ጋደኞቻቸው መፅናናትን እመኛለሁ::

ከዚያስ…

ይህ የብርሃኑ ለንጅሶ መልዕክት እንደሚያረጋግጠው ጠ/ሚ አቢይ ባህር ዳር ተገኝተው ነበር:: ብርሃኑ ለንጅሶ የአቶ ለማ እጅግ ቅርብ የሆነና ከጠ/ሚ አቢይም ሆነ የኦሮሞ አክራሪወች ጋር ቅርብ በመሆኑ አቢይ ባህር ዳር ሄዶ ነበር የሚለው ታዓማኒ ነው ብለን እንውሰድ (ሁለኛ ኢዲት ያደረገው የአቢይን ባ/ዳር መሄድ ወደ “ወደ ይባላል” ዝቅ አድርጎታል (ጥያወችን ካዬ በኃላ ይመስለኛል) ::

ፌደሬል መንግስት ህዝቡን ለማረጋጋት ነው ብሎ
የሚያደርገው እንቅስቃሴ በጣም ውስንና ለአጭር ጊዜ ብቻ መሆን ይገባዋል:: የኦህዴድን ፕሮፓጋንዳ እንዳለ
መቀበል የለብንም:: በጭራሽ:: የመነሻ መሰረታዊ ጥያቄውች መካከል ጥቂቶቹ:-

1) ጠ/ሚ አብይ የከፍተኛ ባለስልጣናት መሞትና መቁሰልና ትልቅ አደጋ ሲሰሙ: (ምናልባትም ከምሽቱ ከ12 ስዓት በኃላ): ገና ምንም ባልታወቀበት ሁኔታ: አደጋው ባለበትና ምን ተጨማሪ አደጋ እንዳለ ወደ በማይታወቅበት ባህር-ዳር አውሮፕላን አዘጋጁ ብለው ይሄዳሉ: ወይስ በማዘዣ ኮማንድ ፖስት ሆነው ሁኔታወችን ይከታተላሉ? እንዴት ገና ሁኔታው ውዳልታወቀ ቦታ የራሳቸውንንም የሀገርንም ደህነነት ስጋት ላይ ጥለው ወደ ባህር-ዳር ይሄዳሉ? ወይስ ቀድመው ያውቁ ነበር?

2) ባህር-ዳር ሲሄዱ ለምን የጦር-ኃይሎች ኢታማጆር ሹምን ጥለው ሄዱ?

3) የጀኔራል ሰዓረ ገዳይ ተይዟል ብለው ነበር:: አሁን ግን ገዳዩ ጠባቂ “ራሱ አጠፋ” ተብሏል:: ከጀኔራል አሳምነው ጋርም አያያዙት:: ምንም ምርመራ ሳይደረግ:: ገዳዩም ራሱን አጥፍቶ እያለ ለምን ታሳሯል ተባለ? ለምንስ ይህንን ያህል ጊዜ ፈጀ “ራሱን ማጥፋቱን” ለማወቅ? እንዴትስ ሌሎች ጠባቂወችን አምልጦ መሄድ ቻለ?

4) ባለፈው አመት በጠ/ሚ አቢይ ላይ የተቃጣ የነፍስ ግድያ ተጠርጣሪወችን ለማወቅ ወራት ፈጅቷል:: የኢንጅነር ስመኘው ሞትም ተድበስብሶ ቀረ:: እንዴት በስዓታት ውስጥ የዚህ አደጋ ከነ-አላማው (motive and objective) ሊታወቅ ቻለ?

5) መፈንቅለ-መንግስት የሚለው ምክንያት ምን ማለት ነው? ባህር-ዳር ላይ የክልሉን ፕሬዝዳንት “በጉልበት ተክቻለሁ” ያለን ጋጠ-ወጥ ደ/ማርቆስ ወይም ደሴ እንዴት ይቀበለዋል? እንኳንስ አዲስ-አበባ? ይህን ማሰላሰል የማይችሉ: በደመ-ነፍስ መንቀሳቀስ ብቻ የሚችሉ ግብዝ ናቸው ማለት ነው ጄነራል አሳምነው?
6) የፌደራል ኃይል (መከላከያና ፓሊስ) እንደዚያ በብርሃን ፍጥነት ባህር-ዳር ሊገባ እንዴት ቻለ? የክልሉ መንግስት ጠይቆ?
7) መንግስትለምን በምርመራ ተጣራርቶ የሚደርስን ድምዳሜ ቀድሞ ደረሰ? እንዴት ሊታወቅ ቻለ? ለምን መጀመሪያ ጥሬ ሀቆችን እንዳለ ከድርጊቶች ስዓት ጋር አይገልፅም?

ገለልተኛና ታአማኒነት ያለው መርማሪና አጣሪ ኮሚሲዮን መቋቋም አለበት::

በዚህ ጉዳይ አዜማ: ህወሓትና ኦዴፓ/ኦነግ አንድ አይነት ተመሳሳይ አቋም መያዛቸውንና ኦህዴድ የሚላቸውን ትርክት እንዳለ እያወረዱ እንደሆነ ለታሪክ መዝግበናል::

ኢትዮጵያንና ህዝቧን እግዚአብሔር ይባርክ!! ቸር ያሰማን::

The post አንዳንድ መሰረታዊ ጥያቄወችና የገለልተኛ መርማሪ አስፈላጊነት ጥሪ – ጌታነህ ይስማው appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.


አንዳንድ መሰረታዊ ጥያቄወችና የገለልተኛ መርማሪ አስፈላጊነት ጥሪ – ጌታነህ ይስማው