የአማራ ክልል ፕሬዚደንት እንዲሆኑ በእጩነት የተመረጡት አቶ ተመስገን ጥሩነህ አጭር የህይወትና የስራ ልምድ ታሪክ

Satenaw: Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!

አቶ ተመስገን ጥሩነህ
አቶ ተመስገን ጥሩነህ

የትውልድ ቦታ፡- ጎጃም ፣ ብቸና ደብረወርቅ ልዩ ስሙ ወይራ

የትምህርት ዝግጅት፡- የመጀመሪያ ዲግሪ በኮምፒውተር ሳይንስ
እና የሁለተኛ ዲግሪ በተቋም የለውጥ አመራር

የትዳር ሁኔታ፡- ያገቡ

የሰሩባቸው ቦታዎች፡ –

በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ባገለገሉበት ወቅት እስከ ሻለቅነት ማዕረግ ደርሰዋል፡፡
• የሃገር መከላከያ ሰራዊት መረጃ ዋና መምሪያ
• ኤሌክትሮኒክስ መምሪያ
• ቴክኒካል መረጃ መምሪያ

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ መስራች አመራር ሆነው ሰርተዋል፤ በዚህም

• ከመምሪያ ኃላፊነት እስከ ዋና ዳይሬክተርነት የመሩ

በአማራ ክልል በተለያዩ የኃለፊነት ደረጃ ያገለገሉ ሲሆን በዚህም
• የርዕሰ-መስተዳድሩ የፀጥታ እና ቴክኖሎጂ አማካሪ
• የአማራ ገጠለር መንገዶች ባለስልጣን ም/ስራ አስኪያጅ
• የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ
• የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ
• የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር
. የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር
• የኢትዮቴሌኮም ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሰርተዋል፡፡

በመጨረሻም በሚኒስትር ማእረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ የደህንነት አማካሪ ሆነው እያገለገሉ ሲሆን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደርነት በእጩነት እንዲቀርቡ ወስኗል።

ምንጭ፡- የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅ/ቤት

The post የአማራ ክልል ፕሬዚደንት እንዲሆኑ በእጩነት የተመረጡት አቶ ተመስገን ጥሩነህ አጭር የህይወትና የስራ ልምድ ታሪክ appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.


የአማራ ክልል ፕሬዚደንት እንዲሆኑ በእጩነት የተመረጡት አቶ ተመስገን ጥሩነህ አጭር የህይወትና የስራ ልምድ ታሪክ