የርብ ወንዝ ከመጠን በላይ ሞልቶ በመፍሰስ ጉዳት እያደረሰ ነው

Satenaw: Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!

በደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦከምከም ወረዳ የርብ ወንዝ ሞልቶ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡

በወረዳው 8 ቀበሌዎች በ2 ሺህ 203 ቤቶች እንዲሁም በፎገራ ወረዳ በ10 ቀበሌዎች በ2 ሺህ 400 ቤቶች ሙሉ በሙሉ እና በከፊል ተውጠዋል፤ በሊቦ ከምከም እና ፎገራ ወረዳዎች በሚገኝ የሩዝ ሰብል ላይ ደግሞ እስከ 80 ከመቶ ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ዝርዝር ዘገባውን የሚመለከታቸውን የመንግሥት አካላት ሐሳብ በማካተት የምናደርስ ይሆናል።

ዘጋቢ፡- ብሩክ ተሾመ -ከሊቦ ከምከም

አብመድ

ፎገራ ጎንደር በጌምድር አማራ

ለማያውቀው ፎገራ ዱሩ ነው!!!

ፎገራ በአብዛኛው የሚታወቀው ሜዳማውና ውኃ በብዛበት በክረምት የሚተኛበት የጣና አዋሳኝ ቦታ ነው። ቦታው በዚህ ስም የተጠራበት ምክንያት በጊዜው አንድ ንጉስ በተጠቀሰው ቦታ አልፈው በሚሔዱበት ወቅት ነጫጭ አሞራዎች በብዛት በሜዳው ላይ ፈሰው ያያሉ ንጉሱም በአሞራዎች ብዛት ተደንቀው ለመሆኑ ይህ ሁሉ አሞራ ምን ይበላል? ብለው ይጠይቃሉ የተሰጠቸው መልስ ይህ ሁሉ አሞራማ የሚበላው “ፎግሮ” ነው የሚል መልስ ይሰጣቸዋል። ፎግሮ ማለት ጭሮ፣ በእግሩ ቆፍሮ ማለት ነው። ከዛም በጊዜ ሂደት ፎግሮ ወደ ፎገራ ተቀይሮ መጠሪያው ሆነ።

ፎገራ አሁን በፍጥነት እየገሰገሰች ያለችውን ወረታ ዋና ከተማ አድርጎ እየገሰገሰ ይገኛል። ፎገራ ከደምቢያ ጋር የመልካም ምድር አቀማመጡ አንድ ነው፤ ኩታ ገጠምም ናቸው።ለዚህ ነው ለካ ብዙ አርቲስቶች ሲዘፍኑ ደምቢያን ጠርተው ፎገራን ፎገራን ጠርተው ደምቢያን ሣይጠሩ አያልፉም።ፎገራ ሜዳው ለጥ ያለ ሜዳ ከጣና ጋር የተዋሃደ ሩዝ አምራች አገር ነው፤ ምን ሩዝ ብቻ ከብቶቹም የተለዩ ናቸው።

ወረታ የነፍጠኛው ፋሲል ደሞዝ የትውልድ። ቦታ ነች።
ከጎንደር ባህርዳር ስትመላለሽ
ወረታን አታውቂም ብሎ ሰው አማሽ
ብለው እነቃኘው እንደልቤ ፋሲል ደሞዝ ተቀኝተውላታል።ወረታ ውለታ ሲሆን# በሌላኛው ወረታ የፎገራዎች ከተማ ናት።

ፎገራ የእነቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ቅዱስ ያሬድ ጣና ቂርቆስ ሐና ማርያም ገዳም ይገኙበታል።

ጉማራና ርብ ወንዞች የሚነሱት ጉና ተራራ ሲሆን ሁለቱም የሚንቀሳቀሱት ጣና ሐይቅ ነው፤ የሚያቋርጡት ቦታ ወይም ረቀት ግን እኩል አይደለም። ጉማራ ረጅም ረቀት ይጓዛል ከርብ በአንፃሩ ሲታይ።

ርብ፦በዚህ ስም የተጠራበት ምክንያት ሲመነጭ “ቱግ ወይም ብር ብር እያለ በመሆኑ ሁኔታውን ያዩ ሰዎች ተርብ ይመስላል በማለት ተርብ የሚለውን ቃል በጊዜ ሂደት “ተ”ን ፊደል ጎርደው ትተው “ርብ” ብለው ጠሩት።

ጉማራ፦ ብዛቱም ሆነ የሚያካልለው ቦታ ብዙ በመሆኑ፤ ይህን ያዩ ሰዎች ብቻውን እንደ “ገመሮ” እየተጎማለለ ይሔዳል በማለት ተናገሩ። ገመሮ የሚለው ቃል ወደ ጉማራ ተቀይሮ የወንዙ መጠሪያ ሆነ።

በፎገራ ውስጥ ብዙ ታሪካዊ ቦታዎች አሉ ከእነዚህ መካከል
ናበጋ፦ ናበጋ ክረምቱ በጣም ከባድ ነው፤ በዚህም የተነሣ በጋን ከመናፈቃቸው የተነሣ ናበጋ ይላሉ ቦታውም”ናበጋ” ተብሎ ተጠራ። ናበጋ የኢትዮጲያው የጨዋታ አባት የፍትሐ ነገሥቱ ሊቅ የአቋቋሙ ጠበብት የተክሌ አባት የአለቃ ገበረሀሃና የትውልድ ቀየ ነች። አለቃ ገብረሃና የተማሩበት ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ናበጋ ጊዮርጊስ ይባላል። የፎገራ ሰው መማያው መገዘቻው ናበጋ ጊዮወርጊስ ነው። ናበጋ ጊዮርጊስ ታሪካዊና ጥንታዊ ነው አለቃ የተማሩትም የተቀበሩትም ከዚሁ ቤተክርስቲያን ነው፤ አሁን ግን ሲታይ ይህ ሁሉ ታሪክ ያለበት አይመመሥልም እንዳልነበረ ሆኗል።

ኃገረ ሰላም፦ አንዷ በጣም ታሪካዊ ቦታ ነች።አገረ ሰላም የአፄ ሱስንዮስ ቤተመንገስት ቅርስ አላት። አፄ ፋሲል ለኃጢያት ስርየት አስገነቧቸው የሚባሉት ቆማን አፈርዋናትንና ጭስ አባይን የሚገናኘው አንዱ የዛሬው ሰባራ ድልድይ ነው። በአድያም ሰገድ ኢያሱ ዘመን የተቆረቆረች ቅድስት ቤተክርስቲያን አለች። ስሟ አትጠገብ ማርያም ይባላል።የድንግል ማርያምን ፍቅር አልጠገባቸውጠቢል አትጠገብ ማርያም አሏት፤ እውነት አትጠገብ እናት እንዴት ጠገባለች ያውም እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም

ኃገረ ማርያም ልክ እንደነጎርጎራ ጉዛራ ደንቀዝ ጎመንጌ ጎንደር ለነገስታቶች ተመራጭ ነበረች። አሁንማ ስንቱ ቀረ

ፎገራ ከወራቶች በኋላ ይህን ይመስላል፤ብዙም አትጨነቁ ያ ማለት ድጋፍ አያስፈልጋቸውም ማለት አይደለም!!!

ጉዛራ ጎርጎራ ጎንደር

The post የርብ ወንዝ ከመጠን በላይ ሞልቶ በመፍሰስ ጉዳት እያደረሰ ነው appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.


የርብ ወንዝ ከመጠን በላይ ሞልቶ በመፍሰስ ጉዳት እያደረሰ ነው