የአቢይ መንግስት በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚያደርሰዉን ግፍ እንዴት ማስቆም ይቻላል?ኢትዮጵያንስ የኢትዮጵያዉያን ሁሉ ሀገር እንዴት ማድረግ ይቻላል?

Satenaw: Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!

ሸንቁጥ አየለ
————
1- የባልደራስ አመራሮች አባላት በግፍ ታስረዋል

2-የአስራት ሚዲያ ጋዜጠኞች: የኢቶጲስ ጋዜጠኞች እና በርካታ ጋዜጠኞች በግፍ ታስረዋል

3-የአብን አመራር እና አባላት በብዙ መቶ በሚቆጠር ሁኔታ በግፍ ታስረዋል

4- ቁጥሩ በወል የማይታውቅ ህዝብ ከባህር ዳርና ከአዲስ አበባ በአክራሪ አማራነት ተፈርጆ በገፍ ታፍሶ ታስሯል

5- የአብይን መንግስት ይቃወማሉ የሚባሉ ምሁራን በሀገር ቤት በከፍተኛ ሁኔታ የማሸማቀቅ ስራ እየተሰራባቸዉ ነዉ

6-የጀነራል አሳምነው ባለቤት ወደ ነብሰ ጥሩ ሆና ሳለ አለ ወንጀሏ ወደ እስር ቤት ተወርዉራ የጤና መቃወስ እየደረሰባት ነዉ

7- ዜጎች በዋና ዋና ከተሞች በተለይም በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ አሁንም ቤታቸዉ እንደፈረሰ እና የፍትህ ያለህ እየጮሁ ነዉ

8. በብዙ አስር ሽህ የሚቆጠሩ ዜጎች ከአስራ አምስት አመታት በላይ ገንዘባቸዉን ቆጥበዉ እና በብዙ ጉጉት የደረሳቸዉ ኮንዶሚኒዬም ሸዋ ሀገራችሁ አይደለም: ለአዲስ አበባ እና ዙሪያዉ እናንተ መጤ ናችሁ ተብለዉ ኮንዶሚኒዬም ቤታቸዉን ተከልክለዋል

9-በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ተፈናቅለዉ አሁንም ሜዳ ላይ ናቸዉ

10-በርካታ አቢያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዉ ህዝበ ክርስቲያን ተበትኖ አሁንም የፍትህ ያለህ እያለ ክርስቲያን ቢጮህም መሳቂያ እና መዘበቻ እንጅ ፍርድ ማግኘት አልቻለም

11-የቲያትር መከወኛዉ የካንጋሮ ፍርድ ቤት በኢትዮጵያዉያን ላይ ለሃያ ስምንት አመታት ሲያደርግ እንደ ነበረዉ ፍርድን በግር የመርገጥ እና በህግ የበላይነት የመቀለድ ስራዉን እያከናወነ ነዉ

12.ኢትዮጵያዉያን በአባቶቻቸዉ የነጻነት ሀገር ላይ መጤ ናቸዉ:ወራሪ ናቸዉ : መባረር አለባቸዉ የሚሉ በርካታ የጥናታዊ ጽሁፎችን የሚያቀርቡ የኦሳ ምርምር አቅራቢ ምሁራ በአደባባይ ኢትዮጵያዉያንን ሀገር አልባ እንደሆኑ እያወጁ ነዉ::የሚቀጥለዉም እርምጃ እጅግ የከፋ እና የከረፋ የወንጀል ፖሊሲያቸዉን አዉጥተዉ ተግባራዊ የማድረግ ስራ እንደሆነ በአደባባይ እየለፈፉ ነዉ::

13. በደቡብ ኢትዮጵያ:በምስራቅ ኢትዮጵያ:በመሃል ኢትዮጵያ:በአማራ ክልል እና በበርካታ የሀገሪቱ ክፍል ኢትዮጵያዉያን በታላቅ መከራ ዉስጥ ወድቀዉ እየጮሁ ነዉ?

14. የጎሳ ፖለቲካ እንደ ፋሽን ተወስዶ አብሮ የኖሩ ነገዶች እንዲባሉ በየአቅጣጫዉ እየተቀሰቀሱ ነዉ

15. ኢትዮጵያዊነት የሚባል ማንነት የለም:ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር የለችም የሚለዉ የኢህአዴጋዉያን/ኦነጋዉያን/ህዉሃታዉያን ስብከት በአስተማማኝ መሬት ወርዷል::እናም ኢትዮጵያ ሲባል ልቡ ደንገጥ የሚል ትዉልድ ሙሉ ለሙሉ እንዲከስም አሁንም በስፋት እየተሰራ ነዉ

ይሄ ሁሉ የሚከናወነዉ ደግሞ በአቢይ መንግስት ነዉ:: እናም ጥያቄዉ የአቢይ መንግስት በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚያደርሰዉን ግፍ እንዴት ማስቆም ይቻላል?

ኢትዮጵያዉያንስ ወደ አስተማማኝ ሰላም: ኢትዮጵያም የሁሉም ሀገር እንድትሆን እንዴት ማድረግ ይቻላል?

የህግ የበላይነት የሰፈነበት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዴት ማምጣት ይቻላል?ኢትዮጵያንስ የኢትዮጵያዉያን ሁሉ ሀገር እንዴት ማድረግ ይቻላል?

The post የአቢይ መንግስት በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚያደርሰዉን ግፍ እንዴት ማስቆም ይቻላል?ኢትዮጵያንስ የኢትዮጵያዉያን ሁሉ ሀገር እንዴት ማድረግ ይቻላል? appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.


የአቢይ መንግስት በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚያደርሰዉን ግፍ እንዴት ማስቆም ይቻላል?ኢትዮጵያንስ የኢትዮጵያዉያን ሁሉ ሀገር እንዴት ማድረግ ይቻላል?