የኢድ አል አድሃ በዓል ሲከበር አቅመ ደካሞችን በማሰብና በመደገፍ ሊሆን ይገባል – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር

Satenaw: Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!

የኢድ አል አድሃ (ዓረፋ) በዓል እምነቱ በሚያዘው መሰረት አቅመ ደካሞችን በማሰብና ያለው ለሌለው በማካፈል እንዲያከብር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር እድሪስ አሳሰቡ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር እድሪስ 1 ሺህ 440 ኛውን የዓረፋ በዓል አስመልክተው ለሕዝበ ሙስሊሙ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚሁ መልዕክታቸው በዓሉን የተቸገሩትን በማሰብና በማካፈል በፍቅር ማሳለፍ እንሚገባ ተናግረዋል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብርም እምነቱ በሚያዘው መሰረት አቅመ ደካሞችን በማሰብ፣ ያለውን በማካፈልና በማስደሰት መሆን እንዳለበትም ነው የገለጹት።

በአሁኑ ወቅት አንገብጋቢው ጉዳይ አንድነትና ሠላምን ማስጠበቅ መሆኑን የጠቀሱት ሃጅ ኡመር፥ “በሀገርም ሆነ በውጭ ያለን ሁሉ አንድነታችንንና ሠላማችንን ልንጠብቅ ይገባል” በማለት ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

The post የኢድ አል አድሃ በዓል ሲከበር አቅመ ደካሞችን በማሰብና በመደገፍ ሊሆን ይገባል – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.


የኢድ አል አድሃ በዓል ሲከበር አቅመ ደካሞችን በማሰብና በመደገፍ ሊሆን ይገባል – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር