አበረ አዳሙ! የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተብዬው ማን ነው?

Satenaw: Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!

አያሌው ፈንቴ

ማንነቱን ኢንጂነር ቅጣው እጅጉ ይነግሩናል እንከታተላቸው።

በኢንጂነር ቅጣው እጅጉ ይመራ የነበረው “የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ግንባር (አብአግ) በእንግሊዝኛው አጠራር Ethiopian National United Front(ENUF)  “አበረ አዳሙን”በአባልነት ተቀብሎ ሲሰራ፣ የአበረን ክህደት አሥመልክቶ ኢንጂነር ቅጣው በፋክስ (Fax) ፅሁፉ የሚከተለውን እንዲህ ሲል አሥፍሯል።

ከኢንጂኔር ቅጣው እጅጉ በጥቂቶች ዘንድ Danny በሚል ለምትጠራው ለውድ መቶ አለቃ አበረ አዳሙ!

“ መላኩና እኔ ብዙ ጊዜ በሥልክ ልናገኝህ ፈልገን ብንደውልልህ ፣በተደጋጋሚ ሥልኩን አንሥተህ እየዘጋህ እኛን ማነጋገር አልፈለግህም ።ተያያዥ ደብዳቤዎችን ለመላክ የፋክስ ቁጥርህን እንደምትልክልን ቃል ገብተህልን ብንጠብቅህም ቃልህን አልጠበቅህም።በዚህ ምክንያት ሥካን(Scan) በማድረግ ደብዳቤውን አያይዤ አንተም ሌሎቹም እንድታነቡት ላኩኝ።

ወንድሜ አበረ!  ባለመታመንህ በመጨረሻ ይህንን ጠንካራና ወሳኝ  ደብዳቤ እንድፅፍ ተገደድኩኝ።ለምንወዳት አገራችን ኢትዮጵያ ለሠንደቋ፣ለተገፋውና ለተጨቆነው ሕዝባችን በእግዚአብሔር መሃላ ፈፅመህ  ለአገራችንና ለሕዝቧ  የገባኸውን የትግል ቃልኪዳን በተደጋጋሚ አፍርሰሀል።በድርጅታችንም ላይ ክህደት ፈፅመሃል።

ፕሮፌሰር ሙሴ ተገኝ  አስመራ ላይ ሳይካትሪ ሆስፒታል  ሊያስገባህ በተነሳ ጊዜ እና በእሥር የመማቀቅ ችግርም ሲጫንህ፣ለኤርትራ ባለሥልጣናት ተማፅኖ በማቅረብ  ነፃ እንድትሆንና ወደኬንያ አምልጠህ ከድርጅቱ ደጋፊዎች ጋር እንድትቀላቀል አሥቻልንህ።

ከአባላቱም ጋር እንድትተዋወቅ ተደረገ። ብዙም ሳይቆይ በተደጋጋሚ ገንዘብም ለድርጅቱ ታጋዮች እንዲውል ላኩልህ።በመጨረሻ ደግሞ $11000( አሥራ አንድ ሽህ ዶላር) ተላከልህ። ይህ ሁሉ ገንዘብ የተላከው ለትግል እንዲውል ለታጋዮቹ እንዲሰጥ ነበር፣ግን አልተሰጠም።

አበረ!ለታጋዮቹ ጥሩ ምሳሌና የአርበኛ መሪ የሆነ አመለካከት እንዲኖራቸው ጥረት አድርግ።ለእኛም የነበረንን ዕምነት ብታሳዬን ይመረጣል።

አበረ! ”እመነኝ” ብለህ በጠየቅከኝ መሠረት አመንኩህ፣ግን የማያሥተማምን ተግባር ፈፀምክ።

ገንዘቡን ለድርጅታችን ሠዎች ካምፓላ ዩጋንዳ እንደምትሠጥ ቃል ገብተህም አልሠጠህም። ለሕዝባችን ነፃነት ወያኔን ታግሎ ለማሥወገድ  በሚታገለው ድርጅታችን ላይ ሻጥር አትሥራ። ለወያኔ የሚጠቅም አሻጥር መሥራት  ከወያኔ  ጋር መወገን  በመሆኑ፣ ሕዝባችን ይቅር የማይለው ወንጀል ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብም ዕድሜልክህን በወንጀለኛነት ይፈርጅሀል።ወንጀልህ ዕድሜ ልክ ሲከተልህም ይኖራል። ለራሥህም፣ለዘመድ አዝማድህም ፣ለአያት ቅድመ አያቶችህም  ማፈሪያ ትሆናለህ” በማለት ኢንጂነር ቅጣው በፋክስ ከ 1 እሥከ 4ገፅ ከፃፈው ውስጥ በጥቂቱ ይህን ይመሥላል።

ማሳሰቢያ! ከሳይካትሪ ሆስፒታልና ከእሥር ሁኔታ ከማምለጥ ባሻገር የታጋዮችን ገንዘብ እሥከመብላትና ክህደት እሥከመፈፀም  የዘለቀው አበረ “ከአብአግ” ድርጅት እንዴት እንደተባረረ  አሥመልክቶ ከዚህ በላይ ባጭሩ የተፃፈውን ፅሁፍ የሚደግፉ በቅድሚያ የአማርኛውን፣ቀጥሎም የእንግሊዝኛውን፣ከዚያም ቀጥሎ ከ 1—4 ተራ ቁጥር  ድረስ ያሉትን ማሥረጃዎች፣ከዚህ በታች በአባሪነት በማያያዝ ሳሥቀምጥ ፍርዱን ለአንባቢው ሕዝብ  በመተው ነው። የፅሁፎቹም  ዕድሜ ረዥም በመሆኑና ከፊሎቹም የፋክስ ውጤት ሥለሆኑ፣ኮፒ ሲደረጉ በደንብ አልወጡም።ሥለዚህ በማሳደግ( Zooma  በማድረግ ) ቢነበቡ

በመጨረሻ! ይህ አበረ የሚባለው ግለሰብ፣

-በNASAው ሳይንቲስት በኢንጂነነር ቅጣው እጅጉ መሪነት  ፀረወያኔ ትግል ለሚያካሂዱ ታጋዮች እንዲሰጥ የተላከለትን ገንዘብ ሳይሰጥ ገንዘቡን  መብላት፣ ዕምነት ማጉደል፣ ሆዳም መሆንና ከሀዲነት ከመሆኑም በተጨማሪ ወያኔን በተዘዋዋሪ የመደገፍ ባንዳነት ነው።

–በአማራነት ከቆሙት ጋር ሲገናኝ በህቡዕ ለአማራው እንደሚሰራ እያወናበደ  የኖረው ! ከሞቀው፣ከደራውና  ገንዘብ ባለበት አካባቢ የማይጠፋው አበረ!ሥዊድን አገር የግንቦት 7  አባል  የሆነውም  ከዚሁ አንፃር ጭምር እንደነበር ልቦናው ያውቀዋል።

-መቼም አበረ አድርባይ ነውና እነጄኔራል አሳምነውና እነ ኮሎኔል አለበል ወደሥልጣን  እንደመጡ ፣ለንደን የሚገኘው የኢሳቱ ወንደማገኝ ጋሹ! እንዲህ ሲል ቃለመጠይቅ  ያደርግለታል ፣”እነጄኔራል አሳምነውና እነ ኮሎኔል አለበል ሌሎችም በሕዝብ ተቀባይነት ያላቸውን ሠዎች ወደፊት የማምጣት ነገር አንዱ ጅምር ሊሆን ይችላል?

አበረ ሲመልስ “ምንም ጥያቄ  የለውም።የሚገባቸውን ቦታ ነው ያገኙት። አሳምነው ታሥሮ እሥር ቤት ሲማቅቅ ፣አለበል ተሠዶ በሥደት የነበር ለዚያ ሕዝብ ሲለፈልፍ  የሚቻለውን ሁሉ ሲያደርግ የነበረ ነው።ሁለቱም ጥሩ ልምድና ጥሩ ሞያ ያላቸው መኮንኖች ናቸው።ለዚያ ሕዝብ ታግለዋል መከራ አይተዋል።በአጋጣሚም ለ20ቀናት ኢትዮጵያ ነበርኩ።ዕድል ገጥሞኝ አንዳንዶችን አነጋግሬአለሁ።

አበረ! ቀደም ሲል ኢትዮጵያ ሳይገባ ጄኔራል አሳምነውንም ሆነ ኮሎኔል አለበልን በማድነቅና በማሞገሥ የካባቸው፣ኢትዮጵያ ገብቶ እያምታታ ለመኖር ሥላቀደ  እንደነበር ተግባሩ ምሥክር ነው።  ይህ ሠው ኢትዮጵያ ገብቶ አዴፓ ውስጥ ከመታየቱ በፊት  አብኖችንም የእነርሱ ደጋፊ በመምሠል ሳያዘናጋቸው አልቀረም።ሳይውል ሳያድር ግን  ሆዱና ሥልጣኗ ሥለጣመችው ከግንቦት 7 ወደአዴፓ ተወንጭፎ  በመግባት ሥራ ያዘ።

ዛሬ የሠራውን ሥናይ ይህ ሠው እነጄኔራል አሳምነውን የካበበት ምክንያት በኋላ ላይ ለደረሰበት ሥልጣን  አሥቀድሞ ራሱን ለመሸጥ ያደረገው ጉዞ ይመሥላል።

ሥለ እነአሳምነው ይህንን  ከማለትም አልፎ፣ “የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ያደረገኝ አሳምነው ነው” ብሎ ያለን አበረ፣አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውሥጥ አፍራሽ ተልዕኮውንና የባንዳ አርበኝነቱን  ለመወጣት፣ከኦሮሞ ወራሪ ወንጀለኞች ከእነአቢይ ጋር በመወገን  በሚሊዮኖች የሚቆጠር አማራ የደገፈውን፣ ሥራው ምሥክር የሆነለትን ጄኔራል አሳምነውን  ከመሳደብም አልፎ  ባልሠራው ሥራ  ወንጀለኛ አድርጎት አረፈ።

በዚህ ቃለ መጠይቅም ላይ ከተናገራቸው  መካከል አንዱ፣በእነበረከት  ጊዜ ብአዴን! አማራውን ትጥቅ ሊያሥፈታ ነው የሚል ወሬ እንደሰማሁ ለፋኖዎችም ለሚመለከታቸውም መልዕክት በማሥተላለፍ አማራ ትጥቅ እንዳይፈታ ታግያለሁ” ይላል።

ታዲያ ትናንት ይህን አደረግኩኝ የሚለን አበረ ዛሬ እርሱ ራሱ ሥልጣን ሲይዝ ይበልጥ አማራን ማሥታጠቅ ሲገባው ለምን ትጥቅ ማሥፈታትን፣ማሳደድን፣ማሳሰርን እና መግደል ማሥገደልን መረጠ? ያው የተለመደው ቃል አባይነቱና ክህደቱ ጠፍሮ ይዞት ነው?

አበረ!ሥለሰኔው ግድያ ምሥክርነቱን ሲሰጥ “ጄኔራል አሳምነው ሥብሰባ ጠርቶን እንደተሰበሰብን ከውጭ የመሳሪያ ድምፅ ሰማን።ሞቢሎቻችን በእጆቻችን ሥለነበሩ መረጃ መለዋወጥ ጀመርን” ይለናል።

እንደአበረ  አባባል የሰበሰባቸው እና  ግድያውን የፈፀመው ጄኔራል አሳምነው ከሆነ፣

(1)እንዴት  በቅድሚያ ሞቢላቸውን  ሳይሰበስብ ቀረ?

(2) ጄኔራሉ  ሰብስቧቸው  መረጃ ሲለዋወጡበት እንዴት ቁጭ ብሎ አያቸው ወይስ ህይወቱን እንዲያጠፉት ፈቀደላቸው?

አዬ አበረ ብርብራው! ውሸትን አንተ ዋሻት።ሠው ከቀወሰና ካበደ ንግግሩ “አራባና ቆቦ መረገጡ” አያሥገረመንም።

-ኢንጂነር ቅጣው እጅጉ ቀደም ሲል የጠቀሰው ፕሮፌሰር ሙሴ ተገኝ! አበረን  “ሳይካትሪ ሆሥፒታል” ሳያሥገባው እንዲያመልጥ መደረጉ፣ለዛሬው “ቀውስ ወይም ዕብደት” ዳርጎታል። ጄኔራል አሳምነውንም  “ዕብድ” ብሎ እንዲዘልፍ ድፍረት ሠጥቶታል ብዬ እንዳምን ተገድጃለሁ።

ልብ በሉልኝ!  ጤነኛ ሠው ቢናገር ኖሮ “አሳምነውን ለመተቸትና ታፔላ ለመለጠፍ የሞራል ልዕልና የለውም” ይባል ነበር።ነገር ግን ተሳዳቢው ራሱ ያበደ ሥለሆነ ሌላውን ሠው “ዕብድ” ብሎ ሲናገር  ከመሳቅ በሥተቀር ምን ይደረጋል።

አበረ! ለሆዱና ለሥልጣኑ ሲል ምንም ከማድረግ የማይመለስ  ሠው እንደሆነ  ታዝበናል።ዛሬም ለአማራ ወገኑ ህይወቱን የገበረውን ጄኔራል አሳምነውን ለማራከስ መሞከር “ጅብ እማያውቁት አገር ሄዶ ነት አንጥፉልኝ”አለ እንደሚባለው ከመሆን አይዘልም።

”ወንድ እኩል ነው ያልሽው፣እንዴት ወንድ እኩል ነው፣

ማሾ እና ብርሌ ሥራው ለእየቅል ነው።                    “አበረና አሳምነው ሥራቸው ለእየቅል ነው”

አሁን በቅርቡ ሰኔ 15ቀን ባህርዳር ላይ፣አበረም የሚጠረጠርበት በእነንጉሱ ጥላሁንና በተወሰኑ የአማራ ባንዳዎች ተባባሪነትና አሳባቂነት፣የአማራን ዘር ከምድረገፅ ለማጥፋት “አባቱ ዳኛ፣ልጁ ቀማኛ”በሆኑት  በአማራ ጠሎቹ በኦሮሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አህመድና  በኦሮሞ መከላከያ ሚኒስቴር ለማ መገርሳ መሪነት  ከ16ኛው ክፍለ ዘመን የጋላ ወረራ የባሰ አሥከፊ ወረራ በማካሄድ  አራት አመራሮችን እና ቁጥራቸው በርከት ያሉ በአዴፓ አካባቢ ያሉ ሠዎችን  ገድለውና አሥገድለው እርስ በእርስ እንደተጋደልንና መፈንቅለ መንግሥት እንደሆነ  አድርገው  ውሸት አቀነባብረው ለፈፉ።

በዚህም ሀሰት ትርክት የአብንን አባላት ከአመራር ጭምር:የባለአደራሱን ሠዎች፣ጋዜጠኞችን ፋኖዎችን በጅምላ እያንገላቱ፣እያፈናቀሉ፣እያሠሩ እና እየገደሉ ይገኛሉ።ይህ ዘር አውዳሚ ተግባር አማራው በአጣዳፊ ተሰባስቦ ካላሥቆመው በሥተቀር መጥፊያው እንደሚሆን መረዳት አይከብድም።

ዛሬ ብአዴን|አዴፓ ከጀግናው ጄኔራል አሳምነው ጭምር  አራት በአቋም ደረጃ ከትግሬውና ከኦሮሞው ተፅዕኖ በመራቅ ላይ የነበሩ መሪዎቹን ካጣ በኋላ፣ ምናልባት አቢይ ያሥቀመጠልን መሪ ካልሆነ አሁን የተሾመው አዲሱ የአዴፓ  መሪ  እና ሌሎቹ ተመራጮች፣እንደአለፉት  መሪዎች ከትግሬውና ከኦሮሞው  ተፅዕኖ ውጭ የመሆን አቅም ፈጥረው ከአማራው ጎን ለመቆም ቁርጠኝነቱ ካላቸው፣ጠላት በቀላሉ ለቡርቦራም ሆነ ለሥለላ በአጠቃላይ በመሣሪያነት ሊገለገልበት የሚችለውንና ለህይወታቸው አሥጊ የሆነውን አበረ አዳሙን ከአጠገባቸው ማራቅ የግድ ነው።

 

አማራው ጠላቱን  አውቆ ማንነቱን እና ህልውናውን  ያሥጠብቅ !

አያሌው ፈንቴ

 

The post አበረ አዳሙ! የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተብዬው ማን ነው? appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.


አበረ አዳሙ! የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተብዬው ማን ነው?