ፍትህ ወዴት አለሽ ?! ለግፉአን’ስ ተጠያቂው ማነው ?! ይድነቃቸው ከበደ

Satenaw: Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!

ክልል የመሆን ጥያቄን ” በግልበት ወይም በህግ አስከብሩ ” ፤ የተባሉትን ትዕዛዝ በመቀበል ፤ እራሱን ኤጄቶ እያለ በሚጠራ ስብስብ አስተባባሪነት እና መሪነት በተፈጸመ አሰቃቂ የጅምላ ጥቃት ከ60 በላይ ሰዎች በግፍ ተገድለዋል ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ፣ ለዘመናት ከኖሩበት የተፈናቀሉም ብዙዎች ናቸው ፣ አብያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ ንብረትም ተዘርፏል።

ክልል የመሆን ጥያቄን በግልበት ወይም በህግ በማለት ግንባር ቀደም በመሆን ፤ ለድርጊቱ መፈጸም ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ ፤ የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጌታሁን ደጉዬ እና ምክትላቸው ( የኤጄቶ መሪ ) ታሪኩ ለማ ጨምሮ ዋና ዋና 9 ሰዎች ፤ እያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር ዋስትና በማቅረብ ጉዳያቸውን ውጭ ሆነው እንዲከታተሉ መወሰኑ ተነግሯል።

ለዚህ ሁሉ ዕኩይ ተግባር ተጠያቂው ማነው ?! አሁንም እንደዚህ-ቀደም ይሄ’ም ተደበስብሶ ሊታለፍ ይሆን ?! ፍትህ ወዴት አለሽ ?! ለግፉአን’ስ ተጠያቂው ማነው ?! ነገሩን ይበልጥ አስገራሚና አሳዛኝ የሚያደርገው ፤ የሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም የተፈጠረውን አሳዛኝ ክስተት ተከትሎ፤ ለረዥም ጊዜ ከፍተኛ ትችት የቀረበበት እና ሊሻሻሉ ይገባል የተባለውን የፀረ ሽብር ሕግ ሽፋን በማድረግ ፤ በቦታው የነበረ እና ያልነበረ ፣ ምን ይሄ ብቻ ፤ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ተከታትሎ ሊዘግብ የሄደ ጋዜጠኛ ጭምር በመያዝ ፤
ዛሬም እንደ-የያኔው ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች፣ ህጋዊ የፖለቲካ ድርጅት አባላት እና ሌሎች በጅምላ በሽብር ወንጀል
ተወንጅለው ፣ የዋስትና መብታቸው ተከልክለው በእስር ላይ ይገኛሉ ።

ፍትህ ወዴት አለሽ ?!
ፍትህ ወዴት አለሽ ?!
ፍትህ ወዴት አለሽ ?!

The post ፍትህ ወዴት አለሽ ?! ለግፉአን’ስ ተጠያቂው ማነው ?! ይድነቃቸው ከበደ appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.


ፍትህ ወዴት አለሽ ?! ለግፉአን’ስ ተጠያቂው ማነው ?! ይድነቃቸው ከበደ