በሳምንት ውስጥ ሌላ የኢሕ አዴግ የስራ አስፈጻሚ ስብስባ ተጠራ

Satenaw: Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከሐሙስ ነሐሴ 2 ቀን 2011 ዓ.ም. እስከ ዓርብ ነሐሴ 4 ቀን 2011 ዓ.ም ስብሰባ ማድረጉን፣ ስብሰባዉን ተከትሎ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የኢሕአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት የኦህዴድ/ኦዴፓው አቶ ፍቃዱ ተሰማ፣  ከስብሰባው መጠናቀቅ በኋላ፣ በስብሰባው ስለተወሰኑ ዉሳኔዎች ገለጻ መስጠታቸው ይታወሳል።

ቀጣዩ አገር አቀፍ ምርጫ ሕገ መንግሥቱ ባስቀመጠው መሠረት በ2012 ዓ.ም፣ የመካሄድ አስፈላጊነት ላይ አቋም በመያዝ፣ እንደ ድርጅትም እንደ መንግሥትም ዝግጅት እንዲደረግ አቅጣጫ መቀመጡን፣ የኢሕአዴግ እህትና አጋር ድርጅቶችን ዉህደት በተመለከተ፣ በሐዋሳ በተካሄደው የግንባሩ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ በተቀመጠ አቅጣጫ መሠረት፣ በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተካሄደ የነበረው ጥናት ማለቁ፣  ጥናቱ ውይይት እየተደረገበት እንደሆነና ሁሉም ድርጅቶች መክረውበት ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ሪፖርት እንዲያቀርቡ መወሰኑን፣ በአገሪቷ የጽንፍኛ ብሄረተኝነት ትልቅ  አደጋና የብሔር ጽንፈኝነት ለአገራዊ አንድነትና ለፌዴራላዊት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ትልቅ ተግዳሮት መሆኑን በሌሎች በርካታ አጀብዳዎች ዙሪያ የስራ አስፈጻሚው መነጋገሩን አቶ ፍቃዱ ገልጸው ነበር።

ሆኖም ኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚውን በድጋሚ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱን  ጦማሪ አያሌው መንበር ዘግባል። ” ድርጅቱ ስብሰባውን ካጠናቀቀ ሳምንት አልሆነውም።በባለፈው ስብሰባው ምንም የረባ ውሳኔ ሳያሳልፍ የተለያየው ስራ አስፈፃሚው በአሁኑ ይካካሳል ተብሎ ይጠበቃል” ሲል የጻፈው አያሌው፣ ” በተለይም የድርጅቱን አራት ከፍተኛ አመራሮች እና ወደ መቶ የሚጠጉ የፀጥታ አመራርና ባለሙያዎችን ለህልፈት የዳረገውን የሰኔ 15ቱን ግድያ የምርመራ ሪፖርት በአሁኑ ስብሰባው መወያያ አጀንዳ ሊሆን እንደሚችል ይገልጻል፡

 

 

The post በሳምንት ውስጥ ሌላ የኢሕ አዴግ የስራ አስፈጻሚ ስብስባ ተጠራ appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.


በሳምንት ውስጥ ሌላ የኢሕ አዴግ የስራ አስፈጻሚ ስብስባ ተጠራ