ኢራን በባህረ ሰላጤው የሚኖር የውጭ ሃገራት ወታደራዊ እንቅስቃሴ የቀጠናውን ሰላም እንደሚያደፈርስ አስጠነቀቀች

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 12 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢራን ባህር ሃይል አዛዥ በባህረ ሰላጤው አካባቢ የሚኖር የውጭ ሃገራት የጦር ሃይል ስምሪት የቀጠናውን ሰላም እንደሚያደፈርስ አስጠነቀቁ።

የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጠባቂ ባህር ሃይል አዛዥ አሊሬዛ ታንሲሪ እንዳሉት፥ ቴህራን በቀጠናው ዘወትር ሰላም እንዲሰፍን እየሰራች ነው።

እንደ እርሳቸው ገለጻ ኢራንን ጨምሮ የባህረ ሰላጤው ሃገራት የቀጠናውን ሰላም የማረጋገጥ አቅም አላቸው።

ይሁን እንጅ ምዕራባውያን በቀጠናው የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለአካባቢው ሰላም ጠንቅ ነው ሲሉም አስጠንቅቅዋል።

በተለይም አሜሪካ እና ብሪታንያ በፐርሺያ ባህረ ሰላጤ እያደረጉት ያለው የባህር ሃይል እንቅስቃሴ በቀጠናው አለመረጋጋት እንዲከሰት ሰበብ ነው በማለትም ሃገራቱን ኮንነዋል።

ከዚህ አንጻርም ሀገራት ከመሰል አደጋ አምጭ ድርጊት እንዲቆጠቡም አስጠንቅቀዋል።

የባህረ ሰላጤው አካባቢ በተለይም የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከባድ ወታደራዊ እሽቅድድም እያስተናገደ ይገኛል።

 

 

ምንጭ፦ ፕረስ ቲቪ

 


ኢራን በባህረ ሰላጤው የሚኖር የውጭ ሃገራት ወታደራዊ እንቅስቃሴ የቀጠናውን ሰላም እንደሚያደፈርስ አስጠነቀቀች