በዓለም ዝናን ያተረፈው ብሎም ተወዳጁ የዕልፍ አዋርዶች ባለቤት የሆነው የሬጌ ስልት አቀንቃኙ ቴዲ አፍሮ በዓለም ዝነኛ በሆነው በኢኮ ስቴጅ እ.ኤ.አ September 1/2019 Washington DC ላይ የሙዚቃ ስራውን ያቀርባል

Satenaw: Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!

ኢኮ ስቴጅ ምንድ ነው..?

ኢኮ ስቴጅ ከ2012 A.C ጀምሮ ለታዳሚዎች የተከፈተ ዝነኛ ስቴጅ ነው። የ30’000 Sq ስፋት ያለው ከ3000 በላይ ታዳሚዎችን የሚያስተናግድ ደረጃውን የጠበቀ የምሽት መዝናኛ /Night Club/ ነው። ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የዘመኑ ቴክኖሎጂ የደረሰባቸውን የድምፅ ማስተጋቢያ /ስፒከር/ ያለው LED Visual /እይታ/ የሆኑ መብራቶችን የገጠመ እጅግ ዘመናዊ መድረክ ነው። ኢኮ ስቴጅ በዓለማችን በ4ኛ ደረጃ በአገሪቷም /አሜሪካ/ 1ኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ የኮንሰርት ስፍራ ነው።  ከላይ እንደጠቀስኩት September 2012 ስራውን የጀመረው ይህ ድርጅት በዕለቱ 7ኛ ዓመቱን ያከብራል።

በኢኮ ስቴጅ የአለማችን ዝነኞች እነማን የሙዚቃ ስራቸውን አቅርበዋል..?
✔ እውቁ የአሜሪካ የኤሌክትሮኒክስ ሙዚቀኛ ZHU
✔የጀርመኑ እና የሩሲያው ታዋቂ ፕሮዲውሰር፣ ዘፋኝ፣ግጥም ፃፊ እና ዲጄ የሆነው በሙዚቃ ስሙ Zedd የተባለው አርቲስት።
✔Rezz የተባለች እውቅ የካናዳ ዲጄ እና ፕሮዲውሰር
✔ kshmr ይሔም የአሜሪካ ታዋቂ ዲጄ እና ፕሮዲውሰር ሲሆን በጠቅላላ የጠቀስናቸው እንደ ቴዲ አፍሮ በመድረክ ስማቸው የሚጠሩ ናቸው።

በአገራችን በስፋት ላይታወቁ ይችላሉ በቀሪው ዓለም ግን ከፍተኛ ዝናን ያተረፉ በርካታ አድናቂዎች ያሏቸው ዝነኞች ናቸው። ከነዚህም በተጨማሪ እንደነ DJ Madeon ፈረንሳዊ, DJ Getter አሜሪካዊ, Meek Mill የተባለ አሜሪካዊ Rapper እና Money Bagg Yo የተባለ ራፐር በጋራ ትልቅ ዝግጅት አዘጋጅተውበታል። ከዓለማችን እውቆች ቀረ ሊባል የሚችል ዝነኛ እስከማይገኝ ድረስ ደረጃቸውን የጠበቁ የዲጄ እና የባንድ ስራዎች የቀረቡበት ግዙፍ መድረክ ነው። በዚህ ሰንጠረዥ መኃል ታላቁ እና ዝነኛው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን / #TeddyAfro / በመገኘቱ ደስታችን እንደ ድርጅት ወደር የሌለው ሲሆን እንደ አገርም የሙዚቃ ኢንዱስትሪያችንን ከፍታ የሚያንፀባርቅ ልዩ አጋጣሚ ነው ብለን እናምናለን። እርግጥ ቴዲ አፍሮ ዘውትር የአገራችንን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ በተሻለ መልክ በዓለም ትኩረት እንዲያገኝ በጥረት የሚሰራ አርቲስት ስለመሆኑ መናገር ለቀባሪው የማርዳት ያህል ነው የሚሆንብን።

The King Teddy Afro is set to rock the world famous Echo Stage – Washington DC – on Labor Day weekend Sunday September 1st. Tickets will be available soon.

ለቴዲ አፍሮ ከወዲሁ መልካም የስራ ጊዜ እንመኛለን።

© 2019 Roman Film Production

The post በዓለም ዝናን ያተረፈው ብሎም ተወዳጁ የዕልፍ አዋርዶች ባለቤት የሆነው የሬጌ ስልት አቀንቃኙ ቴዲ አፍሮ በዓለም ዝነኛ በሆነው በኢኮ ስቴጅ እ.ኤ.አ September 1/2019 Washington DC ላይ የሙዚቃ ስራውን ያቀርባል appeared first on ሳተናው: Satenaw Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!.


በዓለም ዝናን ያተረፈው ብሎም ተወዳጁ የዕልፍ አዋርዶች ባለቤት የሆነው የሬጌ ስልት አቀንቃኙ ቴዲ አፍሮ በዓለም ዝነኛ በሆነው በኢኮ ስቴጅ እ.ኤ.አ September 1/2019 Washington DC ላይ የሙዚቃ ስራውን ያቀርባል