የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መስከረም 04 ቀን 2012 ዓ.ም በመላው አገሪቷ እንዲካሄድ የጠራችው እዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በኦሮሚያ ክልል እንዲካሄድ አልተፈቀደም

Satenaw: Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል ከፍያለው ተፈራ በሰጡት መግለጫ መሠረት፥ በኦሮሚያ ክልል የተፈቀደ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሌለ እና የሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎችም ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑን ገልፀዋል። ስለዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መስከረም 04 ቀን 2012 ዓ.ም በመላው አገሪቷ እንዲካሄድ የጠራችው እዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በኦሮሚያ ክልል እንዲካሄድ አልተፈቀደም:: የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከወዲሁ አቋሙን እና ወገንተኝነቱን አሳውቋል::

ኢሕአዲግን የመሰረቱት ግለሰቦች አስቀድመው በ1960ቹ ዓ.ም በተማሪው እንቅስቃሴ ወቅት የማርክስ ሌኒን የፖለቲካ አማኝ የነበሩ የትግራይ ተወላጅ ሲሆኑ፤ በዚሁ እምነት መሰረት በፀረ ሀይማኖትን አስተሳሰብ በመለከፋቸው በተለይ ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ጥላቻ አላቸው። ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እና ተከታዮችን በሀገሪቱ ብቸኛ ተጠቃሚ አድርጎ የሚሰብከው የ1960ዎቹ የነበረ ዋለልኝ መኮንን የሚባለው ወጣት (The Question of Nationalities in Ethiopia) በሚለው የእንጊልዘኛ ጽሑፉ ላይ በጊዜው የነበሩ ወጣቶች ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ጥላቻ እንደነበራቸው ያሳያል።

በጽሑፍ ላይ እንደታየው ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና ተከታዮቿ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም አይነት የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ የበላይነት ሊኖራቸው እንደማይገባ ይሰብካል። ይህን የወያኔን ጸረ ኦርቶዶክስ አቋም ምቹ ሁኔታ የፈጠረላቸው ጸረ ኦርቶዶክስ ፕሮቴስታንት እና ሙስሊም ባለስልጣናት ስልጣናቸውን በመጠቀም በኦርቶዶክስ ክርስቲያኑ ላይ ከፍተኛ የዘር ፍጅት ፈጽመዋል። በተግባር እንደሚታየው ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ከፖለቲካው ስርአት በተቀነባበረ መልኩ ሲገለሉ በኢኮኖሚውም እረገድ በአዋጅ ንብረታቸውን ተወርሰው አብዛኛውም ምእመናን በድሕነት እንዲማቅቁ ተደርገው በራሳቸው መሬትና ባፈሩት ንብረት ሌሎች ሲንደላቀቁበት ይታያል።

አለም

The post የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መስከረም 04 ቀን 2012 ዓ.ም በመላው አገሪቷ እንዲካሄድ የጠራችው እዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በኦሮሚያ ክልል እንዲካሄድ አልተፈቀደም appeared first on ሳተናው: Satenaw: Ethiopian News/Breaking News: Your right to know!.


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መስከረም 04 ቀን 2012 ዓ.ም በመላው አገሪቷ እንዲካሄድ የጠራችው እዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በኦሮሚያ ክልል እንዲካሄድ አልተፈቀደም