ባልደራስን ለእነ ጃዋር አጀንዳ ለመፈልፈል ምን አደከመው!? (አበነዘር ይስሃቅ)

Satenaw: Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!

ዛሬ ብዙ የባልደራሱ ደጋፊዎች በቅርቡ የጠራውን የጋዜጣዊ መግለጫ አስመልክቶ የተለያዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል። ምነው ባልደራሱ አይ ልክ ተደረገ እንዴ? ከማለት አልፈው ልዩ ልዩ ጥያቄዎች የጠየቁ አሉ ። ባልደራሱ እርግጥ ነው በፈለገው መንገድ እና ርዕስ መግለጫ መስጠት ይችላል ነገር ግን ሕግን ሽፋን አድርገው የዜጎችን መብት ለመገደብ ቀዳዳ ለሚፈልጉ ተረኞች አጀንዳ እና ማምለጫ ማዘጋጀት ግን ብዙ ከሚጠበቅበት ባልደራስ አይጠበቅም ግራ ቀኙን ማየት ያስፈልጋል።ባልደራስ ብቻውን ሮጦ በአንድ መግለጫ የሚፈታው የአገር ችግር እንደሌለ እየታወቀ አብይ አህመድን ጨምሮ የኦርቶዶክስን ጥያቄ ለማፈን “አይዟችሁ ኦርቶዶክስ አትከፈልም ምነው ፖለቲካ ውስጣችሁ ገባ እንዴ?” ማለቱን ልብ ይሉዋል።ሰበብ እየተፈለገ ነው ማለት ነው።

የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጆች ጀርባ የተሸሸገው ሐጂ ጃዋር የዛሬውን የባልደራሱን የጋዜጣዊ መግለጫ ጥሪ ላይ የመስከረም 4/2012 ሰልፍንም አስመልክቶ የራሱን ምልከታ ይሰጣል መባሉ ግርታ ፈጥሩዋል። ብዙዎቹ የባልደራሱ ደጋፊዎች እንደጠረጠሩት ለእነ አያቶላ የተመቸች አጀንዳ መሆንዋን ወዲያው በገጹ ጃዋር ደስታውን ገልጹዋል። ይህን ተከትሎ የተፋራው አለመቅረቱን ስናይ በእርግጥ ባልደራሱ ቆም ብሎ ግራ ቀኙን ለማየት ፈቃደኝነት ማጣት ለእነ ጃዋር የተመቸ ታክቲክ ፈጥሮ ጫጫታ ማስነሳቱን ብዙዎች አልወደዱትም።

ከፈለጉ መግለጫውን ከሰልፉ በሁዋላ በማግስቱ ይስጡ ከሚሉት ጀምሮ ተሰላፊዎችን ባልሆነንአጀንዳ ይከፍላል፣የሰልፉ ጠሪዎች ሌላ እንደሆኑ እየታወቀ ይህን ተከትሎ ባልደራስ ብቅ ማለቱ ከሕዝብ ይልቅ የሚጠቅመው ሰበብ ፈጥረው የሕዝቡን መብት ለመገደብ የተነሱትን ነው የሚል ቅሬታ እየቀረበለት ጆሮ ዳባ ማለቱ ባልደራሱ ውስጡን ይፈትሽ፣የአገሪቱን ተጨባጭ የፖለቲካ ሁኔታ በእግባቡ ይረዳ፣ለተቀናቃኝ ዱላ የምታቀብልበትን አጀንዳ በዲሞክራሲያዊ መብቴ ነው ስም የገዢዎችን አፈና የሚያጠናክር ስትራቶጂ ውስጥ እንዳይዘፈቅ ይጠንቀቅ የሚሉ እና አያሌ የተቆራረጡ ተስፋ ያደረጉትን ባልደራስ ባልሆነ ቦታ እንደማግኘት የቆጠሩትም ነበሩ። ለሁሉም ባልደራስ የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ማለቱ የሚያዋጣ አይደለም።

ተከታዩ የባልደራሱ ደጋፊ ትዝብት የዛሬውን በራሱ በመብት ተሟጋቹ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ትዊተር ገጽ ጭምር የቀረቡ የደጋፊዎቹን ተቃውሞ እሱም ሆነ ሌሌቹ አመራሮች ልማትን ጊዜ ያገኙ አይመስልም ስለዚህም የባልደራሱን ጥሪ ተከትሎ እልል በቅምጤ ያሉትን የእነ ሐጂ ጃዋርን ደስታ ቃኝቶ አቤኔዘር ይስሃቅ ያሰፈረውን ያንብቡ ሼር ያድርይሻል።
እነ ጃዋር የሚፈልጉት ይሄንን ነበር።

” ባልደራስ” የተባለው እንቅስቃሴ መሪ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይና ከአዲስ አበባ ጋር በተገናኘ መግለጫ ለመስጠት ጥሪ ማድረጉን ተከትሎ “ይህ ሰውዬ የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው። ልክ እንደ አባይ ጸሃዬ ነው። እነሱ ያወሩትን ወሬ ያወጣል። በር ዘግተው ያሴሩትን ሴራ እሱ አዳባባይ ያወጣል” ብሏል ጃዋር። ትርጉሙ የ Ephrem Ephrem

በታዋዊ ሰዎችና በፖለቲካ ድርጅቶች በኩል ጊዜውንና ሁኔታውን ያላገናዘበ፣ ትርፍና ኪሳራን ያላሰላ የፖለቲካ ንግግር፣ ጽሑፍና እንቅስቃሴ ሁሉ በተቃራኒ ወገን ለቆመ ቡድን የመምቻ ድንጋይ ማቀበልና በወጥመዳቸው ውስጥ ሰተት ብሎ መግባት ነው። በማንኛውም ዓይነት ሥራ ውስጥ “Timing” የሚባል ነገር አለ። መቼ? ምን? የት? እንዴት? መናገርና ማድረግ እንዳለብህ ቆም ብለህ ማሰብ ካልቻልክ ለበጎ ነው ያልከው ነገር ሁሉ አደጋ ይዞ ሊመጣ ይችላል።

Ermias Legesse Wakjira እስክንደር. . . እባካችሁ ይሄንን ጉዳይ ተውቱ። “አዲስ አበባ የአዲስ አበባውያን ናት” ለማለት የግድ የኦርቶዶክስ ሐይማኖት ተከታዮች የጠሩትን ሰልፍ ተገን አድርጋችሁ መግለጫ መስጠት አይጠበቅባችሁም። የምታደርጉትን ነገር በራሳችሁ ጊዜና ራሳችሁ በምትቀርጹት አጀንዳ ዙሪያ አድርጉ። የተገኘውን መደረክ ሁሉ “ለባልደርስ አላማ እንጠቀምበት” ማለት አካሄዳችሁ ላይ ጥያቄ ማስነሳቱ አይቀርም። እኔን ጨምሮ ደጋፊዎቻችሁን በሁሉ ነገር ሲነታረኩ እንዲዝሉ ታደርጋላችሁ።

አሁን ላይ መግለጫ ባትሰጡ ምንም የምታጡት ነገር የለም። ነገር ግን የመስከረም 4ቱን ሰልፍ ተገን አድርጋችሁ መግለጫ ካልሰጠን ስትሉ የምትፈጥሩት ችግርና የምታመጡት ኪሳራ ይብሳል። ካልሆነም “በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰጥ መግለጫ” ብላችሁ በሚቀጥለው ሳምንት ብታደርጉት ይሻል።

ዓበነዘር ይስሃቅ

The post ባልደራስን ለእነ ጃዋር አጀንዳ ለመፈልፈል ምን አደከመው!? (አበነዘር ይስሃቅ) appeared first on ሳተናው: Satenaw: Ethiopian News/Breaking News: Your right to know!.


ባልደራስን ለእነ ጃዋር አጀንዳ ለመፈልፈል ምን አደከመው!? (አበነዘር ይስሃቅ)