የአዲስ ዓመት በዓል ዕየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2012 አዲስ ዓመት በዓል በመላው ሀገሪቱ እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉን በማስመልከት በተለይም በአዲስ አበባ የተለያዩ የመዝናኛ ዝግጅቶች ተካሂደዋል።

በብሄራዊ ቤተ መንግስት ጳጉሜን በመደመር የብሄራዊ የአንድነት ቀን የማጠቃለያ እና የአዲስ ዓመት የዋዜማ ስነ ስርዓት ተከናውኗል።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂምን ጨምሮ በርከት ያሉ ሰዎች በዚህ ዝግጅት ላይ ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያሰናዳው የዋዜማ ምሽት መርሃ ግብር በአስተዳደሩ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተከናውኗል።

በምሽት መርሃ ግብሩ ላይ ሃገራዊ አንድነትና ፍቅርን የሚያጠናክሩ መልዕክቶች የተላለፉ ሲሆን፥ የተለያዩ ጥዑመ ዜማዎች ቀርበዋል።

በመዲናዋ የተከናወነው የርችት ተኩስ ስነ ስርዓትም የአዲስ ዓመት አቀባበል ስነ ስርዓቱን ደማቅ አድርጎታል።

አዲስ አበባና ድሬዳዋን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ ታላላቅ ሆቴሎች አዘጋጅነትም በዋዜማው የሙዚቃ ድግሶች ተከናውኖዋል።


የአዲስ ዓመት በዓል ዕየተከበረ ነው