የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዋዜማ ምሽት መርሃ ግብር አከናወነ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዋዜማ ምሽት መርሃ ግብር አከናወነ።

በምሽት መርሃ ግብሩ ሃገራዊ አንድነትና ፍቅርን የሚጠናክሩ የተስፋ መልዕክቶች ተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በዝግጅቱ ተገኝተው ልዩ የበአል የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በምሽቱ የዋዜማ ዝግጅት ለአዲሱ አመት ስጦታ ከቻይና መንግስት የተበረከተው ርችት አምባሳደር አካባቢ እየተገነባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግዙፍ ህንፃ ላይ ተተኩሶ ለዋዜማው ድምቀትን ሰጥቷል።

 

በሶዶ ለማ


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዋዜማ ምሽት መርሃ ግብር አከናወነ