በመሬት መንሸራተት አደጋ የሶስት ሰዎች ህይዎት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ጃናሞራ ወረዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ በሰው ህይዎት እና በንብረት ላይ አደጋ ደርሷል።

በወረዳው ወይና ቀበሌ ትናንት ረፋድ ላይ በደረሰው አደጋ የሦስት ሰዎች ህይዎት አልፏል።

ከዚህ ባለፈም ግምቱ በውል ያልታወቀ ንብረትም ወድሟል።

የመሬት መንሸራተት አደጋው ዝናብ ባልጣለበት ሁኔታ መከሰቱን ከአመራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 


በመሬት መንሸራተት አደጋ የሶስት ሰዎች ህይዎት አለፈ