የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን በ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር እየተገነባ የሚገኘውን ደብሊው ኤ የዘይት ፋብሪካ ጎበኙ

ለግንባታው 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጭ እንደተደረገበት እና ከአራት ወይም ከአምስት ወራት በኋላ ሥራ እንደሚጀምር የዘይት ፋብሪካው ባለቤት አቶ ወርቁ አይተነው ተናግረዋል፡፡

የዘይት ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ የአካባቢውን ግብዓት የሚጠቀም በመሆኑ ለአርሶ አደሮች ምርት የገበያ ትስስር ለመፍጠር እንደሚያግዝ የገለፀ ሲሆን ለወጣቶች ከፍተኛ የሥራ ዕድል መፍጠሪያ እንደሚሆንም አቶ ወርቁ ተናግረዋል።

ፋብሪካው ወደ ምርት ሲገባ በቀን 450 ሺህ ሊትር የምግብ ዘይት ማምረት እንደሚችል የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ አቶ እንግዳወርቅ መኮንን ገልፀዋል፡፡

ከሰሊጥ፣ ከአኩሪ አተር፣ ከለውዝ እና ከኑግ ዘይቶችን ያመርታል ያሉት አቶ እንግዳወርቅ የሰሊጥ ዘይትን በግማሹ ወደ ውጭ ለመላክ መታቀዱንም ገልፀዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አባትና
መሐሪ የዱቄት ፋብሪካንም ጎብኝተዋል።

ምንጭ፡- አብመድ


የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን በ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር እየተገነባ የሚገኘውን ደብሊው ኤ የዘይት ፋብሪካ ጎበኙ