ስዊድን ለኢትዮጵያ 3 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች

ድጋፉ በኢትዮጵያ በቀጣይነት የሚከናወኑ የፍትህ ስርዓት፣ መልካም አስተዳደር እና የሰላም ግንባታ ስራዎችን ለማሻሻል የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

የስዊድን የዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚኒስትር ፔር ኦልሰን ፍሪድ በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ፔር ኦልሰን ፍሪድ በዛሬው ዕለትም ከሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ጋር በሰላም ግንባታ እና በዴሞክራሲ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያና ስዊድን ረጅም ጊዜያትን ያስቆጠረ ወዳጅነትና ትብብር ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ያነሱ ሲሆን፥ በቀጣይም ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።


ስዊድን ለኢትዮጵያ 3 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች