ጓዶች በህወሓት ትእዛዝ ምክንያት ከተከራየንበት ቤት ወጥተን አስቸጋሪ ቦታ ላይ እንገኛለን – አብርሃ ደስታ

Satenaw: Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!

ጓዶች በህወሓት ትእዛዝ ምክንያት ከተከራየንበት ቤት ወጥተን አስቸጋሪ ቦታ ላይ እንገኛለን። በአንድ ሳምንት ውስጥ

(1) ከዓረና መቀለ ቢሮ እንድንወጣ ተነገረን።

(2) የዓረና ድርጅት ጉዳይ ሓላፊ አቶ ተክለዝጊ ወልደገብርኤል ከተከራየው ቤት እንዲወጣ ተነግሮታል።

(3) ዓምዶም ገብረስላሴ ከተከራየው ቤት አስወጥቶውት ሌላ ቤት ተከራይቶ እንደገና ከአራት ቀን በኋላ ለቆ እንዲወጣ ተነግሮታል።

(4) አብርሃ ደስታ ለሦስት ዓመታት ተከራይቶ ይኖርበት ከነበረው ቤት እንዲወጣ ተደርጎ ሌላ ቤት ተከራይቶ ቀብድ ከከፈለ በኋላ አስከልክለውት ሌላ ቀይሮ እንደገና በካድሬዎች ማስጠንቀቅያ መሠረት ቤት ተከልክሎ ለወር ኪራይ የከፈለውን ገንዘብ ተመልሶለት አሁን በአንድ ትንሽ ቤት ውስጥ ይገኛል። ሻወር፣ ሽንትቤት ውሃ የሌለው ቤት ውስጥ! ዓምዶምም ነገ ወደኔ ይመጣል! ግን በዚህ አንንበረከክም! በረንዳ ላይ እያደርንም ህወሓትን ከስልጣን ለማባረር በእልህና በቁርጠኝነት እንታገላለን! መኖርያ ቤት ምናገኘው በህወሓት መቃብር ላይ እንደሆነ እናውቃለን! ድል የኛ ነው!

አብርሃ ደስታ

The post ጓዶች በህወሓት ትእዛዝ ምክንያት ከተከራየንበት ቤት ወጥተን አስቸጋሪ ቦታ ላይ እንገኛለን – አብርሃ ደስታ appeared first on ሳተናው: Satenaw: Ethiopian News/Breaking News: Your right to know!.


ጓዶች በህወሓት ትእዛዝ ምክንያት ከተከራየንበት ቤት ወጥተን አስቸጋሪ ቦታ ላይ እንገኛለን – አብርሃ ደስታ