በኦህዴዶች የኢዜማ አባላት ድብደባና እስር በሃረር በጃዋር የሚዘወረው ኦዴፓ አስነዋሪ ተግባር!!

Satenaw: Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!

ትናንትና፡
======
አንዷለም አራጌ በዋሽንግተን ዲሲ ስብሰባ ላይ ይህን አለ

“…በአሁኑ ወቅት ኦሮሚያ ውስጥ ትልቅ ነውር እየገጠመን ነው። ካለፈው ስርአት ተምረው የተሻሉ አመራሮችና የፖለቲካ ልሂቃን ይመጣሉ ስንል ይባስ አሳፋሪ ነገር እየገጠመን ነው። በተለይ ኦዴፓ በአስቸኳይ ስህተቱን ካላረመ ዋጋ ያስከፍለዋል።….ብዙ ችግሮች አሉ። ሁሉን መናገር ስለማንፈልግ ነው። ኢትዮጵያውያን ነን። የትም ቦታ ሄደን ህዝብ ማናገር የዜግነት መብት አለን።..… አይ እዚህ አይፈቀድላችሁም ሊሉን አይችሉም። ቆርጠን ወደ ስራ ስንገባ በኔ ሬሳ ላይ ይሆናል እንጂ ማንም የኢትዮጵያን አፈር እንዳልረግጥ ሊያግደኝ አይችልም።”

ዛሬ፡
===

በኦህዴዱ አክራሪ ብሄረተኛ ክንፍ የሚዘወረው የሀረር ፓሊስ ዛሬ የሀረር ከተማ የኢዜማ አመራሮች ላይ ድብደባ እና እስር ፈጽሟል። አክራሪ ቡድኑ በምስሉ ላይ የሚታዬውን የኢዜማ ፓርቲ የሀረር አደራጅ የሆነውን ወጣት ሄኖክን በተቀነባበረ ሴራ ድብደባ ከፈጸመበት በኋላ ለእስር ዳርጎታል።
———

ጠ/ሚ የሚመሩት ኦዴፓ ከጃዋር ጋር በትብብር የሚቆጣጠረው የቄሮ መንጋ በማንአለብኝነት ሀገር እያመሰ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እናደርጋለን ማለት አይናቹን ጨፍኑ እናሙኛቹ ነው!

ግርማ ካሳ

The post በኦህዴዶች የኢዜማ አባላት ድብደባና እስር በሃረር በጃዋር የሚዘወረው ኦዴፓ አስነዋሪ ተግባር!! appeared first on ሳተናው ዕለታዊ ዜናዎች:ጥናታዊ ጽሁፎችና ዝማኔዎች: መረጃ ማግኘት መብተዎ ነው!.


በኦህዴዶች የኢዜማ አባላት ድብደባና እስር በሃረር በጃዋር የሚዘወረው ኦዴፓ አስነዋሪ ተግባር!!