“አዴፓ አመራሮቹን እስኪተካ፤ የአማራ ህዝብም ከሀዘኑ ቀና እስከሚል በትዕግስት ጠብቀናል። ከእንግዲህ ግን ሁሉንም አይነት የትግል እንቅስቃሴ በማድረግ የአማራ ተቆርቋሪዎችን እናስፈታለን።” ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ /የአብን ሊቀመንበር

Satenaw: Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!

አማራ ሚዲያ ማዕከል /አሚማ
መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ

ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የጅምላ እስሩን ለማስቆም ዝምታን መርጧል በሚል ለተጠየቁት ጥያቄ የሰጡት ምላሽ እንደሚከተለው ነው ።

የሰኔ 15 ክስተት የአማራን ህዝብ የጎዳና ወንድሞቻችንን ያሳጣን ነው። ይህንን በመከተል ደግሞ ኦዴፓ መራሹ የፌደራል መንግስት አማራን ለማጥቃት ተጠቅሞበታል። በዚህም በተለይም የአብን አመራሮችና አባላት ታስረውብናል። ይሄ ግፍ ሲፈፀምበት አብን ዝም አይልም ብለው አስበው ነበር።

የአማራ አንቂዎች፣ የአብን አመራሮችና አባላት በጅምላ ሲታሰሩበት አብን ደጋፊዎቹን በሙሉ አንቀሳቅሶ በሰላማዊ ሰልፍ ጫና እንዲያደርግ በኦዴፓ ታስቦ ነበር። በዚህም አማራ ክልልን የሁከት ማዕከል እንዲሆን ሌላ ተጨማሪ አደጋ ለማድረስም ታቅዶልን ነበር። እኛ ግን ይህንን አላደረግንም።

በመጀመሪያ አብን ባደረገው ትዕግስት ለውጡን ፈትነንበታል፣ ትክክለኛ ለውጥ ነው ወይስ? የማስመሰል የሚለውንም አረጋግጠናል።

ሌላው የክልሉ ህዝብ ከፍተኛ አመራሮቹንና ልጆቹ በሞት አጥቶ ሀዘን ላይ ነበር። በዚህ ሀዘኑ ላይ ቆስቁሰን ወደ ሰላማዊ ሰልፍ አልወሰድነውም – ሰላማዊ ሰልፉ ከቁጥጥር ወጥቶ ሌላ አደጋ እንዲፈጠርም አልፈቀድንም።

አዴፓና የክልሉ መንግስት ያጣቸውን አመራሮቹን እስኪተካ ታግሰናል። የአማራ ህዝብም ከሀዘኑ ቀና እስከሚል በትዕግስት ጠብቀናል። ከእንግዲህ ግን ሁሉንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ የአማራ አንቂዎችን እናስፈታለን።

The post “አዴፓ አመራሮቹን እስኪተካ፤ የአማራ ህዝብም ከሀዘኑ ቀና እስከሚል በትዕግስት ጠብቀናል። ከእንግዲህ ግን ሁሉንም አይነት የትግል እንቅስቃሴ በማድረግ የአማራ ተቆርቋሪዎችን እናስፈታለን።” ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ /የአብን ሊቀመንበር appeared first on ሳተናው ዕለታዊ ዜናዎች:ጥናታዊ ጽሁፎችና ዝማኔዎች: መረጃ ማግኘት መብተዎ ነው!.


“አዴፓ አመራሮቹን እስኪተካ፤ የአማራ ህዝብም ከሀዘኑ ቀና እስከሚል በትዕግስት ጠብቀናል። ከእንግዲህ ግን ሁሉንም አይነት የትግል እንቅስቃሴ በማድረግ የአማራ ተቆርቋሪዎችን እናስፈታለን።” ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ /የአብን ሊቀመንበር