የእነብርጋዲዬር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጉዳይ ለጥቅምት 12 ቀን ተቀጠረ

Satenaw: Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!

የእነብርጋዲዬር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የምርመራ ጉዳይ ላይ የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፖሊስ ምርመራ ቡድን የጠየቁት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ይግባኝ ውድቅ ተደርጓል፡፡

ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዛሬ ረፋድ ባስቻለው ችሎት የመርማሪ ቡድኑ የጠየቀውን የተጨማሪ ቀጠሮ ይግባኝ ውድቅ አደርጓል፡፡ እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2012ዓ.ም ድረስም ክስ እንዲመሠርት ትዕዛዝ በመስጠት መዝገቡን ዘግቷል፡፡

መርማሪ ቡድኑ ይግባኝ ከጠየቀበት ጊዜ ጀምሮ ተጠርጣሪዎቹ ለ64 ቀናት በማረፊያ ቤት የቆዩ በመሆናቸውና መርማሪ ቡድኑ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ መረጃ እያጣራ ያለ መሆኑን፣ ቀሪ ምስክሮችም ጥቂት መሆናቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት ጥቅምት 12 ቀን 2012ዓ.ም ክስ እንዲመሠረት ትዕዛዝ በመስጠት መዝገቡን ዘግቷል፡፡

ዘጋቢ፡- ዘላለም አስፋው/ አብመድ

The post የእነብርጋዲዬር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጉዳይ ለጥቅምት 12 ቀን ተቀጠረ appeared first on ሳተናው ዕለታዊ ዜናዎች:ጥናታዊ ጽሁፎችና ዝማኔዎች: መረጃ ማግኘት መብተዎ ነው!.


የእነብርጋዲዬር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጉዳይ ለጥቅምት 12 ቀን ተቀጠረ