በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን እብናት አካባቢ ከሌሊት ጀምሮ ተኩስ መኖሩ ተገለፀ

Satenaw: Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ

ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም ከስፍራው በስልክ የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው ካሳለፍነው ሌሊት ጀምሮ የአማራ ልዩ ሀይልን ዩኒፎርም የለበሰ አምስት ፓትሮል ጦር ወደ ደቡብ ጎንደር እብነት ደጋ መልዛ አካባቢ በማቅናት ተኩስ መክፈቱን ምንጫችን ገልፀዋል።

ምንጫችን ሲቀጥሉ የተሰማራው ጦር በአካባቢው እነ ሻለቃ ፋኖ አስቻለው ደሴ አሉ በሚል ተኩስ እንደተከፈተ የገለፁ ሲሆን የአስቻለው ደሴን ቤተሰቦች ቤት በከባድ መሳሪያ መምታታቸውንም አክለው ተናግረዋል።

ከሌሊት ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ የተኩስ ድምፅ መኖሩን የተናገሩት ምንጫችን የእብናት ደጋ መልዛ ሕዝብም “ምን ችግር ተፈጠረ?” በሚል ጦሩን ለማናገር ቢሞክርም ተረጋግቶ መልስ ከመስጠት ይልቅ መበተንን እንደመረጡ ተገልጧል።

ሌላኛው ምንጫችን ትናንት ምሽት በደብረ ታቦር በአዲሱ ወረዳ በአይሳ በኩል አድርገው በፓትሮል የተጫኑ የአማራ ልዩ ሀይልን ልብስ የለበሰ ጦር ከአንድ አንቡላንስ ጋር ወደ እብናት ማለፋቸውን ገልፀዋል።

ወደ እብናት ደጋ መልዛ ልዩ ስሙ ላንጎ በተባለ
አካባቢ በሻለቃ አስቻለው ደሴና በቤተሰቦቹ ላይ ተኩስ መከፈቱን ምንጫችን አውስተዋል።

ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም ንጋትም በእብናት በኩል በሁለት ፓትሮል የተጫነ ተጨማሪ ጦር መላኩን ገልፀዋል።

የአማራ ሚዲያ ማዕከል ስለሁኔታው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የአማራ ክልል የሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገር ቢያናግርም በእናት አካባቢ የተፈጠረውን ችግር እንደሚያውቁትና እየተከታተሉት መሆናቸውን በመግለፅ ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

The post በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን እብናት አካባቢ ከሌሊት ጀምሮ ተኩስ መኖሩ ተገለፀ appeared first on ሳተናው ዕለታዊ ዜናዎች:ጥናታዊ ጽሁፎችና ዝማኔዎች: መረጃ ማግኘት መብተዎ ነው!.


በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን እብናት አካባቢ ከሌሊት ጀምሮ ተኩስ መኖሩ ተገለፀ