በቤይሩት ያለ ህጋዊ ሰነድ ይኖሩ የነበሩ 263 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ ፡፡

አባይ ሚዲያ ( መስከረም 27 ፣ 2012 ) በመካከለኛ ምስራቅ ሀገሪቷ ቤይሩት ያለ ህጋዊ ሰነድ ይኖሩ የነበሩ 263 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገልጿል ። ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሀገራቸው የተመለሱትም ካሳለፍነው ሐሙስ ማታ ጀምሮ እስከ እሁድ ማታ ድረስ በነበሩት ተከታታይ ቀናት መሆኑ ታውቋል ። በዚህ መሰረትም በአጠቃላይ 263 ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ዜጎች ከልጆቻቸው ጋር በሰላም ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንፅላ ጄነራል ፅህፈት ቤት አስታውቋል።


በቤይሩት ያለ ህጋዊ ሰነድ ይኖሩ የነበሩ 263 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ ፡፡