ወደ ጣልያን የምትጓዝ መርከብ ተገልብጣ 13 ሠዎች መሞታቸው ተገለጸ፡፡

አባይ ሚዲያ (መስከረም 27፣2012) ከ50 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን በጫነችው የሥደተኞች ጀልባ ላይ ከተሳፈሩት ሰዎች ውስጥ 13 የሚሆኑቱ ሰዎች ወዲያውኑ የሞቱ ሲሆን ቀሪዎቹ ከ 22 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በስደተኞች አድን መትረፋቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ስደተኞቹ ላምፔዱሳ ደሴት ላይ ይህ አደጋ እንዳጋጠማቸው ያስታወቀው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥደተኞች ተቋም ስደተኞቹ መዳረሻቸውንም ወደ ጣሊያን አድርገው ሲጓዙ የነበሩ ስደተኞች መሆናቸውን እና ጀልባዋ ከ ቱኒዚያ እንደተነሳች አስታውቋል፡፡
አብዛኛዎቹ ስደተኞችም ከቱኒዚያና ከሌሎች የሰሜን አፍሪካ ሃገራት የተውጣጡ ናቸው ተብሏል፡፡
በህገወጥ ስደት ምክንያት በ2019 ብቻ በዚህ ባህር ከ1 ሺህ በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ህይወታቸው ማለፍን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡
የዚህ ሰለባ የሚሆኑት አብዛኛዎቹ ስደተኞች መነሻቸው ከአፍሪካ እንደሆነም ተገልጿል፡፡


ወደ ጣልያን የምትጓዝ መርከብ ተገልብጣ 13 ሠዎች መሞታቸው ተገለጸ፡፡