አንድነት ፓርክ ከነገ ጀምሮ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ለጎብኚዎች ክፍት ይደረጋል

Satenaw: Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!

ጥቅምት 10, 2019
እስክንድር ፍሬው/VOA
በኢትዮጵያ ታላቁ ቤተመንግሥት የተገነባው አንድነት ፓርክ የኢትዮጵያና የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ከጥቂት ቀናት በኋላም ለሕዝብ ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል።

ከሕዝብ ርቆ የቆየው ታላቁ ቤተመንግሥት ለጉብኝት ክፍት መደረጉ፤ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የተጀመረው ለውጥ ተምሳሌት መሆኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የውጭ ቋንቋዎችና ዲጂታል ዘርፍ ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ተናግረዋል።

“አንድነት ፓርክ” ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት ይደረጋል

በዛሬው ዕለት የተመረቀው “አንድነት ፓርክ” ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት ይደረጋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የውጭ ቋንቋዎችና ዲጂታል ዘርፍ ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም አንድነት ፓርክን በተመለከተ ለአሜሪካ ድምፅ የአዲስ አበባ ዘጋቢ እስክንድ ፍሬው ማብራሪያ ሰጥተዋል። (የቃለ ምልልሱን ሙሉ ክፍል ከተያያዘው ድምፅ ያዳምጡ)

Posted by VOA Amharic on Thursday, October 10, 2019

ከዳግማዊ አፄ ምኒሊክ እስከ ዛሬው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ያሉት መሪዎች ኢትዮጵያን ከ130 ዓመታት በላይ ለሆነ ጊዜ ያስተዳደሩትም ከዚሁ ቤተ መንግሥት ነው።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

The post አንድነት ፓርክ ከነገ ጀምሮ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ለጎብኚዎች ክፍት ይደረጋል appeared first on ሳተናው ዕለታዊ ዜናዎች:ጥናታዊ ጽሁፎችና ዝማኔዎች: መረጃ ማግኘት መብተዎ ነው!.


አንድነት ፓርክ ከነገ ጀምሮ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ለጎብኚዎች ክፍት ይደረጋል