የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ደጋፊዎች በስቶክሆልም ስዊድን ድምፃቸውን ማሰማታቸው ተገለፀ

Satenaw: Ethiopian News & Breaking News: Your right to know!

አሚማ
ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ

የባላደራው ደጋፊዎች በስቶክሆልም ስዊድን በዛሬው ዕለት በአደባባይ በመውጣት ድምፃቸውን አሰምተዋል።

ሰልፈኞቹ በአሰሙት ተቃውሞ መንግስታዊ ሽብር ይቁም ፣ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ፤ የአብይ መንግስት አፋኝ ነው፣አዲስ አበባ የመላው ኢትዮጵያዊያን ነች የሚሉ እና ሌሎችም መልዕክቶችን በሰልፉ ላይ አሰምተዋል ።

የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት በምክትል ሰብሳቢው ጋዜጠኛ ኤርሚያስ ለገሰ ከኢትዮጵያ ውጭ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገሮች ስለ አዲስ አበባ ቀጣይ ፋንታ እና እየገጠሟት ስላሉ ችግሮች እንዲሁም ስለባላደራው አጠቃላይ ስለ ተቋቋመለት ዓላማ በተለያዮ ከተሞች ህዝባዊ ውይይት ሲያደርግ እንደነበር ይታወቃል።

የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት ስለ አዲስ አበባ ጉዳይ ድምፁን ለመንግሥትና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ጥያቄዎቹን ለማሰማት በአዲስ አበባ ከተማ ሰልፍ ቢጠራም በአስራ አንደኛው ሰዐት የከተማዋ ፖሊስ ሰልፋን በመከልከል እንዳይካሄድ አግዷል።

የባላደራ ምክርቤቱም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ለህዝብ ደህንነተሰ እና ሰላም ሲባል ሰልፋን መሰረዙ ይታወቃል።

በቀጣይም ሰሜን አሜሪካ ጨምሮ በተለያዮ የአውሮፓ ከተሞች የተቃውሞ ድምፆች እንደሚሰሙ ይጠበቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተጠራውን ሰልፋ የባላደራው ምክር ቤት ቢሰርዘውም ፣ የሰልፉ አስተባባሪ ናችሁ የተባሉ ወጣቶች እየተፈለጉ እየታሰሩ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል።

The post የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ደጋፊዎች በስቶክሆልም ስዊድን ድምፃቸውን ማሰማታቸው ተገለፀ appeared first on ሳተናው ዕለታዊ ዜናዎች:ጥናታዊ ጽሁፎችና ዝማኔዎች: መረጃ ማግኘት መብተዎ ነው!.


የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ደጋፊዎች በስቶክሆልም ስዊድን ድምፃቸውን ማሰማታቸው ተገለፀ